የግብርና ኤክስቴንሽን እና የአቅም ግንባታ ዕቅድ ዲዛይንና ትግበራ ዳይሬክቶሬት

የግብርና ኤክስቴንሽንና አቅም ግንባታ ዕቅድ ፕሮግራም ዝግጅትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተግባርናኃላፊነት

የግብርና ኤክስቴንሽን እናየአቅምግንባታዕቅድዲዛይንናትግበራ ዳይሬክቶሬትተጠሪነቱለግብርናኤክስቴንሽን፣ማስፋፊያእናየአቅምግንባታጀነራልዳይሬክተርሆኖየሚከተሉትተግባራትናኃላፊነትይኖሩታል፡፡

  • የግብርና ኤክስቴንሽን አቅም ግንባታና ሥልጠና የፖሊሲ ሀሳብ ያመነጫል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ያጸድቃል፣ የአፈጻጸም መመሪያና ሥልት ይነድፋል፣
  • የቅም ግንባታ ፍኖተ ካርታ፣ ስትራቴጂ፣ የአፈጻጸም መመሪያዎች፣ ሥርዓቶች ያዘጋጃል፣ እንደ ወቅቱና የአርሶ፣ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሩ እንዲሁም ሌሎች በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ፍላጐትን በመዳሰስ ይከልሳል፣
  • በአመራር ደረጃ የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችን የአቅም ውስንነት ለመሙላት የሚያስችል አገራዊ ጥናት በማካሄድ፣ በመተንተን፣ በማቀድ፣ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንዲሰጡ የረጅምና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂዎችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ እንዲሆንም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፣
  • በፌደራል ግብርና እና በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች የአፈጻጸም አቅም ክፍተቶችንና የሥልጠና ፍላጐት ጥናት እንዲካሄድ ያደርጋል፣ በተለየው ክፍተት መሠረትም ዓመታዊ የረጅምና የአጭር ጊዜ የአቅም ግንባታና የሥልጠና እቅዶችን በመቅረጽ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ የሥልጠናዎቹን አፈጻጸም ክትትል እንዲደረግ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ውጤታማነቱንም ይገመግማል፣
  • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግብርና እና ግብርና ነክ የሆኑ ሥርዓተ ትምህርቶች አተገባበርና አፈጻጸም ላይ አገራዊ ጥናት ያካሂዳል፣ ይተነትናል በሥርዓተ ትምርቱም ቀረጻ ጊዜም ሚ/ር መ/ቤቱን ወክሎ ይሳተፋል፣ የተቋሙ የሥልጠና ፍላጐት እንዲካተት ያደርጋል፣
  • በግብርና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለግብርና ባለሙያዎች የሚሰጡ ሥልጠናዎች የአርሶ፣ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሩ እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች ፍላጐት ያገናዘበ ሥልጠና እንዲሰጥ ዲዛይን ያደርጋል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፣ አስፈላጊ የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፣
  • የአርሶና አርብቶ አደሩን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በመጨመር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አላላት ጋር በማካሄድ ውጤቱን ይተነትናል፣ አስፈላጊ የሆኑ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፣
  • በአርሶና አርብቶ አደር ማሰልጠኛ ማእከላት አፈጻጸም ላይ አገራዊ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ ለአርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ይከታተላል፣ ተፈጻሚነቱን ያረጋግጣል፣
  • ገበያ ተኮር የግብርና ኤክስቴንሽን ሥርዓቱ እንዲሰርጽ አስፈላጊ የሆኑ የሥልጠና ሞጁሎች፣ መመሪያዎችን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
  • ግብርናን ለማዘመንና ንግድ ተኮር እንዲሆንና የገጠር ወጣቶች በግብርናው ሥራ እንዲሰማሩ የሚያደርግ ሥልት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ይነድፋል፣ ያስፈጽማል፣
  • ዳይሬክቶሬቱ አነስተኛ ይዞታ ላላቸው አርሶ፣ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮች ትኩረት በመስጠት እሴት በሚጨምሩ ምርቶች እና ተግባራት ላይ ለመሠማራት የሚያስችል አቅም በቋሚነት አቅም እንዲፈጠር  ያደርጋል፡፡
  • ቋሚና ዓመታዊ የአርሶ/አርብቶ አደር ቀኖችን፣ አውደ ርእዮችን፣ ልምድ ልውውጦችን፣ እና የተለያዩ አገራዊና አለም አቀፋዊ መድረኮች እንዲዘጋጁ በማድረግ የቴክኖሎጂ ፍላጐት የሚፈጠርበትን ሥልት ይነድፋል፣
  • የግብርና ሚኒስቴር የፕሮጄክት፣ ፕሮግራም፣ የአቅም ግንባታ እቅዶችን፣ አተገባበሮችን፣ አፈጻጸሞች ላይ ክትትል እንዲደረግ የአሰራር ስልት ይዘረጋል፣ አስፈላጊ የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያመቻቻል፣
  • ዳይርክተሩ በቀጥታ ለጀንራል ዳይሬክተሮች ሪፖርት ያደርጋል እንዲሁም በጄኔራል ዳይሬክተሩ የተሰጠውን ተጨማሪ ተዛማጅ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.