ግብርና ሚኒስቴር

በአገልግሎቶች ይሳተፉ

 

 

የግብርና ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ጎብኝዎች ብዛት

View My Stats

ዜና

 

የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ከክልሎችና ከተጠሪ መ/ቤቶች ከተውጣጡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ከተጠሪ መ/ቤቶች፣ ከሁሉም ክልሎችና ከድሬደዋ መስተዳድር ከተውጣቱ የግብርና ቢሮ እና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር መጋቢት 26 እና 27 ቀን 2006 ዓ.ም የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

ለበለጠ መረጃ

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በአዲስ መልክ እየተቀረፀ ያለው የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ይበልጥ ውጤታማ ነው ተባለ፡፡

ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት በአዲስ መልክ እየተቀረፀ ያለው የልማታዊ ሴፍትኔት ፐሮግራም መሰረቱ የሰፋና ከሌሎች የልማት አከላት ጋር በቅንጅት ስለሚተገበር ይበልጥ ውጤታማ በመሆኑ ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ቤተሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስችላቸው የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ገለፀ፡፡

ለበለጠ መረጃ

በኦሮሚያ ክልል በአትክልትና ፍራፍሬ የተሰማሩ አርሶአደሮች ማሳ ላይ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ መርቲ ወረዳ ወትሮዲኖ ቀበሌ በአትክልትና ፍራፍሬ የተሰማሩና ወደ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮች ማሳ መጋቢት 19/2ዐዐ6 ዓ.ም የመስክ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

ለበለጠ መረጃ

የወረዳ አደጋ ክስተት ፕሮፋይል ሥራ ይፋ ተደረገ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ መረጃ ከተሰበሰበላቸው ወረዳዎች መካከል የማመሳከሪያ ሥራ ተጠናቅቆ ለ200 ወረዳዎች ፕሮፋይሉ መዘጋጀቱን ይፋ የሚያደርግ የምክክር አውደ ጥናት ከባለድርሻ አካላት ጋር አደረገ፡፡

                                                                                                     ለበለጠ መረጃ

ብሔራዊ የአደጋ ክስተት ስጋት  ሥራ አመራር ፖሊሲ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ   እንዳለው ተገለፀ፡፡

አዲሱ ብሄራዊ የአደጋ ክስተት ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኡደት ውስጥ ያሉትን ተግባራት በሙሉ የሚያካትት፣ በሁሉም አደጋዎች ላይ የሚያተኩር እና ብዙ ሴክተሮችን የሚያሳትፍ በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የግብርና ሚኒስቴር አደጋ መከላከልና ዝግጁነት እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ምትኩ ካሳ ገለፁ፡፡  

                                                                                                       ለበለጠ መረጃ

የግብርና ሚኒስቴር፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲና የሀንሰን የአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ እያከናወነ ላለው የአፈር መረጃ ስርዓት ግንባታና የአፈር ለምነት ማሻሻያ ስራዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እውቀት የተደገፈ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲና መቀመጫው በቻይና ካደረገው ቤጂንግ ሀንሰን አለም ዓቀፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ለበለጠ መረጃ

የግብርና ዕድገት ፕሮግራም የአጋማሽ ዘመን አፈጻጸም አውደ-ጥናት አካሄደ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ዕድገት ፕሮግራም አጋማሽ ዘመን የአፈጻጸም ቅኝት አውደ-ጥናት ከመጋቢት 1-2/2006 ዓ.ም  ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ለበለጠ መረጃ

 

 

ዜናዎችና ለውጦች