የስራስር ሰብሎች ልማት ዳይሬክቶሬት

የስራስር ሰብሎች ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የስራስርሰብሎችዳይሬክቶሬትተጠሪነቱ ለሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡፡

  • የሀገሪቱን የስራስር ልማት ዘርፍ ተግዳሮቶችን ሊፈቱ የሚችሉ ሃገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ የፖሊሲ ሀሳቦች ያመነጫል፣
  • የፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችንና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤
  • የስራስር ልማት፣ ግብይት፣ ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ሽግግር ተግባራትን መንግስት ባወጣቸው ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጅዎች፣ ስልቶች፣ ፕሮግራሞች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በተያዘው አቅጣጫ መሰረት ይፈፅማል፤
  • የሀገሪቱን የስራስር ልማት በፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች ከየወቅቱ ተለዋዋጭነት ጋር እንዲከለስ እና እንዲካተት ረቂቅ ሰነድ የማዘጋጀት፣ ግብዓቶችን የማሰባሰብ፣ እንዲሁም በማጠናቀር ጥቅም ላይ እንዲውል የትግበራ ዕቅድ የማዘጋጀት እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት የማስገንዘብ፣
  • በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ የስራስር ልማት ችግሮችን የሚፈታ አሰራር በማስፈንና ትኩረት አድርጎ በመስራት የሀገሪቱ የሆርቲካልቸር ልማትና ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ እንዲሆኑ በማድረግ ይሰራል፤
  • የስራስር ልማት እንዲዘምንና ተገቢውን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ከማድረግ አኳያ ያሉ መሰረታዊ ክፍተቶችን በዳሰሳ ጥናት መለየትና በቅደም ተከተል በማስቀመጥ እንዲፈቱ ማድረግ፣
  • በስራስር ዘርፍ የፈፃሚና አስፈፃሚን አቅም በቀጣይነት የሚገነባበትን ስርዓት ይዘረጋል፣
  • በየደረጃው ላሉ አስፈፃሚዎችና ፈፃሚዎች በሚደረገው የዳሰሳ ጥናትና በተዘረጋው የአቅም ግንባታ ስርዓት መሰረት ክፍተትን መሰረት ያደረገ ተከታተይነት ያለው ተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሰጥ ስልት ይቀይሳል፤ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣
  • አርሶ አደር ከአርሶ አደሮች የልምድና የክህሎት ልውውጥ የሚያደርጉበትን ስርዓት በመንደፍ ተግባራዊ እንዲደረግ ያደርጋል፣
  • የአቅም ክፍተትንና ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ልዩ ልዩ የስራስር ልማት ግብይት የሥልጠና ሞጁሎችን፣ ቴክስቶችንና ማኑዋሎችን እንዲዘጋጁ፣ የሞጁል ሥልጠናዎችን እስከ ተጠቃሚውና በገበሬ ማስልጠኛ ማዕከላት /FTC/ ደረጃ አንዲደርስ የአፈፃፀም ስልት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣አፈፃፀሙን ያከታተላል፣
  • የአምራቹን ፍላጎት ውጤታማና አቅምን ያገናዘበ የስራስር ልማት ለማካሄድ የሚያስችል እንዲሁም ለየስነምህዳር ቀጠናው ተስማሚነት መሰረት ባደረገ መልኩ ፓኬጅ ያዘጋጃል፤ ሥራ ላይ እንዲውሉ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • ሌሎች የአቅም ግንባታ ተግባራትን ማለትም ተግባራዊ የመስክ ጉብኝት፤ የምርጥ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በመቀመርና የልምድ ልውውጥ እና ወርክ ሾፕ መድረኮችን በማጋጀት አቅም ይገነባል፣
  • የስራስር ዘርፍን ለማዘመን ከተለያዩ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲመነጩና መነሻ ቴክኖሎጂዎች ሲቀርቡ (ምርጥ እና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ ዘሮች ወይም ችግኞች፣ ሜካናይዝድ ማሽኖች፣ የድህረ-ምርት ብክነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎች፣ የማቀነባበሪያ ማሽኖች እና የማሸጊያ መሳሪያዎች) እንዲላመዱ፣ ከአባዥ ማዕከላት ጋር በመቀናጀት እንዲባዙና እንዲሰራጩ ያደርጋል፣ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣ ችግር ያለባቸውን ጥናት በማካሄድ ዳግመኛ ምርምር እንዲካሄድባቸው ለተቋማቱ ማቅረብ፤
