የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
  • የዘርፉን የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ሥራዎች በማቀድ፣ በማስተባበር፣ በመምራት፤ ለጥናት እና ምርምር የሚያግዙ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት፣ በማሻሻል፤ የዘርፉን ችግሮች ለመለየት የሚደረጉ የትንተና እና ትንበያ ስራዎችን፣ የፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ቀረፃ ሂደትን፣ የፖሊሲ  የክትትል  እና  ግምገማ  ሥራዎችን፤  የፖሊሲ  ጥናት እና ምርምር ሥራዎችንና የምርምር አጀንዳ እንዲቀረጽ በማድረግ፣በመከታተል፣በማስተባበር፣ በመገምገም፤ በዘርፉ የተዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጅዎች፣ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ውጤቶች በዘመናዊ ዳታ ቤዝ እንዲደራጁና እንዲተዋወቁ በማድረግና በማስተባበር፤ የአስቸኳይ ጊዜ አደጋዎች ምላሽ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች እቅድ እንዲዘጋጅ በማድረግና የዘርፈ ብዙ ምላሽ ትብብርን በማሻሻል ዘርፉ ያስቀመጣቸውን ግቦች ያሳካል፡፡
  • የዘርፉን ስትራቴጅክ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የሥራ ክፍሉን እቅድ ያዘጋጃል፣ ይመራል፣ ያከፋፍላል፤ ይከታተላል፣ይገመግማል፡፡
  • የሥራ ክፍሉን ሥራዎች ለማከናወን የሚያስፈልጉ የሰው ሀብት፣ የገንዘብና የማቴሪያል ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
  • የሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች የግል እቅድ እንዲያዘጋጁ ያግዛል፤ ይከታተላል፤ የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ይገመግማል፣ ለሥራ ክፍሉ የተነደፉ ግቦች በቅልጥፍናና በውጤታማነት ተተግብረው ለውጤት እንዲበቁ የባለሙያዎች የውጤት ተኮር ዕቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣አፈፃፀሙን በየወቅቱ ይገመግማል፣የሥራ አፈፃፀማቸውንም ይሞላል፣ ግብረመልስ ይሰጣል፣ ውጤታማ የሆኑ ሠራተኞችን ያበረታታል፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሠራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ የተለያየ ስልት በመንደፍ አቅማቸውን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የመገንባት ሥራን ያከናውናል፡፡
  • የሥራ ክፍሉን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በየወቅቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
  • የዘርፉን ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎችን ለማዘጋጀት የሚረዳ ስታንዳርድ  እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ የተዘጋጀውን ስታንዳርድ ይገመግማል፣ በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
  • በዘርፉ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለመለየት፣ የሚሰበሰቡ መረጃ እና ምርምር ውጤቶችን፣ ከተለያዩ የጥናት እና ምርምር ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች አቀናጅቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ሀገራዊ ስትራቴጂ ያዘጋጃል፣ ስትራቴጂው ሥራ ለይ እንዲውል ይደግፋል።
  • የፖሊሲ መረጃዎች እና የምርምር ዉጤቶችን ለተጠቃሚው የሚደርሱበትን ሥርዓት ይቀይሳል፡፡
  • በተለያዩ የዘርፍ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ እና የምርምር ተግባራት ላይ ከተለያዩ የምርምር፤ የአካዳሚክ፤ የሥራ ኃላፊዎች፤ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የፖሊሲ ምክክር (policy dialogue) መድረኮችን ውጤታማነት ይከታተላል፣ይገመግማል፡፡
  • የባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ያላቸዉን ፍላጎት እና ተጽዕኖ ለመለየት የባላድርሻ አካላት ትንተና ተግባራትን ያስተባብራል፡፡
  • የአስቸኳይ ጊዜ አደጋዎች ሲከሰቱ ቀልጣፋ ምላሽ የሚሰጥበትን የአሰራር ሥርዓት እንዲቀየስ ያደርጋል፣ ሥራ ለይ እንዲውሉ ያስተባብራል፡፡
  • የዘርፉን ዒላማዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና፣ እቅዶች ከአለም አቀፋዊንና አህጉራዊ አጀንዳዎች የሚናበቡትን ስርዓት ይቀይሳል፣ ዒላማዎቹ መካተታቸውን ያረጋግጣል።
  • የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በጥራትና በመስፈርቶች (Research quality standards) መሰረት መከናወናቸውን ከትትል ያደርጋል፣ በአፈፃፀም ለሚታዩ ጉድለቶች ማስተካከያ ይሰጣል፡
  • ከሌሎች ተመሳሳይ ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ ተቋማት ጋር የጥናትና ምርምር ትብብር የሚፈጠርበትን ስርዓት ይዘረጋል፣ ማሻሻያዎችን ያደርጋል፡፡
  • መልካም ተሞክሮ የሚቀመርበትን የምርምር አጀንዳ ፣አሰራር እና መሳሪያዎችን ይለያል፣ ያበለጽጋል፣ ያዘጋጃል፣ያሻሽላል፡፡
  • መልካም ተሞክሮ የሚገኝባቸው ሀገራት እና ተቋማት እንዲለዩ ያደርጋል፣
  • ለፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት የሚያግዙ አገር አቀፍና ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎች እንዲቀመሩ ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
  • በፖሊሲና ስትራቴጅ ዙሪያ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ከሀገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ይተነትናል፣ሪፖርት ያቀርባል፡፡
  • ተለይተው በታወቁ ዓለምአቀፋዊ እና ሀገራዊ የጥናትና የምርምር ተቋማት፤ ከሚመለከታቸው አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል የግንኙነት ስትራቴጅ ይነድፋል፡፡
  • ለፖሊሲና ስትራቴጅ ዝግጅት የሚያገለግሉ የተለያዩ የጥናትና ምርምር በማድረግ የተለያዩ አዳዲስ የትንበያ ሞዴሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
  • የዘርፉን የረጅም ጊዜ መረጃዎችን በመጠቀም የረጅም ጊዜ ትንበያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሂደቱን ይመራል፡፡
  • የዘርፉን የረጅም አመታት መረጃዎች እና የጥናት ዉጤቶችን መሰረት በማድረግ የአዝማሚያ ትንተና (Trend analysis) እንዲካሄድ ያደርጋል፣ሂደቱንም ይመራል፡፡
  • የተለያዩ የሞዴሊንግ ሥራዎችን በመሥራት ለፖሊሲ፣ስትራቴጅ፣ጥናትና ምርምር የሚያገለግሉ የወደፊት ሁኔታዎች ትንበያ (scenarios) እንዲቀረፁ ያደርጋል፣ ያስተባብራል።
  • ፖሊሲና ስትራቴጅ ቀረጻ እና ትንተና የሚያስፈልጋቸዉን ጉዳዮች የስርዓት ጥናት እና ትንተና እንዲደረግባቸዉ ያደርጋል፣ ሂደቱን ይመራል፣ ያፀድቃል።
  • የመረጃዎች እና የጥናትና ምርምር ዉጤቶች በመተንተን ለፖሊሲ እና ስተራቴጂ ዝግጅትና ለውሳኔ አሰጣጥ ግብዓት እንዲውል ያደርጋል፣ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል።
  • ወቅታዊ እና አመላካች የሆኑ አጫጭር የፖሊሲ ሰነዶችን (policy briefs) በሴክተሩ ፍላጎት ላይ ተንተርሶ እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ የተዘጋጁትን  ይገመግማል፣  የፖሊሲ ዉሳኔ እንዲያገኙም ያደርጋል።
  • በዘርፉ ውስጥ ለሚታዩ ቁልፍ ችግሮች በጥናትና ምርምር ይለያል፣ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ የፖሊሲ አማራጮችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል።
  • የፖሊሲ አማራጭችን በሚያመጡት ውጤት፣ የኢኮኖሚ ፋይዳ፣ ለአፈፃፀም ባላቸው አመቺነት (feasibility) ተመስርቶ ቅደም ተከተል ያወጣል፣ የተሻሉትን እንዲመረጡ ሃስብ ያቀርባል፣ ያፀድቃል።
  • የዘርፉን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ዝግጅቱን ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ክለሳ የሚፈልጉ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች በዳሰሳ እንዲለዩና እንዲከለሱ ያደርጋል ፡፡
  • በዘርፉ ከሌሎች ሴክተሮች ድጋፍ ለሚፈልጉ ጉዳዮች በፖሊሲዎችና በስትራቴጂዎች እንዲያካትቱ ያደርጋል፣ ሂደቱንም ይከታተላል፣ ያስተባብራል።
  • በዘርፉ የተረቀቁ ፖሊሲዎች እንዲፀድቁ የአድቮኬሲ ሥራ ይሰራል፣ እንዲፀድቁ ይከታተላል።
  • በሥራ ላይ ያሉ እና የተዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ እና ስትራቴጂዎች፣ ውጤታማነትን ለመለካት ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፣ ያስተባብራል።
  • በፖሊሲና ስትራቴጅ ትግበራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ ይሰጣል።
  • በጥናትና ምርምሮች ውጤታማነት ላይ ክትትል እና ግምገማ ያደርጋል፣ በተገኙ ውጤቶች መሰረት የማሻሻያ ሃሳብ ያቀርባል፣ መፈጸማቸውን ይከታተላል።
