የሴቶች፣ ሕፃናት ወጣቶች ጉዳይና ኤች አይ ቪ አካቶ ዳይሬክቶሬት

የሴቶችህጻናትናወጣቶችጉዳይናኤችአይቪጉዳዮችዳይሬክቶሬትተግባርናኃላፊነት

የዳይሬክቶሬቱንሥራበማቀድ፣በመምራትናበማስተባበር፣በመገምገም፣ የአሰራርሥርዓትበመዘርጋት፣የዓለምአቀፋዊናአህጉራዊስምምነቶችትግበራንናሪፖርትዝግጅትንበማስተባበር፣ማዕቀፎችንናስትራቴጂዎችንበመቅረፅናሥራላይበማዋል፣የሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች ጉዳይና የኤች አይ ቪ ላይየግንዛቤናንቅናቄተግባራትንበማካሄድ፣የባለድርሻአካላትንአቅምበማጐልበት፣ጥናትናምርምርበማካሄድ፣የፖሊሲሀሳቦችንበማመንጨት፣ተሞክሮዎችንበመቀመርናበማስፋት፣ፕሮጀክቶችንበመቅረጽናበመተግበር፣በፆታናበዕድሜየተለየመረጃእንዲደራጅናጥቅምላይእንዲውልበማድረግ፣ሴቶችንናወጣቶችንበማብቃት፣በሴቶችናወጣቶችወቅታዊናአንገብጋቢበሆኑችግሮችዙሪያየመወያያፅሁፎችእንዲዘጋጁበማድረግናበመምራት፤በሴክተሩለሴቶችናወጣቶችየስራዕድልመፍጠርየሚያስችሉየስራመስኮችየሚለዩበትንስልትበመቀየስናበመዘርጋት፣የወጣቶችየበጎፈቃድአገልግሎቶችንበማስተባበር፣የወጣቶችንየስብዕናልማትግንባታተግባራትንበማስፋፋት፣ልዩትኩረትለሚሹየሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ድጋፍእንዲደረግበማድረግእናየክትትልናድጋፍሥራዎችንበማስተባበርበሴክተሩየሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶችፍትሀዊናሁለንተናዊተሳትፎናተጠቃሚነትማረጋገጥ፡፡

የሴቶች፣ ወጣቶችና ሕፃናት ጉዳይና የኤች አይ ቪ አካቶ ዳይሬክቶሬትተጠሪነቱ ለግብርና ኤክስቴንሽን፣ ማስፋፊያ እና የአቅም ግንባታ ጀነራል ዳይሬክቶሬት ሆኖየሚከተሉትንተግባርናኃላፊነቶችይኖሩታል፡-

