የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ

የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የመንግሥት ሠራተኞችን አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ በመከተል የሚከተሉትን አብይ እና ቁልፍ ተግባራት ያከናውናል፡፡

  • መሠረታዊ አገልግሎት አገልግሎት ሥራ በማቀድ፣ በማስተባበር፣ በመምራት፣ በተቋሙ የሚሰጡ የትራንሰፖርት፣ የቢሮ፣ የአደራሽና የምድረ ግቢ አገልግሎት እንዲሁም ለሚኒስቴር መ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥን በመደገፍና በመከታተል የተቋሙን ሥራ ውጤታማ ማድረግ ነው፤
  • ከተቋሙ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ የስራ ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ለቡድኖች ያከፋፍላል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤
  • የስራ ክፍሉ ሠራተኞች በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤ በምዘናው ውጤት መሠረትም ውጤታማ የሆኑ ሰራተኞችን እውቅና ይሰጣል፣ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላሳዩ ሰራተኞች የአቅም ክፍተታቸው እንዲሞላ ያደርጋል፤
  • ስራን የሚያሳልጡ አዳዲስ አሰራሮች የሚተዋወቁበት ስልጠና እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤ ስልጠናው ያመጣውን ውጤት ይከታተላል፤ ይገመግማል፤
  • ለስራ ክፍሉ አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ ግብዓቶች እና የሰው ኃይል እንዲሟላ ያደርጋል፤ ምቹ የሥራ ሁኔታዎች/conducive working environment / እንዲኖር ያደርጋል፤
  • የመ/ቤቱ የቋሚ ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ዘመናዊ የአሠራር ስርዓት የተከተለ መሆኑን ያረጋግጣል፤
  • የተቋሙ ንብረቶች በአግባቡ ለተፈቀደለት ዓላማ ጥቅም ላይ መዋሉና የሚያስረዱ የንብረት አጠቃቀም ሪፖርቶችና መግለጫዎች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤
  • የግብርና ቋሚ ንብረቶች ተገቢው ጥበቃ የተደረገ መሆኑና ረዥም ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የአሠራር ስርዓት አጥንቶ ያቀርባል ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የንብረት አጠቃቀምና አያያዝ የፈጻሚ ሠራተኞችና ተጠቃሚዎች ግንዛቤ እንዲዳብር ክትትል ያደርጋል፣ይደግፋል፣
  • የመስሪያ ቤቱን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡ የተለያዩ የአሠራር ዘዴዎችና ስልቶች እንዲቀየሱ ድጋፍ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
  • የተሸከርካሪዎች ጥገናና ሰርቪስ ወቅቱንና ጥራትን ጠብቆ እንዲፈፀም እንዲሁም በተሸከርካሪዎች ላይ ጉዳት ሲደርስም በአፋጣኝ ተሰርተው/ተጠግነው/ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  • የተሸከርካሪዎች አጠቃላይ መረጃ /profile/ በአግባቡ ተደራጅቶ መያዛቸውንና ወቅታዊ /update/ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
  • የተሸከርካሪ አቅርቦት ከፍላጎት ጋር የሚጣጣምበት አማራጭ ዘዴዎች እንዲቀየሱ ያደርጋል፣ አዳዲስ መኪናዎች ሲገኙም አስፈላጊው ፎርማሊቲ ተሟልቶላቸው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
  • የተቋሙ ቢሮዎችና አደራሾች አጠቃላይ መረጃ /profile/ በአግባቡ ተደራጅቶ መያዛቸውንና ወቅታዊ /update/ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
  • ለቢሮ፣ ለአደራሽና ለጊቢ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችና ግብዐቶች እንዲቀርቡ ማድረግና ለታለመላቸው አላማ መዋላቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፤
  • ለበላይ አመራሮች፣ ለሥራ ኃላፊዎችና ለሠራተኞች ቢሮዎች እንዲመቻቹ ያደርጋል፣ ይደግፋል፤
  • ለሥራ ምቹ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል አሠራር እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ይደግፋል፣
  • የቢሮና የአደራሽ  ጥገና  ፍላጎት  መረጃ  እንዲሰባሰብ፣  እንዲለይና  እንዲጠገን  ክትትልና  ድጋፍ  ያደርጋል፤
  • መብራት፣ ስልክ እና ውሀን በተመለከተ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ መከታተልና መደገፍ፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.