የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሥራ

የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብይት ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና እና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

  • የግብርና ኢንቨስትመንት ፈጣን ዕድገትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የፖሊሲ ሀሳቦች፣ ስትራተጂዎችና ማስፈጸሚያ ስልቶችን ያመነጫል፤
  • ከክልሎች ጋር በመተባበር ለግብርና ኢንቨስትመንት በጥናት የተለዩ መሬቶችን መረጃዎችን በማሰባሰብ ያደራጃል፣ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፤
  • ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለግብርና ኢንቨስትመንት የተዘጋጀውን መሬት አስፈላጊውን የተስማሚነት መስፈርት ላሟሉ ባለሃብቶች መሬት እንዲያገኙ ያመቻቻል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብይት የአቅም ግንባታ  ስትራቴጂ  በማዘጋጀት  ይተገብራል፣ የክህሎት ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል አጫጭርና መካከለኛ ስልጠናዎች ያመቻቻል፤
  • የግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በኮንትራት እርሻ አሰራር የአካባቢው አርሶና አርብቶ አደሮች ጋር እንዲተሳሰሩ የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • ለግብርና ኢንቨስትመንትና ግብይት የሚያስፈልጉ የመሰረተ ልማት  እና  ሌሎች  ግብአቶች አቅርቦት በወቅቱና በተፈለገው መጠንና ጥራት እንዲቀርብ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
  • ከክልሎች ጋር በመቀናጀት የግብርና ኢንቨስትመንት መሬቶች  አጠቃቀምና  ቢዝነስ  ፕላን አተገባበር በተገባው ውል መሠረት ክትትልና የሙያ ምክርና ድጋፍ ይሰጣል፣
  • ከክልሎች ጋር በመተባበር በከተማ ግብር እና ኮመርሻል እርሻዎች ኢንቨስትመንት የወጣቶችን ተሳትፎ በማሳደግ እንዲቻል የሥራ መስኮች በጥናት መለየትና ወደ ከተማና ግብርና ኢንቨስትመንት የሚገቡበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • የግብርና ኢንቨስትመንት የምርት ማሰባሰብ አሰራር በማጥናትና የሌሎች አገሮች ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር አስፈላጊውን ድጋፍ በማመቻቸት አገልግሎቱ እንዲሻሻል ያደርጋል፣የተቀመረውን ተደራሽ ያደርጋል፤
  • ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የግብርና ኢንቨስትመንት ምርቶች በተለይም የኤክስፖርት ምርቶች በዋጋና  በጥራት  ተወዳዳሪነታቸውን  ለማረጋገጥ  በተሻለ  አመራረት፣ ምርት እንክብካቤ፣ ጥራትና መጠን እንዲመረት ያደርጋል፤
  • የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ የአዋጭ አማራጭና ውጤታማ ፓኬጆች እንዲዘጋጁ በማድረግ ለአገልግሎት ተጠቃሚዎች እንዲደርስ ያደርጋል፤
  • የግብርና ኢንቨስትመንት ግብይት ማነቆዎች እና መልካም አጋጣሚዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ጥናት ያጠናል፣ ይተነትናል የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፤
  • በክትትልና ድጋፍ ዳሰሳ ጥናት ወቅት የተደረጉትን ጥናቶች መሰረት በማድረግ በአመራረት፣ በምርት ጥራት እና በሌሎች ልማት ሥራዎች የሚታዩ ክፍተቶች ከምርምር ተቋማት የሚገኙ የምርምር ስራዎችን በማካተት ፓኬጅና ማኑዋል እንዲዲዘጋጅ እና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱ ጥናቶች እንዲካሄዱ በማድረግ፣ አቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሰጡ በማመቻችት፣ ክትትል፣ ድጋፍና የምክር አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ፣ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን እንዲለዩ በማድረግ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ያደርጋል፤
  • በግብርና ኢንቨስትመንት ምርት ግብይት የተሰማሩ ባለሀብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ቋሚ የምክክር መድረክ/ፎረም በማዘጋጀት በጋራ ለልማቱ እድገት  የሚያግዙ የውሳኔ ሀሳቦች በመውሰድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • የግብርና ኢንቨስትመንትን እና የግብርና ምርት ውልን ማስፋት የሚያስችል ሃገራዊ የመረጃ ሥርዓት እንዲዘረጋ ማመቻቸት፤ የግብርና ኢንስትመንትና የግብርና ውልን አንዲስፋፋ የሚረዱ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ህጎች እንዲነደፉ ማስተባበር፤ የግብርና ኢንስትመንትና የግብርና ምርት ውል እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች እንዲቀረጹ ማስተባበር፤ ሀገርዊና አለማቀፋዊ ምጥ ተሞክሮች እንዲቀመርና እንዲስፋፋ በማመቻቸት፤ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር እና ግንኙነት መረብ በመዘርጋት፤
  • ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት የተመለከቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ያስፋፋል፤ አምራቾች በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒቶች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በየግብርና እሴት ሰንሰለት የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናት ውጤቶች ሥራ  ላይ የሚውሉበትን ስልቶችና አሠራሮችን ያዘጋጃል፤
  • በግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ወደ ልማት የገቡ መሬቶች፣  የምርት  እንዲሁም ተያያዥ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና  ለተጠቃሚዎች  የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ተከታትሎ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣  የህግ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት ይከታተላል፣ የአካባቢው ኅብረተሰብ እሴቶችና ባህሎች ተጠብቀው እንዲፈፀም ያደርጋል፤
  • የተገልጋይ እርካታ ማረጋገጫ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ በቢሮና በመስክ የተሰጡ አገልግሎች እርካታ  ማሰበሰቢያ  ቼክሊስት  ያዘጋጃል፣  እርካታውን  ይለካል፣  ግብረ  መለስ  ይሰጣል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.