  • በሴክተሩ የሚዘጋጁ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ኢትዮጵያ ከሴቶች፣ህፃናትና የወጣቶች ጉዳይአኳያ ተቀብላ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ድንጋጌዎችና ስምምነቶች አኳያ እንዲቃኝ ያደርጋል፣ ተፈፃሚነቱን ያረጋግጣል፣
  • ሴቶችና ወጣቶች በልማቱ ላይ የሚያበረክቱትን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማዳበር የሚያስችል ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀት እንዲገመገም ያደርጋል፣የእርምት ለመውሰድ የሚያስችል ስትራቴጂ ይነድፋል፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ለመ/ቤቱ ሰራተኞችና በየደረጃው ላሉ መዋቅሮች  ግንዛቤ ለማስጨበጥና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚያግዙ ወቅታዊ  የሆኑ ትምህርቶችን እና አውደ ጥናቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
  • በመ/ቤቱ ውሰጥ የሚካሄድ ስልጠናዎች፣ ዕድገቶችና ዝውውሮች የሴቶችን ሙሉ ተሳትፎ የታከለባቸው መሆኑን ይከታተላል፣ ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤
  • የሴቶች፣ህፃናትና የወጣቶች ጉዳይ በሴክተሩ በሚካሄዱ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲካተት የማስፈጸሚያ ማዕቀፎች/ማኑዋሎች/መመሪያዎች/ያዘጋጃል/ያሻሽላል፣
  • በሴክተሩ የሚዘጋጁሰነዶችንከሴቶችና ወጣቶች ተሰትፎና ተጠቃሚነት አኳያ በመገምገምና ተገቢውን ግብአት በመስጠት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • በሴክተሩ እቅዶች የሴቶች፣ህፃናትና የወጣቶች ጉዳዮች እንዲካተቱ አዳዲስ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ክፍተቶችን በጥናት በመለየትናተገቢውን የመፍትሄ አቅጣጫ በመቀየስ ተግባራዊ ያደርጋል፣
  • በሥራ ላይ ያሉ የማስፈጸሚያ ማእቀፎችን የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ያሉ ክፍተቶችና ጥንከሬዎችን በጥናት በመለየትና ከዓለም አቀፍና አህጉራዊ ተሞክሮዎች ጋር በማጣጣም ያሻሽላል፣
  • በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል መቆጣጠር ዙሪያ የክልል ግብርና ቢሮዎች ተጠሪ መ/ቤቶችና የግብርና ኮሌጆች የኤች አይ ቪ ኤድስ ሚኒስትረሚንግ ተሳትፎን ይከታተላል፣በየጊዜውም የሥራ ትስስር ያደርጋል፣
  • የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት አገር አቀፍ፣ አህጉራዊና የዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመቅሰም የፈጠራ ሃሳቦችን ያመነጫሉ፣ አሰራሮችን ይቀይሳሉ፣ በተግባር ያውላሉ፣
  • በሴክተሩ በሴቶችና ወጣቶች ላይ የሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመለየት መፍትሄ የሚያገኙበት ስልት ይቀይሳል፣
  • በሴክተሩ የተዘጋጁ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ማካተቻ ጋይድላይንና ማኑዋሎች አተገባበር ለማጠናከር በተጠሪ መ/ቤቶች፣ በየደረጀው በሚገኙ መዋቅሮችና ባለድርሻ አካላት ተግባራዊ የሚሆንበትን አሰራርይዘረጋል፣ለትግበራውም ድጋፍ ያደርጋል፣
  • በሴክተሩ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ተሳትፎናና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጾታና በእድሜ የተለየና የተተነተነ መረጃ ለጠቃሚዎችና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የመረጃ ቋት እንዲመሰረትና ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርአት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣አፈጻጸሙንም ያረጋግጣል፣
  • በሴክተሩ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ የሥራ መስኮችን ለመለየት የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
  • ከሴክተሩ ተግባርና ኃላፊነት አኳያ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ ሥርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙንም ያረጋግጣል፣
  • ሴክተሩ የወጣቶች ስብዕና ልማት እና ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚስፋፉበትና የሚጠናከሩበት ስርአት ይዘረጋል፣
  • በተጠሪ መ/ቤቶች የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶችን ጉዳይ የሚከታተሉ መዋቅሮችና የቅንጅት ፎረሞች እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ተግባራዊነታቸውንም ያረጋግጣል፣
  • ከሴክተሩ ተግባርና ኃላፊነት አኳያ በሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ተጠቃሚነት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችና ምርምር ሥራዎችን ያካሂዳል፣ ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር በጋራ በሚከናወኑ ጥናቶችም ላይ በባለቤትነት ይሳተፋል፣
  • የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ በሴክተሩ በሚካሄዱ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና እቅዶች እንዲካተት ለማድረግ የሴክተር የማስፈጸሚያ ማዕቀፎችና ማኑዋሎች ከአገር አቀፉ ጋይድላይን፣ መመሪያዎችና ማዕቀፎች በመነሳት ያዘጋጃል፣
  • በዘርፉ ከተሰማሩ አጋር ድርጅቶች፣ከፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ ጽ/ቤት እና በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ከሚገኙ አጋር ድርጅቶች፣ፕሮጀክቶችና የስራ ክፍሎች ጋር ግንኙነት የሚፈጠርበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝባቸው የመ/ቤቱ ሠራተኞች እና ቤተሰቦች ድጋፍና እንክብካቤ የሚያገኙበት ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • ኤች አይ ቪ ኤድስ በግብርናው ሴክተር ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ የፖሊስ ሃሳቦችን ያመነጫል፣
  • ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ክልሎች በተለይም በግብርናው ሴክተር የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጽዕኖ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት እንዲያስከትል በተለይ ለግብርና አርብቶ አደር ቢሮዎች የጸረኤች አይ ቪ ኤድስ የማካተት ሥራ እንደ አንድ ዋና ተግባር ወስደው እንዲፈጽሙ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣
  • ኤች አይ ቪ ኤድስ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ርብርብ የሚጠይቁ በመሆኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፤
  • የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ሥልጠና ኮሌጆች ኤች አይ ቪ ኤድስ ሜኒስትሪም በማድረግ የሥልጠናቸው አካል እንዲያደርጉት አቅጣጫ ይነድፋል፣ እንዲተገበርም ያደርጋል፤
  • በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በተለይም በግብርናው ሴክተር የኤች አይቪ ኤድስ ተጽእኖ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት እንዳያስከትል ሁሉም የክልል ግብርና ቢሮዎች የጸረ- ኤችአይቪ ኤድስ የማካተት ስራ እንደ አንድ ዋና ተግባር ወስደው እንዲፈጽሙ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡ በየወቅቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎች በልማቱ ስለመሳተፋቸው ያስገኘው ጠቀሜታና የተከሰቱ ክፍተቶችን የሚለይ ጥናት በማካሄድ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፤
  • በሁሉም ክልሎች በተለይም በግብርናው ሴክተር የኤች አይቪ ኤድስ ተጽእኖ ኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት እንዳያስከትል ሁሉም የክልል ግብርና ቢሮዎች የጸረ- ኤችአይቪ ኤድስ የማካተት ስራ እንደ አንድ ዋና ተግባር ወስደው እንዲፈጽሙ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡ በየወቅቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎች በልማቱ ስለመሳተፋቸው ያስገኘው ጠቀሜታና የተከሰቱ ክፍተቶችን የሚለይ ጥናት በማካሄድ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፤
  • በገጠር የሚገኙ ሕጻናት መብቶቻቸውን ለመጠበቅ የሚከናወኑ ተግባርት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲከናወኑ ስርዓት ይዘረጋል ፡፡ እነዚህም ተግባራት በማስተማርና በመምራት፣ በቂ ምግብ ፣ልብስና መጠለያ እና የጤና እንክብካቤ ስለማግኘታቸው፣ ስለአለመገለላቸው፣ ሰብዓዊ መብታቸው ስለመጠበቁ፣ ቤተሰቡ ኃላፊነት ወስዶቡ ሕፃናቱን ስለመንከባከቡ ስለአለመጠቃታቸውና ትኩረት ሰለአለማግኘታቸው ጥናት በማድረግ የፖሊሲ ሃሳቦችን ያቀርባል፣ ግንዛቤም እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.