  • የስራስር ልማትን የሚያግዙ አዳዲስና ዘመናዊ አሰራሮች በውጭ ሃገር ያለውን ተሞኩሮ በመውሰድና እንደሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ ምርጥ ቴክኖሎጂዎችም እንዲገቡ በማድረግ እና ለሀገሪቱ ተሰማሚ ሆነው የተገኙትን እንዲስፋፉ ስልት ይቀይሳል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  • በስራስር ልማት የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች የቴክኖሎጂ፣ ልምድና ዕውቀት ሽግግር እንዲኖር አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን የስራስር አልሚ አርሶ አደሮች በኮንትራት ውል ስምምነት እና ሌሎች ጠቃሚ የአሰራር ስርዓቶችን በማስፈን የቴክኖሎጂ ስርፀትና ሽግግር እንዲሳለጥ ያደርጋል፣
  • አምራቾች በምርትና ምርታማነት፣ በማምረቻ ወጭ ቅነሳና አለምአቀፍ ጥራት /ቤንች ማርክ/ ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራዎችን ያከናውናል፤
  • ዳይሬክቶሬቱ በተገቢው የሰው ሃብት፣ ቴክኖሎጂ፣ መረጃ፣ ግብዓት የተደራጀ እንዲሆን ያደርጋል፤
  • ወቅቱን የጠበቀና የዘመነ ስራስር ልማት በሀገራችን ላይ እንዲሰፍን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያቅዳል፤ የማስፈፀሚያ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ እንዲፈፀም ያደርጋል
  • የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም (Climate smart agriculture) የስራስር ልማት ዕቅድ በየደረጃው ስለመኖሩ ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
  • ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት ዓመታዊ የስራስር የግብዓት ፍላጎት፣ ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ሽግግር፣ ምርት ግብይት ተግባራትን ለይቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
  • በስራ ዘርፉ ውስጥ ለሚገኙ ቡድኖች ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፤ አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፤
  • ገበያን መሰረት ያደረገ የስራስር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት ገበያ ተኮር የሆኑ የስራስር ምርቶች እንዲመረቱ ያደርጋል፤
  • ከሌሎች ዘርፎችና የስራ ክፍሎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስትራቴጅክ ግቦች በጋራ ይፈጽማል፤
  • በዳይሬክቶሬቱ ስር ባሉ ቡድኖች መካከል የቡድን መንፈስ (ቲም ስፕሪት) ስሜት በመፍጠር ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ እንዲሰሩ ያስተባብራል፤
  • በስራስር ልማት የተሰሩ ተግባራትን ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታና አለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘበና የተተነተነ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ለበላይ አመራሩ ያቀርባል፡፡
  • በዘርፉ ወቅታዊና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ አጫጭር ፕሮግራሞችና መግለጫዎችን በማዘጋጀት የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ያደርጋል፤
  • የስራስር አምራቾች ገበያን መሰረት ያደረጉ አመራረት እንዲከተሉና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች (ምርጥ እና የተሻሻሉ ዘሮች ወይም ችግኞች፣ ሜካናይዝድ ማሽኖች፣ የድህረ-ምርት ብክነትን የሚቀነሱ ቴክኖሎጂዎች፣ የማቀነባበሪያ ማሽኖች እና የማሸጊያ መሳሪያዎች) እንዲጠቀሙ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
