የመኖ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የመኖ ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-

  • በአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ችግር ላይ የተመሠረተ የሀገሪቱን የእንስሳት መኖ ለማልማት የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፤
  • ለእንስሳት ሀብት ልማት አስፈላጊ የሆኑ የውኃ፤የመኖ ባንኮች፣ የተፈጥሮና የመስኖ ግጦሽ ልማት እና አጠቃቀም የሚስፋፉበትን፣ ቀጣይነት ያለው ጥቅም የሚሰጡበትን የአሠራርና ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነድፋል፤
  • የእንስሳት መኖ ቴክኖሎጂዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ያጠናቅራል፣ለየሥነ- ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የሚያሰራጭበትን ስልት ይነድፋል፡፡
  • ለእንስሳት መኖ ልማትና አጠቃቀም፣ ውጤታማና ቀጣይነት የሚረዱ  ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ያመነጫል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያድረጋል፣
  • በአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ችግር ላይ የተመሠረተ የሀገሪቱን የእንስሳት መኖ ለማልማት የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃዉ የአፈጻጸሙን ሂደት ይከታተላል፣
  • በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ለእንስሳት ሀብት ልማት አስፈላጊ የሆኑ የውኃ፤የመኖ ባንኮች፣ የተፈጥሮና የመስኖ ግጦሽ ልማት እና አጠቃቀም የሚስፋፉበትን፣ ቀጣይነት ያለው ጥቅም የሚሰጡበትን የአሠራርና የአስተዳደር ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነድፋል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊቱን ይከታተላል፣ ሀገራዊ መረጃ ያደራጃል፣ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • አዳዲስ ሀገር አቀፍ የመኖ ልማት ኘሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን ይቀርጻል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃዉ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ቴክኒካዊ ዕገዛ ይሰጣል፣
  • ለሀገሪቱ የመኖ ልማትና የማምረቻ ኢንዱስትሪ ማነቆ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፖሊሲ ችግሮችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በዳሰሳ ጥናት በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱንና ዉጤቱን ይገመግማል፣ግብረ መልስ ያስጣል፣
  • የእንስሳት መኖ ቴክኖሎጂዎችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ለየሥነ-ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በመቅረፅና የአሰራር ስልት በመንደፍ ለባለሙያዎች/ለተጠቃሚዎችስልጠና በመስጠት ያስተዋውቃል፣ሙያዊ  ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የሴቶች እና የወጣቶች ልማት በተለያዩ የእንስሳት መኖ ልማት  አማራጭ  ቴክኖሎጂዎችን መሰረት በማድረግ የሚደረጁበትን የአሰራር ስልትና ስትራቴጂ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ያጠናል፣ ሲፀድቅም ተግባር ላይ እንዲዉሉ ለክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የስልጠና፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣
  • የመኖ ልማት ስትራቴጂዎችና  ፕሮግራሞች  ከአሬንጓዴ  ኢኮኖሚ  ልማትና  የአየር  ለዉጥ መቋቋሚያ ስትራቴጂ ሥራዎች ጋር በማጣጣም እንዲካሄድና የተፈጥሮ ሀብቱን  ለመጠበቅ የሚያስችል ተስማሚነት ያለው አሠራር እንዲፈጠር አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመሆን

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.