የፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ

የፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡

  • የመ/ቤቱን ጥሬ ገንዘብ በማስተዳደር፣ የመ/ቤቱን የሂሳብ እንቅስቃሴዎች በፋይናንስ ህግ መሰረት እንዲከናወኑ በማድረግ፣ የተከፋይ፣ የተሰብሳቢና ፈሰስ ሂሳቦችን አፈጻጸም በመከታተል፣ የመ/ቤቱን የሂሳብ ሪፖርት በማዘጋጀት፤ የአቅም ግንባታ ስራዎች ለማከናወን ጥናት በማካሄድ ውጤታማ የፋይናንስ እንቅስቃሴ እንዲኖር ያደርጋል።
  • ከመስሪያ ቤቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት የስራ ክፍሉን እቅድ በወቅቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ስራዎችን ለስራ ክፍሎች ፤ለቡድኖችና  ለባለሙያዎች  በማከፋፈል  ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • የሥራ ክፍሉን ዓመታዊ በጀትና የሥራ መርሀ ግብረ ያዘጋጃል ፣ያስተዳድራል፡፡
  • በስራ ክፍሉ የሚገኙ ቡድን መሪዎችን ባለሙያዎችንና ሠራተኞችን ያስተባብራል፣የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜና ጥራት መከናወናቸውን ይከታተላል ፡፡
  • አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችና የሰው ሀይል እንዲሟላ ያደርጋል ፣ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ይሰጣል፡፡
  • ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች የሚያስፈልጉት አገልግሎቶች በአግባቡ መሰጠታቸውን እና ቅሬታም እንዳይከሰት ይከታተላል፤ቅሬታ ሲያጋጥም በወቅቱ መፍትሄ ይሰጣል፡፡
  • ከሚመለከታቸው የመንግስት አስፈጻሚ መ/ቤቶች በየጊዜው የሚተላለፉ መመሪያዎች ተፈጻሚነት እንዲያገኙይከታተላል፡፡
  • ከአበዳሪና ለጋሽ  ድርጅቶች  ጋር  በሚደረገው የፋይናንስ ስምምነት መሰረት የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች መከናወናቸውን ይከታተላል ፡፡
  • የመስሪያ ቤቱ ገቢ እንዲጨምር ጥናት ያዘጋጃል በበጀት ጥያቄ ውስጥ እንዲካተት ለበላይ አመራሩ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል ፡፡
  • የፋይናንስ አሰራር ስርአትን ለማዘመን እንዲያስችል ችግሮችን ያስጠናል ለባለሙያዎችም ስልጠና እንዲያገኙ የስልጠና ፕሮግራሞችን ያፈላልጋል ያመቻቻል ፡፡
  • ከቡድኖች የሚቀርቡ የፋይናንስ አሰራር ስርአትን ለማዘመን የሚያስችል ጥናት በማቀናበር እና አመቺ መሆኑን በማረጋገጥ በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል ፡፡
  • በስራ ላይ ያሉት የፋይናንስ ቴክኖሎጂዎች IBEX/IFMIS ሰራተኞች እንዲጠቀሙ በማድረግ ቀልጣፋና ውጤታማ ሪፖርት እንዲቀርብ ያደርጋል ፡፡
  • በተሰጠው የበጀት ጣሪያ መሠረት የሥራ ክፍሉን በፕሮግራም በጀት መርህ መሰረት የሶስት ዓመትና ዓመታዊ በጀት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
  • የፋይናንስግልፀኝነትና ተጠያቂነት ለማስፈን የሚያግዙ የአሰራር ስርሃቶችን ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
  • መ/ቤቱ ዓመታዊ የጸደቀ በጀት ማስታወቂያ ሲደርሰው በፕሮግራም፣በንዑስ ፕሮግራም፣ በውጤት በዋና ዋና ተግባራት/ በካፒታል ፕሮጄክቶችና እና በዝርዝር የወጪ መደብ እንዲመዘገብ ያደርጋልlየፕሮግራሞች ያሳውቃል አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
  • ገንዘብ ፍሰት ከባለፈው አመት አፈጻጸምና የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት አንዲዘጋጅ ያደርጋል፣አፈጻጸሙንይከታተላል፡፡
  • በተፈቀደው በጀትና በተዘጋጀው የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት ዕቅድ መሠረት የክፍያ መጠየቅያና መፍቀጀ ቅጾችን አጽድቆ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
  • በጥሬ ገንዘብና በባንክ ያለውን ሂሳብ በየጊዜው እየተከታተለ የመ/ቤቱን የገንዘብ አቅም እንዲታወቅ ያደርጋል፡፡
  • የመሥሪያ ቤቱን የፋይናንስ እንቅስቃሴ ለታለመለት አላማ መዋሉን እና በአግባቡ መመዝገቡን ይቆጣጠራል ፣ ለዕቅድና በጀት አዘገጃጀት የሚረዱ መግለጫዎች ያዘጋጃል ፡፡
  • የስራ ክፍሉን የበጀት እጥረት ሲያጋጥም ተጨማሪ በጀትና ከፊዚካል እቅድና አፈጻጻም አካያ ከፕሮግራም ሃላፊዎች ጋር በመመካከር የበጀት ዝውውር እንዲፈቀድ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
