የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ተጠሪነቱ ለኦፐሬሽን አገልግሎት ጄኔራል ዳይሬክተር ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የዘርፉ ዓላማዎች ለማስፈጸም የሚችል ዕቅድና በጀት ሲዘጋጅ ይሳተፋል፣ሲጸድቅም ይፈጽማል፣የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤
  • የመ/ቤቱ ዓመታዊ ግቦች ለማስፈጸም የሚያስችል ግልጽና ከፊዚካል ዕቅድ ጋር የተጣጣመና የግዥ አፈጻጸም መመርያ መሠረት በማድረግ የተቋም ግዥ ዕቅድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ሲጸድቅም ይፈጽማል፤
  • በየበጀት ዓመቱ የተፈቀደ የዕቃና አገልግሎት ግዥ በመንግስት በተፈቀደ የግዥ አፈጻጸም መመርያ መሠረት በግልጽነትና በተጠያቂነት ከሙስና በጸዳ መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
  • የመ/ቤቱ የቋሚ ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ዘመናዊ የአሠራር ስርዓት የተከተለ መሆኑን ያረጋግጣል፤
  • የተቋሙ ንብረቶች በአግባቡ ለተፈቀደለት ዓላማ ጥቅም ላይ መዋሉና የሚያስረዱ የንብረት አጠቃቀም ሪፖርቶችና መግለጫዎች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤
  • በተቋሙ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር በሚመለከት የወጡ አዋጆች፣ደንቦችና የአሠራር መመርያዎች ስራ ላይ መዋላቸው ያረጋግጣል፤
  • የዘርፉ ቋሚ ንብረቶች ተገቢው ጥበቃ የተደረገ መሆኑና ረዥም ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የአሠራር ስርዓት አጥንቶ ያቀርባል ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የንብረት አጠቃቀምና አያያዝ የፈጻሚ ሠራተኞችና ተጠቃሚዎች ግንዛቤ እንዲዳብር ክትትል ያደርጋል፣ይደግፋል፣
  • በመ/ቤቱ አስፈላጊው የግዥ አፈጻጸምና የንብረት አያያዝ የሚያስረዱ ሰነዶች፣ካርዶችና መዛግብ መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፤
  • የተቋም የግዥ አፈጻጸምና የንብረት አጠቃቀም በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋል የተገኘው ውጤት ለተቋሙ አመራር አካላት ያሣውቃል በኦዲት የተገኙ ግኝቶች ወዲያውኑ እንዲስተካከሉ ያደርጋል፤
  • በስራ ሂደቱ በየደረጃ ያሉትን ፈጻሚዎች የመልካም አስተዳደርና የስነ ምግባር መርሆዎች አክብረው አገልግሎት እንዲሰጡ ይከታተላል፣ይደግፈል፤
  • በዳይሬክቶሬቱ ያሉት ፈጻሚዎች የስራ አፈጻጸማቸው ለማሻሻል የሚረዱ ስልጠናዎች እንዲያገኙ በመንግስት የስልጠና አፈጻጸም መመርያ መሠረት ያቅዳል፣ ሲፈቀድም ይፈጽማል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.