የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ

የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስትሩ  ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

  • የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፤ለአርብቶ አደሩ፤ለግል ባለሀብቱና በእንስሳት ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
  • የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማትን የሚያፋጥን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ደርጋል፣ ይመራል፤
  • ሀገራዊ የእንስሳት ዘረመል ሀብት እንዲለይ፤እንዲመረጥ፤እንዲሻሻል፤ጥቅም ላይ እንዲውልና እንዲጠበቅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይመራል፣ ይከታተላል፤
  • የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ምርምሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ሲፀድቅም እንዲተገበር ያደርጋል፣ ይመራል፤
  • የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት እና የአየር ንብረት ለዉጥ መቋቋሚያ አሬንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት  እንዲዘረጋ  ያደርጋል፣  ተግባራዊነቱን  ይከታታላል፣ ይመራል፤
  • የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ የስልጠና ማዕከላት/የልህቀት ተቋማትን እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ ይመራል፤
  • ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ኢንቨስትመንት የሚውል የመሬት አቅርቦት  እንዲኖር፤  አጋዥ የሆኑ የፋይናንስ፤የመድን ዋስትና እንዲሁም የብድር አቅርቦት ሥርዓት እንዲጎለብት አግባብ ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራል፤
  • የተፈጥሮ ግጦሽና በመስኖ የሚካሄድ የመኖ ልማት፣ የደረቅና ዕርጥብ መኖ ባንኮችን ያስፋፋል፣ የሚገኘውን ጠቀሜታ ይገመግማል፣ግብረመልስ ይሰጣል፣
  • የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ተገቢውን የጤና አገልግሎት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፣ መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ኤክስቴንሽን ለአርቢው እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  • በየግብርና ለሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠሩ ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይመራል፤
  • ለእንስሳት ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱትን የእንስሳት ዝርያና የመኖ ዕፅዋት ዘር ብዜትና ሥርጭት ተቋማትን የማቋቋሚያ ሐሳብ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ይተገብራል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.