የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ዳይሬክቶሬት

የአትክልትና ዕፀ-ጣዕምልማትዳይሬክቶሬትተግባርናኃላፊነት

የአትክልትና ዕፀ-ጣዕምልማትዳይሬክቶሬትተጠሪነቱ ለሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

  • የሀገሪቱን የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ዘርፍ ተግዳሮቶችን ሊፈቱ የሚችሉ ሃገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ የፖሊሲ ሀሳቦች ማመንጨት፤
  • የፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችንና መመሪያዎችን ማዘጋጀት፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት፣ ግብይት፣ ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ሽግግር ተግባራትን መንግስት ባወጣቸው ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጅዎች፣ ስልቶች፣ ፕሮግራሞች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በተያዘው አቅጣጫ መሰረት መፈፀም፤
  • የሀገሪቱን የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት በፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች ከየወቅቱ ተለዋዋጭነት ጋር እንዲከለስ እና እንዲካተት ረቂቅ ሰነድ የማዘጋጀት፣ ግብዓቶችን የማሰባሰብ፣ እንዲሁም በማጠናቀር ጥቅም ላይ እንዲውል የትግበራ ዕቅድ የማዘጋጀት እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት የማስገንዘብ፣
  • በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ችግሮችን የሚፈታ አሰራር በማስፈንና ትኩረት አድርጎ በመስራት የሀገሪቱ የሆርቲካልቸር ልማትና ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ማድረግ
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት እንዲዘምንና ተገቢውን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ከማድረግ አኳያ ያሉ መሰረታዊ ክፍተቶችን በዳሰሳ ጥናት መለየትና በቅደም ተከተል በማስቀመጥ እንዲፈቱ ማድረግ፣
  • በአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ዘርፍ የፈፃሚና አስፈፃሚን አቅም በቀጣይነት የሚገነባበትን ስርዓት መዘርጋት፣
  • በየደረጃው ላሉ አስፈፃሚዎችና ፈፃሚዎች በሚደረገው የዳሰሳ ጥናትና በተዘረጋው የአቅም ግንባታ ስርዓት መሰረት ክፍተትን መሰረት ያደረገ ተከታተይነት ያለው ተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሰጥ ስልት ይቀይሳል፤ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣ አፈፃፀሙንም መከታተል፤
  • አርሶ አደር ከአርሶ አደሮች የልምድና የክህሎት ልውውጥ የሚያደርጉበትን ስርዓት በመንደፍ ተግባራዊ እንዲደረግ ማድረግ፤
  • የአቅም ክፍተትንና ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ልዩ ልዩ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ግብይት የሥልጠና ሞጁሎችን፣ ቴክስቶችንና ማኑዋሎችን እንዲዘጋጁ፣ የሞጁል ሥልጠናዎችን እስከ ተጠቃሚውና በገበሬ ማስልጠኛ ማዕከላት /FTC/ ደረጃ አንዲደርስ የአፈፃፀም ስልት እንዲዘጋጅ ማድረግ፣አፈፃፀሙን መከታተል፣
  • የአምራቹን ፍላጎት ውጤታማና አቅምን ያገናዘበ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ለማካሄድ የሚያስችል እንዲሁም ለየስነምህዳር ቀጠናው ተስማሚነት መሰረት ባደረገ መልኩ ፓኬጅ ያዘጋጃል፤ ሥራ ላይ እንዲውሉ ድጋፍ ማድረግ፤
  • ሌሎች የአቅም ግንባታ ተግባራትን ማለትም ተግባራዊ የመስክ ጉብኝት፤ የምርጥ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በመቀመርና የልምድ ልውውጥ እና ወርክ ሾፕ መድረኮችን በማጋጀት አቅም መገንባት፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ዘርፍን ለማዘመን ከተለያዩ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲመነጩና መነሻ ቴክኖሎጂዎች ሲቀርቡ (ምርጥ እና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ ዘሮች ወይም ችግኞች፣ ሜካናይዝድ ማሽኖች፣ የድህረ-ምርት ብክነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎች፣ የማቀነባበሪያ ማሽኖች እና የማሸጊያ መሳሪያዎች) እንዲላመዱ፣ ከአባዥ ማዕከላት ጋር በመቀናጀት እንዲባዙና እንዲሰራጩ ያደርጋል፣ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣ ችግር ያለባቸውን ጥናት በማካሄድ ዳግመኛ ምርምር እንዲካሄድባቸው ለተቋማቱ ማቅረብ፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማትን የሚያግዙ አዳዲስና ዘመናዊ አሰራሮች በውጭ ሃገር ያለውን ተሞኩሮ በመውሰድና እንደሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ ምርጥ ቴክኖሎጂዎችም እንዲገቡ በማድረግ እና ለሀገሪቱ ተሰማሚ ሆነው የተገኙትን እንዲስፋፉ ስልት መቀየስ፤ አፈፃፀሙን መከታተል፤
  • በአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች የቴክኖሎጂ፣ ልምድና ዕውቀት ሽግግር እንዲኖር አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም አልሚ አርሶ አደሮች በኮንትራት ውል ስምምነት እና ሌሎች ጠቃሚ የአሰራር ስርዓቶችን በማስፈን የቴክኖሎጂ ስርፀትና ሽግግር እንዲሳለጥ ማድረግ፤
  • አምራቾች በምርትና ምርታማነት፣ በማምረቻ ወጭ ቅነሳና አለምአቀፍ ጥራት /ቤንች ማርክ/ ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን፤
  • ዳይሬክቶሬቱ በተገቢው የሰው ሃብት፣ ቴክኖሎጂ፣ መረጃ፣ ግብዓት የተደራጀ እንዲሆን ማድረግ፤
  • ወቅቱን የጠበቀና የዘመነ አትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት በሀገራችን ላይ እንዲሰፍን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያቅዳል፤ የማስፈፀሚያ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ እንዲፈፀም ማድረግ፤
  • የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም (Climate smart agriculture) የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ዕቅድ በየደረጃው ስለመኖሩ መከታተል፣ መደገፍ፤
  • ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት ዓመታዊ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም የግብዓት ፍላጎት፣ ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ሽግግር፣ ምርት ግብይት ተግባራትን ለይቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
  • በስራ ዘርፉ ውስጥ ለሚገኙ ቡድኖች ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፤ አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፤
  • ገበያን መሰረት ያደረገ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት ገበያ ተኮር የሆኑ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ምርቶች እንዲመረቱ ማድረግ፤
  • ከሌሎች ዘርፎችና የስራ ክፍሎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስትራቴጅክ ግቦች በጋራ መፈፀም፤
  • በዳይሬክቶሬቱ ስር ባሉ ቡድኖች መካከል የቡድን መንፈስ (ቲም ስፕሪት) ስሜት በመፍጠር ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ እንዲሰሩ ማስተባበር፤
  • በአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት የተሰሩ ተግባራትን ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታና አለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘበና የተተነተነ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ለበላይ አመራሩ ያቀርባል፡፡
  • በዘርፉ ወቅታዊና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ አጫጭር ፕሮግራሞችና መግለጫዎችን በማዘጋጀት የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ማድረግ፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም አምራቾች ገበያን መሰረት ያደረጉ አመራረት እንዲከተሉና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች (ምርጥ እና የተሻሻሉ ዘሮች ወይም ችግኞች፣ ሜካናይዝድ ማሽኖች፣ የድህረ-ምርት ብክነትን የሚቀነሱ ቴክኖሎጂዎች፣ የማቀነባበሪያ ማሽኖች እና የማሸጊያ መሳሪያዎች) እንዲጠቀሙ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፤
