የህግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ

የህግ አገልግሎት ተጠሪነቱ ለሚንስትር ጽ/ቤት ሆኖ የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ለሚንስትር መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን የውልና የተናጥል ሥልጣንና ተግባራት ከሌሎች የሀገሪቱ ሕጎችና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር ተጣጥሞ ሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

  • የሥራ ክፍሉን ሥራዎች በመመራት፣ የህግ ጥናት በማድረግ ከህግ ማስረጽ ጀምሮ አዲስ ወይም የማሻሻያ የሕግ ረቂቅ ዝግጅትን በመመራት እና የመሥሪያ ቤቱን ጥቅም ያስከብራል።
  • የህግ ጉዳዮች አገልግሎቱን ሥራዎች ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፡፡
  • ለሥራ ክፍሉ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል፣ ቁሳቁስና በጀት እንዲሟላ ያደርጋል፣ ያስተዳድራል፣ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፡፡
  • በዘርፉ ለሚገኙት ባለሙያዎች ሥራዎችን ከፋፍሎ ይሰጣል፣ ይደግፋል፣ አፈፀፀማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፡፡
  • በአፈፃፀም ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን እየተከታተለ አፋጣኝ መፍትሔ ይሰጣል፣እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
  • ለሥራ ክፍሉ  ባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታ ይፈጥራል፣ያላቸውን የአቅም ክፍተት በመለየት የሚሞላበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
  • የሥራ ዘርፉን አፈፃፀም ውጤታማነት ይገመግማል፣ ደንቦችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውንና መከበራቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • የመሥሪያ ቤቱን የህግ አገልግሎት ሥራዎች አፈፃፀም ለማሻሻል የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮዎች የሚገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
  • የዘርፉን አጠቃላይ የዕቅድ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ለበላይ ኃላፊ ያቀርባል፡፡
  • መሥሪያ ቤቱን በሚመለከት የሚዘጋጁ ረቂቅ ህጎችከግብርና ፖሊሲዎች አንፃር መቃኘታቸውን ያረጋግጣል፣ ረቂቅ ፖሊሲ ዝግጅቶች ላይ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ለማዘጋጀት በጥናት የተደገፉ አዲስ ወይም የማሻሻያ ሃሳቦችን ያመነጫል፣እንዲመነጩ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
  • በመሥሪያ ቤቱ የሚወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከሀገሪቱ ሌሎች ሕጎች ጋር የማይጋጩ መሆኑን ያረጋግጣል ወይም ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመመካከር የትብብር አሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.