የግብርና ሥራ ዕድል ፈጠራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የግብርና ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የከተማ ግብርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ያከናውናል፡-

 • የግብርና ዘርፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የከተማ ግብርና ልማት እንዲስፋፋ የሚያስችሉ የፖሊሲ ሀሳብ ያመነጫል፣ ስትራቴጂ፣ መመሪያዎችና ማንዋሎችን ያዘጋጃል፤
 • በግብርና ዘርፍ  የሥራ  ዕድል  ለመፍጠርና  ለከተማ  ግብርና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችል የአካባቢውን ዕምቅ ሀብት ጥናት እንዲካሄድ ያደርጋል፣
 • በግብርና ምርቶች  ላይ  ተጨማሪ  እሴት  የሚፈጥሩ  አማራጭ  የሥራ እድሎችን  ያጠናል፤ አዋጭነቱን በማረጋገጥ ፓኬጆችንና ብዝነስ ሞዴሎችን ቀርፆ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ያደርጋል፤
 • ወጣቱ ትውልድ ወደ ግብርና ልማት ሥራዎች እንዲሰማራ የአስተሳሰብ ግንባታ ስራዎችን ይሰራል፤
 • በግብርና ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸውን ሥራ ፈላጊ የህብረተሰብ ክፍሎችን  ፍላጎትን፣ ዝንባሌንና የአካባቢውን እምቅ ሃብት (potential) መሰረት ያደረገ በተለያየ አደረጃጀቶች ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ይደግፋል፣
 • በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው ሥራ ለሚፈልጉ ወንድና ሴት ወጣቶች ከሙያቸዉና ዝንባሌያቸዉ አንጻር አዋጭ የሆኑ  የሥራ  አማራጮችን  በመለየትና  በማጥናት  በግብርና  ዘርፍ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ያደርጋል፤
 • ከሚመለከታቸው የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና  ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በግብርና ዘርፍ ሥራ ለሚፈጠርላቸው ዜጎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፤
 • የአግሪ ቢዝነስ አሰተሳሰብ ለህብረተሰቡና ለሥራ ፈላጊዎች የተለያዩ መድረኮችን፤ ወርክ ሾፖችንና መገኛኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ግንዛቤ እንዲፈጠርላቸው ያደርጋል፤
 • በግብርና ዘርፍ በጥናት በተለዩ የሥራ አማራጮች እና  በከተማ  ግብርና  ልማት  የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ውጤታማ ለማድረግ የመስሪያና የመሸጫ ቦታ፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት፤ የብድርና የገበያ ድጋፎችን እንዲያገኙ ደርጋል፣
 • በግብርና ዘርፍ አዳዲስ የሥራ ፈጠራ ማስፈጸሚያ የሚውል ሃብት ማፈላለጊያ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፣ ድጋፍ ያደርጋል፣
 • ለግብርና ሥራ ዕድል ፈጠራ ተስማሚና አዋጭ የሆኑ እና የከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጅዎችን ይለያል፤ተደራሽ ያደርጋል፤
 • ለግብርና ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች የአግሪ ቢዝነስ ልማት አገልግሎት (BDS) ተደራሽ እንዲሆን ያስተባብራል፤
 • በግብርና ዘርፍ በተፈጠሩ የሥራ አማራጮች የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከምርታቸው ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የገበያ ጥናት ያካሄዳል፤ትስስር ይፈጥራል፤ ገበያ መር ምርቶች ላይ እዲሰማሩ ያደርጋል፣
 • በገጠር አካባቢዎች በግብርና ዘርፍ የተፈጠሩ የሥራ አማራጮች በከተሞች አከባቢ ከተቋቋሙ ወይም ከሚቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች ጋር በሚተሳሰሩበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፤
 • የተሻለ የግብርና ዘርፍ የሥራ ዕድል አፈጻጸም ካላቸው ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጦች እንዲካሄዱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በተጨማሪም በየተግባሩ የሚገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር በፌደራል ተቋማትና በክልሎች መካከል እንዲሰፋ ያደርጋል፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.