የግብዓት አቅርቦት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የግብዓት አቅርቦት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለግብርና ኢንቨስትመንትና ግብይት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤

  • የግብዓት አቅርቦት ስርዓት ክትትል በማድረግ እና ግብይት ስርዓት ፖሊሲዎችንና ፕሮግራሞችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ይቀርጻል፣ውሳኔ ሲያገኝ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • የግብዓት አቅርቦቱ ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ በመጠን፣ በጥራትና በዓይነት ተደራሽ እንዲሆን ጥናት ያደርጋል፤
  • ከአገር ውጭ እና በአገር  ውስጥ  በግዥ  የሚቀርቡ  ግብዓት  እና  ስርጭት  ተግባር  ላይ  የተሳተፉ እና ለመሳተፍ የሚፈልጉ አካላትን የአቅም ግንባታ ስራ ይሰራል፤
  • ጥራትና ደረጃው የተጠበቀ ግብዓት ለአርሶና አርብቶ አደሩ፣ ለባለሀብቶችና የተደራጁ የማህበረሰብ አካላት እየቀረበ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ይከታተላል ችግር ያለባቸውን በመለየት  ለበለጠ  ሙያዊ ጥራት ቁጥጥር ለሚመለከታቸው ላቦራቶሪ እንዲያሳወቁ ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • የግብዓት አመራረት፣ ክምችት፣ የአጓጓዝ ሂደት በሥርዓት እንዲመራ የአሰራር ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል ፡፡
  • ከምርምር ማዕከላትና ከግብዓት አቅራቢ ማዕከላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ተፈላጊ የስነ- ህይወታዊ ግብዓት ምርት ግብዓት ውጤታማ የሆኑ በምርምርና በጥናት እንዲቀርቡ በቅንጅት ይሰራል ፣
  • ለምርምር በሚቀርቡ ሃሣቦች/ የምርምር ኘሮፖዛሎች/ ላይ በሚደረግ ውይይት በመሳተፍ የበኩሉን አስተያየት ያቀርባል፣
  • የግብዓት ጋር የተገናኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ያዘጋጃል፣ ያፀድቃል፣ አተገባበራቸውንም በመከታተል ሪፖርት ያቀርባል፣
  • በግዥ የሚቀርቡ ግብዓቶች ፍላጎት ትንበያ፣ እና ስርጭት ዙሪያ ለአቅራቢዎች እና ተጠቃሚዎች ምቹ እንዲሆን አዳዲስ የአሰራር ሥርዓት ስለሚሻሻልበት ሁኔታ ሀሳቦችን ያቀርባል፤ይዘረጋል፡፡
  • በግብዓት ሥርጭት ዙሪያ ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
  • ቅንጅታዊ አሠራር ለማጎልበትና ለማጠናከር የሚያስችሉ ስልቶችን  በመቀየስ  በወቅቱ  ግብዓት ለአርሶ አደሩ/አርብቶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤
  • ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችና ልማታዊ ባለሀብቶች በግዥ የሚቀርቡ ግብዓቶች ና ሥርጭት ላይ እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
  • ግብዓቶች ተገዝተው ከመቅረባቸው በፊት ተገልጋዮች ዝግጅት እንዲሁም የቅበላ አቅም በመገምገም ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የዝግጅት ክፍተት ሲኖር የማሟያ  ስልት ይነድፋል፣
  • በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የግብርና ግብዓት እና ስርጭት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ የውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰባሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ደርጋል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.