  • ለመ/ቤቱ የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎችን አግባብነት በማጣራት ለሚመለከተው ቡድን መሪ ወይም ባለሙያ ይመራል ፣አፈጻጸሙንም ይቆጣጠራል፡፡
  • በመ/ቤቱ ስም የሚገኙ የእርዳታና ብድር ገንዘቦች በሚደረጉ ስምምነቶችና የአሠራር ማንዋሎች መሠረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመተባበር በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣የምክር  አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡
  • የሳጥን የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ወቅቱን ጠብቆ መደረጉን ይቆጣጠራል፡፡
  • መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የሚሰበሰቡ ገቢዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውንና በየዕለቱ ወደ ባንክ መተላለፋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
  • የመ/ቤቱን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በአግባቡ ማስተዳደርና ለታለመለት አላማ  እንዲውል በማድረግ ሀብትና ንብረትን ከብክነት ይከላከላል፡፡
  • ለሂሣብ ስራ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ፎርማቶች፣መዛግብቶችና ቼኮችና ሰነዶች በአግባቡ መያዛቸውንና ስራ ላይ መዋላቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መቆጣጠሪያ ስልት ይቀይሳል፣በትክክል በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ይከታተላል፡፡
  • የአለም አቀፍ ግዥ ሲከናወን ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲከፈት ማድረግ፤አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
  • በተሰጠው የስልጣን ውክልና መሠረት የደመወዝና የሥራ ማስኬጃ ልዩ ልዩ የክፍያ ጥያቄዎች አስፈላጊነት በመመርመር እና ትክክለኛነት በማረጋገጥ የክፍያ ቼክና ማዘዣዎች በፊርማው ያፀድቃል፡፡
  • ከመ/ቤቱ የሚመጡ የግዥና አገልግሎቶች የክፍያ ሰነዶችን በመመሪያው መሰረት መሆኑን አጣርቶ ይመራል፤ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፡፡
  • የመስሪ ቤቱን የባንክና የመዝገብ ሂሳብ መሰራቱንና ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፡፡
  • ከመንግስት የሚመደብ በጀት፤ ከዕርዳታና ብድር ለሚገኙ ገንዘቦች ማንቀሳቀሻ የሚከፈቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮችን ይቆጣጠራል፤የተከፈቱበትን አላማ ሲያጠናቅቁ በወቅቱ እንዲዘጉ ያደርጋል፡፡
  • ጥሬ ገንዘብና በባንክ ያለውን ሂሳብ በየጊዜው እየመረመረ የመ/ቤቱን የገንዘብ  አቅም እንዲታወቅ ያደርጋል ፡፡
  • የመ/ቤቱን የጥሬ ገንዘብ አጠቃቀም ለታለመለት አላማ መዋሉን እና በአግባቡ መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል ፡፡
  • በመ/ቤቱ ስም የሚገኙ የእርዳታና ብድር ገንዘቦች በሚደረጉ ስምምነቶችና የአሠራር ማንዋሎች መሠረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመተባበር በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡
  • መ/ቤቱ የሚሰበስባቸውን ልዩ ልዩ ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውንና ለሚመለከተው አካል ፈሰስ መሆናቸውን ይከታተላል ፣አረጋግጦ ያፀድቃል፡፡
  • የተለያዩ የመንግስት ግብርና ታክስ እና ሌሎች በተከፋይ የሚቀነሱ ሂሳቦችን  ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ገቢ መደረጋቸውን ይከታተላል፡፡
  • ተቀናናሽና ተከፋይ ሂሳቦችን በወቅቱ ለሚመለከታቸው አካላት መከፈላቸውን ይከታተላል፤ያረጋግጣል፡፡
  • የዕርዳታና የብድር ገቢዎች በወቅቱ መሰብሰባቸውን ይከታተላል፣ በድርጅቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጋቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፡፡
  • የፋይናንስ መግለጫ የሚያስፈልጋቸው የሂሣብ ምዝገባዎች መግለጫዎችን ፣ የሂሳብ ሚዛንና ትንታኔ እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፤ ያረጋግጣል ፡፡
