የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ

በሚኒስቴር ዴኤታ የሚመራ የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለአርብቶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በሰብል ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ልማትን የሚያፋጥኑና ከየግብርና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ደርጋል፣ ይመራል፤
  • ሀገራዊ የዕፀዋት ዘረመል ሀብት እንዲለይ፣ እንዲመረጥ፣ እንዲሻሻል፣ ጥቅም ላይ እንዲውልና እንዲጠበቅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ከምርምር፣ ከዩንቨርሲቲዎችና ከብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር ይሠራል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት የሚያሻሻሉ የምርምር ሥራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ሲፀድቅም እንዲተገበር ያደርጋል፣ ይመራል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤
  • ስነ-ምህዳርና ከባቢ አየርን መሠረት ያደረጉ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በሰብል አመራረት ስርዓቱ ውሰጥ ውጤታማነትና ዘላቂ ልማት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣ በዘርፋ የሚሰሩ አካላትንም ይደግፋል፣
  • የመነሻ ዘር ብዜትን ያስተባብራል፣ ስርዓቶችን ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፣ እንዲሁም የዘር ብዜት ሥራ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኝ ያደርጋል፣
  • የአየር ንብረት መረጃን መሠረት ያደረገ የሰብል ልማት ምክረ ሀሳብ  በዘመናዊና  ተደራሽ  በሆነ መልኩ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤
  • የምርት ብክነትን ለመቀነስ እና የምርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ይለያል፣ የምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ይደግፋል፣ ለአርሶ አደሩና ለግል ባለሀብቱ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፤

 

  • የመደበኛ ተባዮች ጉዳትን ለመቀነስ የሚረዱ ከዘር ጀምሮ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ ተደራሽ ያደርጋል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች ይለያል፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ የስልጠና ማዕከላት የልህቀት ተቋማት እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ ይመራል፤
  • ለእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ምርታማነትና ዕድገት ዘለቄታዊ ልማት አጋዥ  የሆኑ ስትራቴጂዎችንና አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማዘጋጀት የሀብት ምደባ በማመቻቸት የቁጥጥርና ክትትል ድጋፎችን በማድረግ የግብርናን ይመራል፤
  • ለዕቅድና ለውሳኔ አሰጣጥ ድርሻ ያላቸውን የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ መረጃዎች ከባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን ሊያሳኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን፣ፓኬጆችንና አሰራሮችን ይለያል፣ ይመርጣል፣ ቴክኖሎጂዎችና የመፍትሄ ሀሳቦች በኤክስቴንሽን ስርዓቱ እንዲስፋፉ ይመራል፣ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.