የኤክስፖርት ቄራዎች ኢንስፔክሽንና ሠርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት

የኤክስፖርትቄራዎችኢንስፔክሽንናሰርተፊኬሽንዳይሬክቶሬትተግባርናኃላፊነት

የኤክስፖርት ቄራዎች ኢንስፔክሽንና ሠርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የሥጋ ምርመራ አገልግሎትን አስመልክቶ አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም ተፋጻሚነቱንም ይከታተላል፣
  • ስለ ሥጋ ምርመራ አዳዲስ ዓለም አቀፍ አሠራሮችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ በኤክስፖርት ቆራዎችም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ባሉ ቆራዎች ለሚሠሩ ባለሙያዎች ያስተዋውቃል፣
  • በኤክስፖርት ቄራ ግንባታና በሥጋ ምርት የወጪ ንግድ ሥራ ላይ ለመሰመራት ጥያቄ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች የማማከር ሙያው ድጋፍ ይሰጣል፣ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ለግንባታ የሚመረጠውን ሥፍራ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣
  • በኤክስፖርት ቄራዎች ውስጥ የሚሠጠው የቅድመ ዕርድ እና የድህረ ዕርድ የምርመራ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፣
  • ለውጪ ሀገር ገበያ በሚቀርብ የሥጋ ምርት ላይ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለው የሥጋ ምርመራና የሠርተፊኬሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፣
  • በሥጋና በሥጋ ውጤቶች አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የወጡ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ደንቦችንና ስምምነቶችን ያስከብራል፣
  • የእንሰሳት ማጓጓዣ ተሸከርካሪ ለእንሰሳት ማጓጓዣ ምቹና ፅዱ መሆናቸውን ይቆጣጠራል፣
  • በኤክስፖርት ቄራዎችና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ውስጥ የንፅህና አሠራርን መመሪያ (Standard Sanitation Operation Procedures) ያዘጋጃል ትግባራዊ ያደርጋል፣
  • በኤክስፖርት ቄራዎች ውስጥ ለሚሠሩ ሠራተኞችና ባለሀብቶች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ይሰጣል፣
  • ለኤክስፖርት ተመርቶ የተዘጋጀ የሥጋ ምርትና ውጤት በተገቢው ንፅህናና ቅዝቃዜ ወደ ኤርፖርት መጓጓዙን ይቆጣጠራል፣ዓለም አቀፍ የጤና ሠርተፊኬት በመስጠት ይሸኛል፣
  • ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን በሥጋ ምርት የወጪ ንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶችና የቄራ ሠራተኞች በየጊዜው የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣
  • የሥጋ ምርመራ አገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናል፣መልካም ተሞክሮዎችን ይቀስማል ተግባራዊም ያደርጋል፣ከሥጋ ምርት ተቀባይ ሀገሮች የሚቀርቡ ግብረ መልሶችን መሠረት በማድረግ የማሻሻያ እርምጃዎችን ይወስዳል፣
  • ለእንስሳት በሽታዎች የመረጃ አሰባሰብ ሥራ አጋዥ የሆኑ የሥጋ ምርመራ ሪፖርቶችን ከኤክስፖርት ቄራዎች ያሰባስባል፣ለሀገራዊ የመረጃ ቋት ሪፖርት ያደርጋል፣
  • ከሥጋ ምርመራ አገልግሎት የሚሰበሰቡ ገቢዎች በአግባቡ ወደ መንግሥት ካዝና ገቢ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያስፈፅማል፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.