  • ከምርምር ተቋማት ጋር በመገናኘት የስራስር አምራች አውትግሮዎርስ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶአደሮችን ችግር ያጠናል፣ ጠቃሚ የምርምር ውጤቶችን በማካተት አሰራሩን ይከልሳል፣ እንዲተገበሩ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣
  • የስራስር አምራቾች ያለባቸውን የምርትና ምርታማነት እንዲሁም የጥራት ችግሮች ያጠናል፣ የመፍትሄ ሃሳብ ለሚመለከተው ኃላፊ ያቀርባል፣ ሲፈቀድ በስራ ላይ ያውላል፤
  • የስራስር አምራቾችንና ባለሞያዎችን ያካተተ የምክክር መድረክ ያዘጋጃል፣ የኢንዱስትሪውን ችግሮች በጋራ በመፍታት ልማቱ እንዲፋጠን ያደርጋል፤
  • አምራቾች የስራስር ምርትን በሀገር ደረጃ አምረቶ ለመሸጥ ሊከተሏቸው የሚገቡ የመልካም እርሻ አተገባበርና ስራ አመራር ደንቦችን (Local GAP) ይቀርፃል፣ ግንዛቤ ይፈጥራል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል
  • የስራስር አምራቾች በተለይም ለውጭ ገበያ የሚያመርቱትን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር የአውሮፓ/ Euro-GAP/ ወይም የአለም ዓቀፍ (Global -GAP) የመልካም እርሻ አተገባበርና ስራ አመራር ደንቦችን ተከትለው እየሰሩ መሆኑን ክትትል በማድረግን ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ያረጋግጣል፤
  • ስራስር ለሚያመርቱ አምራቾች የአመራራት እና ጥራት አጠባበቅ ማኑዋል ያዘጋጃል፤ ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
  • የስራስር ልማትና ግብይት ሰፊ ጉልበት የሚጠይቅ ዘርፍ በመሆኑ ስራአጥ የሆኑ ሴቶችና ወጣቶችን ከሚመለካተው አካላት ጋር በመሆንና በመለየት በሆርቲካልቸር የስራ ዘርፍ ያሉትን ዕድሎች በመለየት በዘርፉ ጠቃሚነት ላይ ግንዛቤ መፍጠር፤
  • ለስራስር ልማት የሚውሉ የተፈጥሮ ዕምቅ ሀብቶችን (የተራራ ልማት፣ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ የማልማት፣ አማራጭ የውሃ ባንክ መጠቀም) በመለየት ያሉትን አማራጮች በመለየትና በመተንተን በዘርፉ ልማት ለመሳተፍ ለተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች የሚውሉበትን አሰራር ስርዓት በመቅረጽ ሳይንሳዊና ዘመናዊ ሆነ መንገድ እንዲፈፀም ማድረግ
  • በከተማና በጓሮ አካባቢ ሊለሙ የሚችሉ የስራስር ሰብሎችን እንደየአግሮ ኢኮሎጂ ለይቶ በማቀድ ሴቶችና ወጣቶች በስፋት እንዲጠቀሙ ማድረግ፤
  • ከፍተኛ የኒውትሪሽን ይዘት የያዙ የስራስር ሰብሎች በብዛትና በጥራት በማምረት ለምግብና ስነ ምግብ ዋስትና መረጋገጥ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ማስቻል፤
  • ምርጥ የአገር ውስጥ እና የውጭ የአሰራር ተሞክሮዎችን እንዲሰበሰቡ ያደርጋል፤
  • የስራስር ልማት ስራዎች መረጃ እንዲሰበሰብ፣ በመረጃ ቋት እንዲደራጁ እና እንዲተነተኑ በማድረግና ሥራውን በማስተባበር ውጤቱ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ያደርጋል፤
  • አካባቢዎች ለስራስር ልማት ያላቸውን አንጻራዊ የልማት አቅም (Potential) በመለየት ልማት ላይ እንዲውሉ ስልት ይቀይሳል፣ በጥናቱ መሰረት መተግበራቸው ይከታተላል፤
  • ከሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶች ጋር በመገናኘት በኮሪደር ልማት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ ይሰራል፤
  • አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አልሚዎች ምርታቸው ላይ እሴት በመጨመር ኤክስፖርት ለሚያደርጉ ልዩ የማበረረታቻ ፓኬጅ አጥንቶ ለሚመለከተው ኃላፊ ያቀርባል፣ ሲፈቀድ እንዲተገበር ድጋፍ ያደርጋል፤
  • የስራስር ልማትን ሊጠቅሙ የሚችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ይነድፋል፣ በኤክስፖርት ሒደት የተሻለ አሰራር በመቀመር ከማምረት እስከ ውጭ ገበያ ማቅረብ የሚተላለፍባቸውን የእሴት ሰንሰለት አቀናጅቶ መጠቀም ማስቻል እንዲሁም አቅም ያላቸውን ሞዴል አምራቾች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.