ግብርና ሜካናይዜሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የግብርና ሜካናይዜሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለግብርና ኢንቨስትመንትና ግብይት ዘርፍ ሚኒስቴር  ዴኤታ      ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤

  • ተገቢ የግብርና ሜካናይዜሽን ምንጮችን የግዥ ስልት፣ እቅድ ፣ፖሊሲ፣ አሰራርና ፣ መመረያዎችን መፈተሽና ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
  • የግብርና ሜካናይዜሽን ከጠቅላላው የግብዓት ስልት አንጻር በመቅረጽ ይመራል፤
  • ግዥ፣ ማከማቸትና ማሰራጨት የሥራ እንቅስቃሴዎች የጥራትና ብቃት፣ የዋጋ ተወዳዳሪነት እንዲሁም የላቀ አገልግሎት ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች ከመስጠት አንጻር ያለውን እንቅስቃሴ በመፈተሽ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  • የተፋሰስ ልማት በሚካሄድበት አከባቢ የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃና ችግሮችን ለመፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መነሻ የሚሆኑ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ ይለያል፤
  • የሜካናይዜሽን ግብዓት መረጃዎችን የማደራጀት፣ ለዘመናዊ መረጃ ቋትና ፣ለዕቅድ ዝግጀት ያመቻቻል፤
  • የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራ በአከባቢው ያለበትን ደረጃና የህበረተሰቡን ልማዳዊ አሠራር በመለየት የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ትንታኔ መስጠት፣ በአግባቡ ያደራጃል፤
  • በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት  ሥራዎች  ጋር  በተቀናጀ መልኩ የሜካናይዜሽን ግብዓት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ ውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰብሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ያደርጋል፤
  • የሜካናይዜሽን ግብዓት በተመለከተ ለሚዘጋጁ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መረጃዎችን ያሰባስባል፤
  • የግብርና ሜካናይዜሽን ግብዓት በሚመለከት በተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ መሰረት ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ይሰጣል፤
  • በተፋሰስ ልማት የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራዎች ለማስፋፋት የተቀመሩ አዳዲሰና የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችና መመሪያዎችን ማሰራጨት፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • በተፋሰስ ልማት ተግባራዊ የሚደረጉ የሜካናይዜሽን ግብዓት ሥራዎች በተዘጋጀው ዕቅድና መመሪያ መሰረት እንዲከናውኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ይከታተላል፤
  • የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የሜካናይዜሽን ግብዓት በተዘጋጀው የአሰራር ማኑዋል መሠረት እንዲተገበሩ ድጋፍ ማድረግ፣ መከናወናቸውንም ውጤታማነታቸውን በመከታተል ሪፖርት ያደርጋል፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.