የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የኦፕሬሽን አገልግሎት ጄኔራል ዳይሬክተር  ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አጠቃላይ የሀገራችን የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ፖሊሲና ስትራቴጂ መሠረት በማደረግ የዘርፉ ዓላዎች ለመደግፍና ለማስፈጸም የሚያስችል የአይሲቲ ስትራቴጂዎች፣ፖሊሲዎችና የአጠቃቀም መመሪያዎችን ያወጣል ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
  • የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ሚኒስትር መ/ቤቱ የተሰጠውን ተልእኮ ለመፈፀም የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ እቅድ ያቅዳል፣ ያስተባብራል በበላይነት ይመራል፤
  • የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቀዋማት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ግንባታና የአገልግሎት ተደራሽነቱ በየጊዜው ክትትል ያደርጋል ወቅታዊነቱን በመገምገም እንዲሻሻል ሀሣብ ያቀርባል አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የሚኒስቴር መ/ቤቱ መረጃ ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር
    ግኙነት ያደርጋል፣ አስፈላጊ የሆኑና ወቅቱ የሚፈልጋቸውን የኔትወርክ ሴኩሪቲ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎዕች ወደስራ እንዲገቡ ያደርጋል፣ አገልግሎቱን ይከታተላል፣ ደህንነቱን ይቆጣጠራል፤
  • በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሲስተም ልማት ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግና የሚያስችል ፕሮጀክት እንዲቀረጽ ያደርጋል ሲፈቀድ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • በተቋሙ የዳታ ማዕከል ውስጥ የዲዛይን፣ተከላና የኮንፊግሬሽን ስራ ያከናውናል፣ ፈጣንና የኔትወርክ አገልግሎት እንዲኖር ያደርጋል፣ ማዕከሉን በበላይነት ያስተዳድራል፤
  • የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በክልል የግብርና ቢሮዎች የኔትወርክ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • ዘርፉን በኢኮቴ ለማዘመን የሚሰሩና በፌደራልና በክልል ግብርና ቢሮዎች ለሚተገበሩ የሲስተም ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በበላይነት ይከታተላል፣ክፍተቶችን እየለየ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • ለሚኒስቴር መ/ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ሶፍትዌሮች እእንዲሰሩ፣የመሥሪያ ቤቱን ድህረ-ገፅ እንዲገነባ እንዲሁም በየጊዜው ወቅታዊ መሆኑን ይከታተላል፣ያሻሽላል፤
  • ሚኒስቴር መ/ቤቱን ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተለያዩ ሲስተሞችን በራስ አቅም እንዲለሙ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  • የሚኒስቴር መ/ቤቱ መረጃ በማጠናቀር ተሰብስቦ ወደ መረጃ ቋት መግባቱ ይከታተላል መረጃው ተደራሽነቱ ያረጋግጣል፤
  • የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳርያዎች ግዥ ለማከናወን ወቅታዊ የሆነ የቴክኒከ መስፈርት ያዘጋጃል፣ የቴክኒክ ግምገማ ያከናውናል፤
  • የተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳርያዎች አገልግሎት ጊዜ እንዲራዘም የጥገናና ዕድሣት ተግባራት እንዲከናወኑ ያደርጋል፤
  • የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሠራተኞች የኮምፒዩተር ክህሎትና የዕውቀት ክፍተቶች በመለየት ይህን ለማሻሻልና አፈጻጸማቸው ለማሣደግ የሚያስሉ ስልጠናዎች ያዘጋጃል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.