  • የመ/ቤቱን የሂሳብ ሪፖርት በየወሩ እንዲዘጋጅ በማድረግ አጣርቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ያቀርባል፡፡
  • ሊሰበሰቡ የማይችሉ የተሰብሰቢ ሂሳቦች መረጃዎችን ኮሚቴ በማቌቌም ያስጠናል፣ በጥናቱ ውጤት መሰረት ለበላይ አካል ለውሰኔ ያቀርባል፣የውሰኔ ሃሳብ ሲደርሰውም ምዝገባ እንዲካሄድ ያስደርጋል
  • በተሰብሳቢና በተከፋይ ያልተሰበሰበ ገንዘብ መሰብሰብ እንዲቻል በእድሜ ዘመን በመተንተን ለክትትል አመቺ በማድረግ ሪፖርቱን ለሚመለከተው ክፍል ያቀርባል ፡፡
  • በቅድሚያ ክፍያ ወጪ ሆኖ የተከፈለው ገንዘብ በፋይናንስ መመሪያና ደንብ መሰረት ወቅቱን ጠብቆ እንዲወራረድ ያደርጋል፡፡
  • ጊዜያቸው ከአስር አመት በላይ የሆኑ የፋይናንስ ገቢና ወጪ ሰነዶች  በመመሪያው  መሰረት ኮሚቴ በማቌቌም ያስጠናል በጥናቱ ውጤት መሰረት ለበላይ አካል ለውሳኔ ያቀርባል፣የውሰኔ ሃሳብ ሲደርሰውም እንዲወገዱ አፈፃፀሙን ክትትል ያደርጋል፡፡
  • የሂሳብ እንቅስቃሴ ምዝገባ በፋናንስ አዋጅ፤ ደንብና መመሪያ መሰረት በአግባቡ መከናወኑን ይከታተላል ፣ ያረጋግጣል፡፡
  • በኦዲት ሪፖርት ግኝት መሠረትመርሃ ግብር በማዘጋጀት የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡
  • በውጭ ኦዲተር የተመረመረውን ሂሣብ ከተሰብሳቢ እና ተከፋይ ሂሳብ መግለጫዎች ጋር በማያያዝ ለሚመለከተው አካል እንዲላክ ያደርጋል፡፡
  • የመ/ቤቱ የዝውውር ሂሳብና የፈሰስ ሂሳብ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሂሳብ ጋር መታረቃቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • በመ/ቤቱ ስም የሚገኙ የእርዳታና ብድር ገንዘቦች በሚደረጉ ስምምነቶችና የአሠራር ማንዋሎች መሠረት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
  • በወርሃዊ የሂሣብ ሪፖርት መሠረት የሂሳብ መደቦች ሚዛን ከሂሣብ ምዝገባና ሪፖርት ማጠቃለያ ጋር በመናበብ የተፈጠሩ ልዩነቶች በወቅቱ ማስተካከያ እንዲዘጋጅ ያስደርጋል፡፡
  • ለኦዲት ምርመራ ቅድመ ዝግጅት ማድረግና በኦዲት ወቅት ለሚቀርቡ መጠይቆችና በሚታዩ ግኝቶች ላይ ምላሽ ይሰጣል፡፡
  • የተፈቀደ በጀትን መሠረት በማድረግ በአጠቃላይ ሌጀርና ተቀፅላ ሌጀሮች ምዝገባ መደረጉን ይቆጣጠራል፡፡
  • ሰራተኞች ከአዳዲስ ሲስተም ጋር ማስተዋወቅና ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ የተሻለ አቅም በመገንባት የስራ አፈፃጸማቸው እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡
  • የክፍሉ ባለሙያዎች ከሂሳብ ሪፖርትና የክፍያ አስተዳደር ዝግጅት ጋር በተገናኝ ወቅታዊ ከሆኑ የሂሳብ መርሆችና ህጎችን በማሰልጠን ብቁ ያደርጋል፡፡
  • የስልጠና ዓይነቶችን የክህሎት ችግሮችን በመለየትና በመተንተን ባለሙያዎች ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ እና የስልጠና ተቋሞችን ያፈላልጋል ፡፡
  • በቴክኖሎጂ የዘመነ የፋይናንስ አሰራሮችን በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ ስልጠና እነዲወስዱ ያደርጋል፡፡
  • በወርሃዊ የሂሣብ ሪፖርት መሠረት የሂሳብ መደቦች ሚዛን ከሂሣብ ምዝገባና ሪፖርት ማጠቃለያ ጋር በመናበብ የተፈጠሩ ልዩነቶች በወቅቱ ማስተካከያ እንዲዘጋጅ ያስደርጋል፡፡
  • ለኦዲት ምርመራ ቅድመ ዝግጅት ማድረግና በኦዲት ወቅት ለሚቀርቡ መጠይቆችና በሚታዩ ግኝቶች ላይ ምላሽ ይሰጣል፡፡
  • የተፈቀደ በጀትን መሠረት በማድረግ በአጠቃላይ ሌጀርና ተቀፅላ ሌጀሮች ምዝገባ መደረጉን ይቆጣጠራል፡፡
  • ሰራተኞች ከአዳዲስ ሲስተም ጋር ማስተዋወቅና ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ የተሻለ አቅም በመገንባት የስራ አፈፃጸማቸው እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡
  • የክፍሉ ባለሙያዎች ከሂሳብ ሪፖርትና የክፍያ አስተዳደር ዝግጅት ጋር በተገናኝ ወቅታዊ ከሆኑ የሂሳብ መርሆችና ህጎችን በማሰልጠን ብቁ ያደርጋል፡፡
  • የስልጠና ዓይነቶችን የክህሎት ችግሮችን በመለየትና በመተንተን ባለሙያዎች ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ እና የስልጠና ተቋሞችን ያፈላልጋል ፡፡
  • በቴክኖሎጂ የዘመነ የፋይናንስ አሰራሮችን በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ ስልጠና እነዲወስዱ ያደርጋል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.