  • ዘርፉን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች አፈጻጸም ትንተና በማድረግ ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
  • የፕሮግራሞችን አፈጻጸም ውጤታማነት ትንተና በማካሄድ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን ይለያል፣የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣
  • ለፖሊሲና ስትራቴጅ ማስፈፀሚያ የሚያገለግሉ የህግ ማእቀፎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ያስተባብራል፣ይገመግማል፡፡
  • የዘርፉን የረጅም ጊዜ የጥናት እና ምርምር አጀንዳዎችን የስርዓቱን ቁልፍ ችግሮች ላይ ተመስርቶ እንዲቀረፁ ያደርጋል፣ ያስተባብራል።
  • በዘርፉ ምርመር ስራዎችን ለማከናወን የሚረዱ ከፍተኛ የፕሮጀክት ሃሳቦችን ያመነጫል፣ ከፍተኛ ፕሮጀክቶችን በመዘጋጀትና ሀብት በማፈላለግ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡
  • የጥናትና ምርምር ሥራው የሚመራበትን ቴክኒካል የሥራ መመሪያና ማስፈፀሚያ (guide line) እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ማሻሻያዎችን ያደርጋል፡፡
  • የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ጥናት እና ምርምር ሥራዎች ለይ የሚሳተፉ አካላት የሴክተሩን የምርምር አጀንዳዎችን እንዲያውቁት ያደርጋል።
  • የጥናት እና ምርምር ሥራዎች እና ዉጤቶች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆናቸዉን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣ በተገኘው ውጤት መሰረት ግብረ  መልስ  ይሰጣል፣  የማሻሻያ  ሃሳቦቹ  ተግባር ላይ መዋላቸውን ይከታተላል።
  • በሴክተር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ያሉ የሪሰርች ካውንስሎች ሥራ የተናበበ እንዲሆን ይደግፋል።
  • በዘርፉ ፈፃሚ የፖሊሲ ዲያሎጎችን ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል።
  • የዘርፉን ፖሊሲና ስትራቴጅ ውጤታማ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ትኩረት ሊደረግባቸው እና ሊጠኑ የሚገባቸው የዘርፉ ፖሊሲ ጉዳዮች እንዲለዩ ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
  • በዘርፉ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሊደረግባቸው የሚገቡ መስኮች /Thematic Areas/ እንዲለዩ ያደርጋል፣ ችግር ፈች የሆኑ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር እንዲካሄድ ያደርጋል፣ያስተባብራል፣ይገመግማል፡፡
  • ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በተለዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲደረግበት ያደርጋል፤ ግብአቱን በማካተት ለዝክረ-ተግባር (concept note) ዝግጁ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
  • በተለዩ የምርምር አጀንዳዎች ላይ የምርምር concept note/proposal/project እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
  • በዘርፉ ችግር ፈች የሆኑ የፖሊሲ ጥናትና ምርምሮች እንዲካሄዱ ያደርጋል፤ በበላይነት ይመራል፣ይገመግማል፡፡
  • የሚዘጋጁ ጥናትና የምርምር ሥራዎች ሳይንሳዊ የምርምር ሂደቶችን ተከትሎ የተዘጋጁ መሆናቸውን ይገመግማል፣ያረጋግጣል፡፡
  • የጥናትና ምርምር ውጤትን መሰረት በማድረግ ረቂቅ የፖሊሲና ስትራቴጅ ሰነዶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
  • የፖሊሲ ሰነድ ይዘቶችን ይለያል፣ ፍሬምወርክ ይቀርፃል፣እንዲቀረፅ ያደርጋል፣ሂደቱን ይመራል፡፡
  •  
    የፖሊሲ አዘገጃጀት መስፈርትን ተከትሎ መነሻ የፖሊሲ ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ያስተባብራል፣ይገመግማል፡፡
  • የፖሊሲ ረቂቅ ሰነዱን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የመገምግሚያ ወርክሾፕ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ እንዲገመገምና ግብአት እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
