የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሚኒስቴር መ/ቤቱየኦፕሬሽን አገልግሎት ጄኔራል ዳይሬክተር ሆኖ የመንግሥት ሠራተኞችን አዋጅ፣ደንብና መመሪያ በመከተል የሚከተሉትን አብይ እና ቁልፍ ተግባራት ያከናውናል፡፡
  • የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ክፍተቶችንይለያል፣ያበቃል።
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ሃይል ልማት የሚመራ ገዢ ስትራቲጂና ዝርዝር ዐቅዶች እንዲዘጋጁና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል።
  • ከስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል።
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ሃይል ልማትና አስተዳደር የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፣ የስራ ሂደቶች፣ ማዕቀፎችን ወዘተ እንዳግባቡ ተዋደው / ተቀርጸው ተግባራዊ እንዲሆኑ ይመራል ይቆጣጠራል።
  • በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል።
  • በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል።
  • አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል።
  • የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ወጥና ዘመናዊ የአፈጻጸም ምዘና ግምገማና ማሻሻል ስርዐት እንዲኖረው የሚያስችል የአፈጻጸም ምዘናና አመራር ስርዐት እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል።
  • የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ኃይል ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የሰው ሃይል ልማት ፡ ስልጠናና ትምህርት ዕቅድና መርሃ ግብር እንዲዘጋጅና እንዲተገበር ያደርጋል።
  • የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የአመራር ብቃትና ዝግጅት ለማሳደግ የሚያስችል የተከታይ ማፍራትና የሞያ ዕድገት ስትራቴጂ፣ ዕቅድና ስርዐት ዝግጅትና ትግበራ በበላይነት ይመራል ያስተባብራል ይቆጣጠራል።
  • የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የሰው ሃይል ልማት አገልግሎት አሰጣጥ ለማላቅ የሚያስችል የክዋኔ ትዕምርትና (operating model); የስራ ሂደት የቲክኖሎጂና የመረጃ ስርዐት ግንባታና ትግበራን ይመራል።
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አደረጃጀትና ተቋማዊ ዕድገት ብሎም ባህል በሚፈለገው አቅጣጫ ለማጎልበት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የተቋማዊ አቅም ግንባታ ማዕቀፍ፣ ስልትና ዕቅድ እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል።
  • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል።
  • ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል።
  • ከፍተኛ አደረጃጀት ያለው ተቋም ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን እንዲከናወኑ ያደርጋል።
  • ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሃብት የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የተጠኑትን ይገመግማል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል።
  • የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል።

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.