ስነ-ህይወታዊ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት

ስነ-ህይወታዊግብዓትአቅርቦትዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

ስነ-ህይወታዊ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤

  • ተገቢ ስነ-ህይወታዊ ግብአቶችን ፍላጎትና የግዠ ምንጮችን የመለየት አሰራርና እቅድን ፣ፖሊሲንና አሰራርን መፈተሸና ተግባራዊነታቸውን ይመለከታል፤
  • ስነ-ህይወታዊ የግብአት አቅርቦት አሰራርን ከጠቅላላው የግበዓት አቅርቦት ሰርዓት አንጻር እቅድ ማውጣት ስራን ይመራል፤
  • በግዠ ምንጮች ፣ በመጋዘኖች፣ እና በስርጭት ፖሊሲ ፣ አሰራር እቅድና አተገባበርን ይመራል፤
  • የስነ-ህይወታዊ ግብአት አቀራረብና ከአቅራቢዎች ጋር የሚኖርን ኮንትራቶችን ስራ ይመራል፤
  • የስነ-ህይወታዊ ግብአት አቅርቦት መልካም ተሞክሮዎችን በማውጣት ፣የተሻለ የዋጋ አቅርቦትና የቆሻሻ አወጋገድን ይተገብራል፤
  • የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለመተግበርና ለመደገፍ ፣ እና የንግድ ፍትሀዊነትን ይመርጣል፤
  • የግብርና ግብይት ለማስፋፋት እና የግብዓት አቅርቦት አሰራርን ፖሊሲዎች፣ ስልት፣ አሰራር ፣ ፕሮግራምና ሂደቶችን ቀረጻና ትግበራ ይመራል፤
  • የጎለበተና የማይናውጥ የግዢ ቦታዎችን ፣ ግዢዎችን፣ የቆጠራ ቁጥጥሮችን ፣ መጋዘኖችንና የአቅርቦትና የስርጭት ስራዎችን ይመራል፤
  • ተፋሰስ ልማት በሚካሄድበት አከባቢ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ሥራዎች  ያሉበትን ደረጃና ችግሮችን ለመፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መነሻ የሚሁኑ መረጃዎችን ይሰበስባል ይለያል፤
  • የተሰበሰቡ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት መረጃዎችን የማደራጀት፣ ለዘመናዊ መረጃ ቋትና ፣ለዕቅድ ዝግጀት ያመቻቻል፣
  • የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ሥራ በአከባቢው ያለበትን ደረጃና የህበረተሰቡን ልማዳዊ አሠራር በመለየት የተሰበሰቡ መረጃዎጨችን መሰረት በማድረግ ቀላል ትንታኔ ይሰጣል፣ በአግባቡ ያደራጃል፣
  • በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ የውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰብሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ያደርጋል፤
  • የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት በተመለከተ ለሚዘጋጁ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ ህጎች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች መረጃዎችን ያሰባስባል፤
  • የስነ-ህይወታዊ ግብአት በሚመለከት በተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ መሰረት ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ይሰጣል የሚሰጥበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • በተፋሰስ ልማት የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ሥራዎች ለማስፋፋት የተቀመሩ አዳዲሰና የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችና መመሪያዎችን ያሰራጫል ፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • በተፋሰስ ልማት ተግባራዊ የሚደረጉ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ሥራዎች በተዘጋጀው ዕቅድና መመሪያ መሰረት እንዲከናውኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ይከታተላል፤
  • የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት በተዘጋጀው የአሰራር ማኑዋል መሠረት እንዲተገበሩ ድጋፍ ያደርጋል ፣ መከናወናቸውንም ውጤታማነታቸውን ይከታተላል ሪፖርት ያደርጋል፤
  • በብዜት ስለሚቀርቡ የስነ ህይወታዊ ግብዓት አቅርቦት አሰራር እቅድና አተገባበርን ይመራል፤
  • የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የገጠር ፋይናንስ አገልግሎቶችን ስርዓት ለማሻሻል፣የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት፣ጥናቶችን በማድረግ፣ስልጠናዎችን በመስጠት፣ በመከታተልና በመደገፍና በአቅራቢዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ትስስር እንዲኖር በማድረግ ማህበረሰቡን የፋይናንስ ተጠቃሚነቱን ያረጋግጣል ፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.