ግብርና ገበያ ልማት ዳይሬክቶሬት

የግብርና ገበያ ልማት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

ይህ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤

  • የግብርና ግብይት ስልት፣ ፖሊሲና የስራ ሂደትን ቀረጻና ትግበራ ይመራል፤
  • የግብይት እቅዱን ከዋጋ፣ ማስፋፋት፣ ተጠቃሚ፣ ምርት አንጻር በመፈተሽ የግብይት መነሻ ሀሳቦችን ይተገብራል፤
  • የግብርና ግብይት ስራ አጋዦችን፣ መሰራያዎችን፣ መገልገያዎቸን ለውጤታማ የውጭና የሀገር ውስጥ ግብይት ሰርዓት ውጤታማነት ቀረጻና ፍተሸ አግባብነት ይመለከታል
  • የምርት ጥራት ዋስትና ክትትልና ፍተሻ በግብርና ግብይት ስረዓትን እንዲመራ ማደረግ
  • የግብርና ምርት ፍላጎት መጨመር የሚያችልበትን አሰራር ይመራልየግብርና ግብይት አሰራርና ሂደቶች ላይ የተሰሩ የምርምር ስራዎችን፣ መረጃዎችና ዳታዎች ይመለከታል፤
  • የእውቀትና ክህሎት መሰረት ያደረግ  ወጤታማ ግብይት እንዲኖርና በዚህም በግብይት ውስጥ ባለደርሻ አካላትን፣ ፖሊሲን፣ ፈንድ የሚያደርጉ ባለደርሻዎችን በበጎ ተጽእኖ ማደረግ እንዲቻል ያደርጋል፤
  • የገንዘብ አስተዳደር ስርአትን በመምራት የገጠር ብድርና እውን በማደረግ የፋይናንስ ዶኩመንቶቸን፣ ኦዲትነን ይመራል፤
  • ክፉሉን አሰራርና ፣ እቅድ ትግበራንና አላማውን ማሰደግና መምራትየክፉሉን በጀት መሰራትና ይከታተላል፤
  • የክፉሉን የስው ሀይል ፋላጎት መለየት እና ያለውን ፍለጎት ለሙላት እቅድ ያወጣል፤
  • የፖሊሲ ቀረጻዎችን የስራ መመሪያዎችን የማውጣት ስራን ይመራል፤
  • የክፍሉን ሪፖርት ማጽደቅና ለሚመለከተው ክፍል ያስረክባል፤
  • በስሩ ያሉትን አካላት ወቅታዊ የስራ አፈጻጸም በመገምገም፣ በማሰልጠን ፣ በመከታተል ፣ በመምከርና ግብረ መልስ በመስጠት ያግዛል፤
  • የክፉሉን የሰራተኛ ዲስፒሊን በአግባቡ ይይዛል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.