የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ሥራ አስፈጻሚ

የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስትር ጽ/ቤት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የክፍሉን ስራዎች በማቀድና በመምራት፤የስነ ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል፣ የሙስና ሥጋት ተጋላጭነት ጥናት፣ የኦንላይን የሀብት ማሳወቅያና ምዝገባ ፣ የጥቅም ግጭት መከላከል ስርዓቶች ተግባራዊ በማድረግ፣ የሙሰና መረጃ የማመንጫት ሥርዓት በመዘርጋት፣ የጠቋሚዎች የከላላ ሰርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግና በመከታተል በተቋሙ ሥነምግባር እንዲሰፍን በማድረግ እና ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ይከላከላል፡፡
  • የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ያቅዳል፤ ያስተበባብራል፤ ሥራውን በበላይነት ይመራል፣ ያደራጃል፤ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
  • ለሥራው የሚያስፈልገው በጀት፣የሰው ኃይል እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እንዲሟሉ በማድረግና የተመደበ ሀብት ለታለመላቸው ዓላማ በአግባቡ እንዲውሉ ክትትል ያደርጋል፤
  • ለሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች በተመደቡበት የሥራ መዘርዝር መሠረት የሥራ ክንውኖችን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊውን ማስተካከያ ያደርጋል፤
  • ዳይሬክቶሬቱን ውጤታማ ለማድረግ የተቀየሱ አሰራሮች በተገቢው  መንገድ  ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፤ተቋሙን  በመወከል  በተለያዩ  ጉዳዮች  ላይ  ውይይቶችና  ስብሳበዎች ላይ ማብራሪያ እና መረጃዎች ይሰጣል፤
  • ከሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚሰጡ አዳዲስ አቅጣጫዎችን፣ ወቅታዊና ተለዋጭ ሁኔታዎችን እና አሠራሮችን ተቀብሎ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች ግልጽ የማድረግና ከኮሚሽኑ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲተገበር ያደርጋል፤
  • የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድና አፈፃፀም ሪፖርት ከባለሙያዎች ጋር በየጊዜው ይገመግማል፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ይለያል፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
  • የአፈፃፀም ሪፖርት ለኮሚሽኑ እና በግልባጭ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፣  የፅሑፍ  ግብረ መልስ ይቀበላል፣ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • ለተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች የስልጠና ፍላጎት እና የስልጠና ርእሶች በዳሰሳ  ጥናት እንዲለዩ ያስተባብራል፤
  • የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን ተሞክሮዎች በመቀመር የማሰልጠኛ ሰነዶች እና መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ በተቋሙ ሠራተኞች ያስተቻል፤ ሥራ ላይ እንዲውል ክትትል ያደርጋል፣
  • የስልጠና መረጃዎች ተደራጅቶ እንዲያዙ ያደርጋል፤ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፤
  • የስልጠና ስትራቴጂና ፕሮግራም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በጀት  ያስመድባል፤  ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • በሥነምግባር ስልጠና የገኘውን የስነ ምግባር ምጣኔ ደረጃ ይለካል፣ ለኮሚሽኑ እና ለተቋሙ ያሣውቃል፤
  • በኮሚሽኑ የተዘረጋውን የስልጠና ምዘና፣  የሥነምግባር  ተደራሽነት  እና  የጥራት  ማረጋገጫ ስርዓት (Ethics and Integrty Framework) ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.