የአበባ ልማት ዳይሬክቶሬት

የአበባልማትዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት

የአበባ ልማት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

  • ተገልጋዮች የሚፈልጓቸውን የአገልግሎት አይነቶች በአግባቡ መለየት፣ ወቅታዊ በማድረግ ተደራሽነታቸውን ማረጋገጥ፤
  • በወሳኝ የአበባ እርሻ ሥራ ወቅቶች በመስክ በመገኘት ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፤
  • ወቅታዊ የሜቲዮሮሎጂ እና የበሽታና ተባይ ክስተት መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያደራጃል ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፣ ምክር አገልግሎት መስጠት፤
  • በአበባ ልማት እርሻዎች የተሰማሩ ባለሀብቶች አፈጻጸም ለማሳደግና ምርታማነትንና ጥራትንና ለመጨመር የሚረዳ የኤክስቴንሽን ስርዓት መዘርጋት፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፤
  • የአበባ አምራች ባለሀብቶችን አቅም በተከታታይ ለማሳደግ የሚረዳ የአቅም ክፍተትና የስልጠና ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ አስተያየት ማቅረብ፤
  • የክፍሉን ፈጻሚዎች አቅም ክፍተት በመለየት ሥልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
  • ለባለሀብቱና ሌሎች አልሚዎች ልማት አዋጪና ውጤታማ የሆኑ ምርጥ የአበባ ልማት ቴክኖሎጂዎችና ተሞክሮዎችን በማሰባሰብ፣ መተንተን፤ መቀመር፣ የሚስፋፋበትን ሰርዓት መዘርጋት፤
  • የተዘጋጁ ቴክኖሎጂዎችና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረግ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማስፋት እንዲቻል የአሰራር ማንዋል ማዘጋጀት፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፤
  • ከዩኒቨርሲቲዎች እና ግብርና ምርምር ተቋማት ጋር በቅርበት በጥናትና ምርምር ስራ ተቀናጅቶ መስራት፤
  • መካከለኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲቻል የአበባ ልማት ተግባር ማሰልጠኛ ተቋማትን ማጠናከር፤
  • የሚመለከታቸው ዩኒቨርስቲዎች ካሪኩለም የማሻሻል ስትራቴጂና የትምህርት አሰጣጡም ለዘርፉ ውጤታማነት አስተዋፅኦ በሚያደርግ መልኩ እንዲሆን ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ፤
  • ለአበባ ልማት ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉትን ነባር የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት በመለየት፣ ለተቋማት የበጀትና የቁሳቁስ ምንጭ በማፈላለግ ተቋማቱን ማጠናከርና አዳዲስ የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት  ማቋቋም፤
  • የአምራቹ፣ የኮንትራት አርሶ አደሩና የአዉትግሮወሩን አቅም በስልጠና በመደገፍ አሰራሩ እንዲጎለብት ማድረግ።
  • አዉትግሮወሮች በግሎባል-ጋፕ ሰርቲፋይ እንዲሆኑ በማብቃት መስፈርትን ጠብቆ የመስራት ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ፤
  • በአውትግሮወርስና ኮንትራት እርሻ ስርዓት ከአልሚዎችና ባለሀብቱ ጋር የሚተሳሰሩ የአካባቢው አርሶ አደሮች የላቀ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የኢንተርፕሪነርሽፕ ስልጠና መስጠት፤
  • ለዘርፉ ልማት አዋጪና አስፈላጊ የሆኑ ከስልጠናና ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ መረጃ አደራጀቶ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ  ማድረግ፤
  • ባለሀብቱና ሌሎች ተገልጋዮች የሚፈልጉትን የድጋፍ ጥያቄዎች የቀረጥ ነጻ፣ የውጭ ዜጋ የሥራ ፈቃድ፣ የፈቃድ እድሳት ወዘተ/ በተቀላጠፈና በተቀናጀ ሁኔታ ጥራት ባለው መልኩ እንዲያገኙ ማድረግ፤
  • የአበባ ልማት መሬት የተረከቡ ባለሀብቶች በገቡት ውልና ባቀረቡት የአዋጭነት ጥናት ሰነድ መሰረት ልማት ማከናወናቸውን የአፈጻጸም መከታተያና መገምገሚያ መስፈርትና ደረጃ (Standard) ማዘጋጀት፣ ተደራሽ ማድረግ፤
  • የአበባ ልማት የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች ለክትትልና ድጋፍ በሚመች መልኩ በወቅት፣ በዝርያ አይነት፣ በተግባራት ዓይነትና በአካባቢ በመለየት የቁጥጥር፣ ክትትልና ድጋፍ ክላስተር ማዘጋጀት፣ መገምገም፤
  • በአበባ ልማት እርሻዎች የተሰማሩ ባለሀብቶች የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ሥርዓትና ማንዋል ማዘጋጀት፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
  • በተዘጋጀው ክትትልና ድጋፍ ማዕቀፍ መሰረት በየክላስተሩና በየወቅቱ ክትትል በማድረግ ችግሮችን መለየት፣ የተደራጀ መረጃ መያዝ፣ የድጋፍ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ የተዘጋጀውን የድጋፍ ዕቅድ ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ማሰራጨት፤ መፈጸማቸውን ክትትል ማድረግ፤
  • በተደረገው ክትትል መሰረት በተለዩ ችግሮች ዙሪያ ተወሰዱ እርምጃዎችንና መፍትሄዎችን ችግር ፈቺነትና ተፈጻሚነት ይከታተላል መቆጣጠር፤
  • የአበባ ልማት እርሻዎች የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በሚያግዝና በሚያሻሽል መልኩ እንዲከናወንና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የሁኔታ ዳሰሳ በማደረግ ለአመራሩና ለአካባቢው ማህበረሰብ ስልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፤ ትስስር የሚፈጠርበትን አግባብ መጠቆም፤
  • የአበባ ልማት እርሻዎችን ለማበረታታት ለአልሚዎችና ባለሀብቶች የሚሰጡ የተለያዩ ማበረታቻዎች በታሰበው መንገድ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ይመዘግባል፣ ይከታተላል፣ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት መስራት፤
  • በአበባ ልማት እርሻዎች የሚካሄድባቸው አካባቢዎች በመሰረተ ልማትና አስፈላጊ ግብዓት አቅርቦት የተሟሉ እንዲሆኑና ለባለሀብቱና ሌሎች አልሚዎች አዋጭ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ በትብብር መስራት፤
  • ለቀጣይ ክትትልና ድጋፍ የእያንዳንዱ አልሚ እና ባለሀብት ደረጃ የሚያሳይ ፕሮፋይል ማዘጋጀት፤ ለሚመለከተው የበላይ አካል አቅርቦ እንዲገመገም ማድረግ፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.