የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሰብልና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ሆኖ የሆርቲካልቸር ሰብሎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፡-

  • የሆርቲካልቸር ልማት አቅም የመገንባትና የማሳደግ ስራዎችን መምራት እንዲሁም በሆርቲካልቸር ልማቱ ውስጥ የቁጥጥር እና የጥራት ማረጋገጥ ተግባራት በአግባቡ መከናወናቸውን በበላይነት የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፤
  • ለሆርቲካልቸር ልማቱ የሚያስፈልጉና በየደረጃው ባሉ ስትራቴጂካዊ ውሳኔዎችን ለሚሰጡ አካላት የሚያገለግሉ የተደራጁ መሠረታዊ የሆርቲካልቸር ልማት መረጃዎች መኖራቸውን ያረጋግጣል፤
  • ለፖሊሲ እና ስትራቴጂ ቀረፃ እና ትግበራ የሚጠቅሙ ያላቸውን መነሻ ሀሳቦችን ማመላከት እና ለቀረቡትም ማረጋገጫ ይሰጣል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት በቀጥታ የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ደረጃዎችና ተግባራት ተቀባይነት ማግኘታቸውንና ተሻሽለውም መተግበራቸውን ይከታተላል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን የሚደግፉ የቴክኖሎጂዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች ልየታ፣ መረጣ፣ ጥንቅር እና የማላመድ ተግባራትን በበላይነት ይመራል፤
  • በሆርቲካልቸር ልማቱ ውስጥ አስፈላጊ የቁጥጥር ደረጃዎች እና ትግበራዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን በበላይነት ይመራል፤
  • የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግና የፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል በጋራ በማፅደቅ ለተፈፃሚነታቸው አስፈላጊውን ሀብት እንዲመደብ ያደርጋል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት ውጤታማነት ከልህቀት ማዕከልነት አኳያ እንዲሁም የስልጠና ፕሮግራሞችና ጠቃሚ ሀሳቦችን በማፍለቅ ሂደት በበላይነት ይሠራል፤
  • በሆርቲካልቸር ልማት የግብርና ውስጥ ባሉ ክፍሎች መካከል የዕውቀት ልውውጥ እንዲኖር እንዲሁም የማበረታቻ ሥራዎች መኖራቸውን ያረጋግጣል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት የሥራ ዕቅድ እና ትግበራው በበላይነት በመምራት ይቆጣጠራል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት ፍትሃዊ በጀት አጠቃቀም ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት አስፈላጊ የሰው ኃይል ልየታ እና መሟላት ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፤
  • የሆርቲካልቸር  ልማት ፖሊሲዎች እና የትግበራ የሙያ ደረጃዎች በትክክል መዋቀራቸውን እንዲሁም ባለተቋረጠ አግባብ መተግበራቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት ሪፖርቶች ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱና በጥራት  መቅረባቸውን በበላይነት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት ሙያ  ክፍል  ሠራተኞች  የመፈፀም  እና  የማስፈፀም  አቅም  ለማሳደግ ወቅቱን የጠበቀ የአፈፃፀም ግምገማ፣ የመምራት እና የማብቃት እንዲሁም አፈፃፀምን የተመለከቱ ውይይቶች እና ግብረ-መልስ እንዲኖር በማድረግ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • የሆርቲካልቸር ልማት የክሂሎት እና ብቃት ፍላጎቶች ለማሟላት ስልታዊ የልየታ ስራዎችን በበላይነት ይመራል፤
  • የተለያዩ ውሳኔዎችን ለመስጠት የሚያስችሉ ኮሚቴዎች ወይም አደረጃጀቶች እንዲኖሩ በማድረግ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ድርሻ በመውሰድ ተሳትፎ ማድረግ፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.