  • ከምርምር ተቋማት ጋር በመገናኘት የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም አምራች አውትግሮዎርስ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶአደሮችን ችግር ያጠናል፣ ጠቃሚ የምርምር ውጤቶችን በማካተት አሰራሩን ይከልሳል፣ እንዲተገበሩ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም አምራቾች ያለባቸውን የምርትና ምርታማነት እንዲሁም የጥራት ችግሮች ያጠናል፣ የመፍትሄ ሃሳብ ለሚመለከተው ኃላፊ ማቅረብ፣ ሲፈቀድ በስራ ላይ ማዋል፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም አምራቾችንና ባለሞያዎችን ያካተተ የምክክር መድረክ ማዘጋጀት፣ የኢንዱስትሪውን ችግሮች በጋራ በመፍታት ልማቱ እንዲፋጠን ማድረግ፤
  • አምራቾች የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ምርትን በሀገር ደረጃ አምረቶ ለመሸጥ ሊከተሏቸው የሚገቡ የመልካም እርሻ አተገባበርና ስራ አመራር ደንቦችን (Local GAP) ይቀርፃል፣ ግንዛቤ መፍጠር፣ አፈፃፀሙን መከታተል፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም አምራቾች በተለይም ለውጭ ገበያ የሚያመርቱትን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር የአውሮፓ/ Euro-GAP/ ወይም የአለም ዓቀፍ (Global -GAP) የመልካም እርሻ አተገባበርና ስራ አመራር ደንቦችን ተከትለው እየሰሩ መሆኑን ክትትል በማድረግን ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ማረጋገጥ፤
  • አትክልትና ዕፀ-ጣዕም ለሚያመርቱ አምራቾች የአመራራት እና ጥራት አጠባበቅ ማኑዋል ያዘጋጃል፤ ተግባር ላይ እንዲውል ማድረግ፤ አፈፃፀሙን መከታተል፡፡
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማትና ግብይት ሰፊ ጉልበት የሚጠይቅ ዘርፍ በመሆኑ ስራአጥ የሆኑ ሴቶችና ወጣቶችን ከሚመለካተው አካላት ጋር በመሆንና በመለየት በሆርቲካልቸር የስራ ዘርፍ ያሉትን ዕድሎች በመለየት በዘርፉ ጠቃሚነት ላይ ግንዛቤ መፍጠር፤
  • ለአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት የሚውሉ የተፈጥሮ ዕምቅ ሀብቶችን (የተራራ ልማት፣ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ የማልማት፣ አማራጭ የውሃ ባንክ መጠቀም) በመለየት ያሉትን አማራጮች በመለየትና በመተንተን በዘርፉ ልማት ለመሳተፍ ለተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች የሚውሉበትን አሰራር ስርዓት በመቅረጽ ሳይንሳዊና ዘመናዊ ሆነ መንገድ እንዲፈፀም ማድረግ
  • በከተማና በጓሮ አካባቢ ሊለሙ የሚችሉ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ሰብሎችን እንደየአግሮ ኢኮሎጂ ለይቶ በማቀድ ሴቶችና ወጣቶች በስፋት እንዲጠቀሙ ማድረግ፤
  • ከፍተኛ የኒውትሪሽን ይዘት የያዙ የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ሰብሎች በብዛትና በጥራት በማምረት ለምግብና ስነ ምግብ ዋስትና መረጋገጥ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ማስቻል፤
  • ምርጥ የአገር ውስጥ እና የውጭ የአሰራር ተሞክሮዎችን እንዲሰበሰቡ ማድረግ፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ስራዎች መረጃ እንዲሰበሰብ፣ በመረጃ ቋት እንዲደራጁ እና እንዲተነተኑ በማድረግና ሥራውን በማስተባበር ውጤቱ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ያደርጋል፤
  • አካባቢዎች ለአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማት ያላቸውን አንጻራዊ የልማት አቅም (Potential) በመለየት ልማት ላይ እንዲውሉ ስልት ይቀይሳል፣ በጥናቱ መሰረት መተግበራቸው መከታተል፤
  • ከሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶች ጋር በመገናኘት በኮሪደር ልማት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት፤
  • አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አልሚዎች ምርታቸው ላይ እሴት በመጨመር ኤክስፖርት ለሚያደርጉ ልዩ የማበረረታቻ ፓኬጅ አጥንቶ ለሚመለከተው ኃላፊ ማቅረብ፣ ሲፈቀድ እንዲተገበር ድጋፍ ማድረግ፤
  • የአትክልትና ዕፀ-ጣዕም ልማትን ሊጠቅሙ የሚችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ይነድፋል፣ በኤክስፖርት ሒደት የተሻለ አሰራር በመቀመር ከማምረት እስከ ውጭ ገበያ ማቅረብ የሚተላለፍባቸውን የእሴት ሰንሰለት አቀናጅቶ መጠቀም ማስቻል እንዲሁም አቅም ያላቸውን ሞዴል አምራቾች እንዲፈጠሩ ማድረግ፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.