  • በተለያዩ አካላት የተሰጡ ግብረ መልሶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተሻሻለ የፖሊሲ ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ እንዲጸድቅ ያደርጋል፣አፈጻፀሙን ይከታተላል፡፡
  • የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ትንበያዎችን አጠቃቀም በቴክኖሎጂ በመታገዝ የተለያዩ ሞዴሎችን በመጠቀም ተጨባጭ መረጃዎች ትንተና እንዲሰራ ያደርጋል፣ ያስተባብራል።
  • በአገር ላይ ወረርሽኝ፣ ድንገተኛ አደጋዎች፣ ጦርነት እና ሌሎች ከፍተኛ አገራዊ  ችግሮች ሲከሰቱ መንግስታዊ የሆኑ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ለጋሽ ድርጅቶችን  በማስተባበር የአስቸኳይ ግዜ አደጋ ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል።
  • የድንገተኛ አደጋዎች ሲከስቱ የዘርፉን ምላሽ እቅድ ዝግጅት ያስተባብራል፣ ሃብት ያፈላልጋል፣ ውጤቱን ይገመግማል፣ በየወቅቱ የእቅድ ማሻሻያ ያደርጋል።
  • በአደጋዎች ዙሪያ የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲጎለብት የሚያደርጉ ስትራቴጂዎች እንዲቀረፁ ያደርጋል፣ያስተባብራል።
  • የድንገተኛ አደጋ ተጎጅዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባራትን ያከናውናል፣ ያስተባበራል፡፡
  • የአደጋዎች የዘርፈ ብዙ ምላሽ አካል በመሆን አገራዊ ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ያስተባብራል።
  • የምላሽ እና የመልሶ ማቋቋም ተግባራትን ከዘላቂ የልማት ፕሮግራሞች ጋር የማስተሳሰር ሥራዎችን ይመራል፣ያስተባብራል።
  • በዘርፉ የፖሊሲና ስትራቴጅ ዙሪያ የተከናወኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶች፣ የተሰጡ ግብረ መልሶች፣ ሪፖርቶች፣ የመልካም ተሞክሮ ግኝቶች እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው መረጃዎች በዘመናዊ ዳታ ቤዝ ሲስተም (Database System) እንዲደራጅና ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
  • በዘርፉ ያሉ የፖሊሲ፣ ስትራቴጅና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች በትላልቅ መረጃዎች (Big Data) ለተጠቃሚዎች በሚያመች መልኩ እንዲዘጋጁና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ያረጋግጣል ፡፡
  • ለፖሊሲ አፈጻጸም  ግምገማ  ጥናት  የሚያስፈልጉ  መረጃዎች  እንዲሰበሰቡ፣እንዲደራጁና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ሂደቱንም ይከታተላል፡፡
  • በዘርፉ ያሉ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች በሚፈለገው መልኩ ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ መሆናቸውን ያረጋግጣል ።
  • የዘርፉ ፖሊሲ እና ስተራቴጂ ትንተና እና መረጃዎች ለውሳኔ መጠቀም የሚያስችል የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እንዲከናወኑ ያደርጋል፣ ያስተባብራል።
  • ለዘርፉ ፖሊሲና ስትራቴጂ ግብዓት የሚሆኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማቅረብ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
  • የተለያዩ የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም በዘርፉ የተከናወኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶች እንዲተዋወቁና ግብረ መልስ እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
  • በዘርፉ የፖሊሲና ስትራቴጅ አፈፃፀም ዙሪያ በአገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ዓውደ ጥናቶች፣ ኮንፈረንሶችና ስልጠናዎች ላይ በመሳተፍ የስራ ክፍሉን የመፈፀም አቅም እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡
  • የዘርፉ ምርምር ክህሎትን ለማጎልበትና በጥናትና ምርምር በተገኙ ውጤቶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፡፡
  • በአስቸኳይ ጊዜ አደጋዎች ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም ዙሪያ የባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲጎለብት ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፣ይከታተላል፣ያስተባብራል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.