የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ

የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ  አስፈጻሚ  ሆኖ የመንግሥት ሠራተኞችን አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ በመከተል የሚከተሉትን አብይ እና ቁልፍ ተግባራት ያከናውናል፡፡

  • የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ኃይል ልማት የሚመራ ገዢ ስትራቲጂና ዝርዝር ዐቅዶች እንዲዘጋጁና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
  • ከስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር  የሚመለከቱ  ፖሊሲዎች፣  መመሪያዎች፣ የስራ ሂደቶች፣ ማዕቀፎችን እንዳግባቡ ተዋደው / ተቀርጸው ተግባራዊ እንዲሆኑ ይመራል ይቆጣጠራል፤
  • በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሀብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፤
  • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ልዩ  ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፤
  • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወጥና ዘመናዊ የአፈጻጸም ምዘና ግምገማና ማሻሻል ስርዓት እንዲኖረው የሚያስችል የአፈጻጸም ምዘናና አመራር ስርዓት እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ኃይል ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የሰው ኃይል ልማት ፡ ስልጠናና ትምህርት ዕቅድና መርሃ ግብር እንዲዘጋጅና እንዲተገበር ያደርጋል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የአመራር ብቃትና ዝግጅት ለማሳደግ የሚያስችል የተከታይ ማፍራትና የሞያ ዕድገት ስትራቴጂ፣ ዕቅድና ስርዓት ዝግጅትና ትግበራ በበላይነት ይመራል ያስተባብራል ይቆጣጠራል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ኃይል ልማት አገልግሎት አሰጣጥ ለማላቅ የሚያስችል የክዋኔ ትዕምርትና (operating model); የስራ ሂደት የቲክኖሎጂና የመረጃ ስርዓት ግንባታና ትግበራን ይመራል፤
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አደረጃጀትና ተቋማዊ ዕድገት ብሎም ባህል በሚፈለገው አቅጣጫ ለማጎልበት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የተቋማዊ አቅም ግንባታ ማዕቀፍ፣ ስልትና ዕቅድ እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፤
  • ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
  • ከፍተኛ አደረጃጀት ያለው ተቋም ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን እንዲከናወኑ ያደርጋል፤
  • ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሀብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የተጠኑትን ይገመግማል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
  • የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል።

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.