የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ

በሚኒስቴር ዴኤታ የሚመራ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

  • የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነትና ውጤታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለአርብቶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ለተሰማሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
  • የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነትና ውጤታማነት የሚያፋጥን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ያደርጋል፤
  • ሀገራዊ ለአነስተኛ አርሶ እና አርብቶ አደር መስኖ ልማት የሚውል የውሃ ሀብት እንዲለይና ጥቅም ላይ እንዲውል ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይመራል፣ ይከታተላል፤
  • ሀገራዊ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፣ የተፋሰስና አግሮ ፎረስትሪ፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ የተሻሻሉ ዘመናዊ አሠራሮች ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይመራል፣ ይከታተላል፤
  • የተፈጥሮ ሀብት ልማት ምርምሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበት ስርዓት ይዘረጋል፣ ሲፀድቁም እንዲተገበሩ ያደርጋል፤
  • የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤
  • የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፤
  • የደን ልማት፣ ጥበቃ እና አጠቃቀም እንዲሁም ለደን ምርምር ሥራዎች ትኩረት በመስጠት የሀገሪቱን ከፍተኛ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ ሁኔታ የተቀናጀ የደን ልማት፣ የቁጥጥር፣ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ያስተባብራል፤
  • የአገሪቱን የብዝሀ ሕይወት ሀብቶች በአግባቡ እንዲያዙ፣ እንዲጠበቁና የህብረተሰብ ጥቅም ተጋሪነት እንዲሰርጽ ይከታተላል፣የቅርብ አመራር ይሰጣል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.