የአነስተኛ መስኖ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ለተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተጠሪ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

  • የአነስተኛ መስኖ ልማትንና የአነስተኛ መስኖ አውታሮች አስተዳደርና ውሃ አጠቃቀም ብቃት ለማሳደግና ለማጠናከር ፖሊሲዎችና መመሪያዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ፣ አዳዲስ የፖሊሲ ማሰፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን ማመንጨት፣ ሲፈቀዱም ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • የማህበራዊ ምጣኔና የዘላቂ አካባቢያዊ ልማትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ የመስኖ ውሃ መገኛ አካላትንና አማራጮችን ማጥናትና መረጃዎችን በተጠናከረ መልኩ ማደራጀት፣ መመርመርና መተንተን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አፈጻፀማቸውን መከታተልና ሪፖርት ማድረግ፤
  • በሃገር አቀፍ ደረጃ እየለማ ያለውን የመስኖ መሬት መጠን የመረጃ ክፍተት ተዓማኒ በሆነ መልኩ በዘለቄታዊነት ያለውን የመሬት መጠንና የውሃ ማልማት አቅም ጅኦ-ሪፈረንስና ሪሞት ሴንሲንግ ተክኖሎጂ በመታገዝ መረጃን በመያዝና በመተንተን በመስኖ በይነ መረብ የመረጃ ስርዓት ውስጥ ማደራጀት፤
  • ብቃት ያለው የአነስተኛ  መስኖ  አውታሮች  አስተዳደርና  ውሃ  አጠቃቀም  ሥርዓት  ለማስፈን
  • የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት እንዲስፋፋ የፖሊሲና ስትራቴጂ አቅጣጫዎችን መንደፍ፣ ሲፈቀዱም ከክልሎች ጋር በቅንጅት ተግባራዊ ማድረግና አፈፃፀማቸውን መከታተል፣
  • የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት አውታሮች ቅድመ  ግንባታ  (ጥናትና  ዲዛይን)፣በግንባታ  ወቅትና ድህር ግንባታ የመስኖ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ሚና ድርሻና ሃላፊነትን በመለየት፤የመስኖ ልማት ፈንድ ምንጮችን በመለየት መተግበሪያ መመሪያና አሰራር ስርዓት መዘርጋት፤
  • ከተቋሙ ራዕይና ተልዕኮ በመነሳት የሥራ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
  • የሥራ ሂደቶች ቅንጅትና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለዉ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
  • ከሥራ ዕቅዱ በመነሳት ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበዉ በጀት በትክክል ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.