የአካባቢ፣ አየር ንብረት ለውጥና ጥምር ደን እርሻ ዳይሬክቶሬት

የአካባቢ፣ አየር ንብረት ለውጥና ጥምር ደን እርሻ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን በማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥ በግብር ሴክተር ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በመቀነስ ምርትና ምርታማነት በቀጣይነት በማሳደግ ዘላቂ ልማትን እንዲረጋገጥ ይሰራል፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ መ/ቤቶች የተለያዩ የሥራ ዘርፎችና ሂደቶች ዓመታዊ የልማት ዕቅድ ውስት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስራዎችን በማካተት እንዲተገብሩ ያስተባብራል፣ ይከታተለል፣ ይደግፋል፡፡ በተጨማሪም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ የልማት ድርጅቶች እንዲሁም በተለያዩ የልማት አጋሮች በአገሪቱ ውስጥ በተበታተነና በተዘበራረቀ መልኩ እየተገበሩ የሚገኙትን የዓየር ንብረት ለውጥሥራዎችን በማስተባባርና በመምራት የዓየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በሁሉም ክልልና የኅ/ሰብ ክፍል ውስጥ በአግባቡ መስረፁንና አገሪቱም ለውጡን መቋቋም የምትችልበትን የአሰራር ሂደት እንዲፈተር ያደርጋል፡፡ 

ከአካባቢያዊና ማህበራዊ ህጎች አንፃር ሁሉም የሰብል፣ ሆርቲካልቸርና እንሰሳት ልማት ፕሮጀክቶች ህጎቹን መሰረት አድርገው የአካባቢና ማህበራዊ ጥበቃ ስራ ለሚካሄደው ግብርና ልማት ዋስትናና ህልውና መሆኑን በመረዳት ተግባራዊ እንዲያደርጉ የስራ ሂደታችን ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ መፍጠር፣ የክትትልና ድጋፍ ስራ በመሰራት የአካባቢና ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ግብርና ልማት በመፍጠር ልማቱ ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያስችሉ ስልቶችን ይነድፋል፣ የአሰራር ስረዓቶችን ይዘረጋል፡፡

የጥምርደንእርሻ፣አካባቢናአየርንብረትለውጥዳይሬክቶሬትተጠሪነቱለተፈጥሮሀብትናምግብዋስትናዘርፍሆኖየሚከተሉትተግባራትናኃላፊነትአለው፡-

 • በአገሪቱ ውስጥ ከዓየር ንብረት ለውጥ መላመድና ማተስረይ ጋር በተያያዘ በግብርና ሚ/ር ንዑሳን ዘርፎች፣ የክልል ቢሮዎችና በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያለሆኑ አካላት እየተከናወኑ የሚገኙና ወደፊትም የሚከናወኑ የዓየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም እንቅስቃሴዎችን በበላይነት ማስተባበርና መምራት፤
 • በተቋሙ ለዓየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ተያያዥነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊ ስምምቶች (Conventions) እና አገራዊ ይዘት ያላቸው ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እንዲሁም የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች መተግበራቸውን በበላይነት መከታተልና ማስተባበር፤
 • ተቋሙን የሚመለከቱ የአከባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ዙርያ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን አገሪቷ ከማጽደቋ በፊት መመርመር፣ ለበላይ አመራር አካላት ማቅረብ፣ ከጸደቁም በኋላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትክክል መተግበራቸውን መከታታልና ማረጋገጥ፤ መረጃውን አደራጅቶ ይይዛል፤
 • በሚኒስቴር መ/ቤቱ ስር በሚገኙ ዘርፎች የሚተገበሩ ሥራዎችን ከዓየር ንብረት ለውጥ መቋቋም/መላመድና ማስተሰረይ ጋር በማሳለጥ ለማስኬድ የሚረዱ ስርዓቶችን (ደንብ፣ መመሪያና የአሰራር ማኑዋሎችን) ማዘጋጀት ሲጸድቁም በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፤
 • ከዓየር ንብረት ለውጥ መቋቋምና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ከተቋሙ ተልዕኮ ጋር በተያያዘ ከዓለም-አቀፍም ሆነ ከሀገር ውስጥ በሚገኝ የገንዘብ ድግፍ የልማት ፕግራሞችንና ፕሮጄክቶችን መቅረፅ፣ ሲፈቀዱም መምራትና አተገባባራቸውን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • በክልል አግባብነት ያላቸው ቢሮዎች፣ በተቋሙ ስር የሚገኙ የስራ ክፍሎች፣ ተጠሪ ተቋማትና የዘርፎች አመራሮች በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገት አቅጣጫ (Green Growth Plan) የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የጋራ የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ተግባራት በቂ ትኩረት በመስጠት በመደበኛ የልማት ዕቅድ ውስጥ በማካተት በተቀናጀ መልኩ እንዲተገብሩ ማስተባበርና መከታተል፤
 • ተቋሙን የሚመለከቱ የዓየር ንብረት ለውጥን መላመድና ማስተስረይ ተግባራት በክልል አግባብነት ያላቸው ቢሮዎች፣ በተቋሙ ስር የሚገኙ የስራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት ዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ እንዲያካትቱ ማስተባባር በአግባቡ መተግበራቸውን መከታታልና ማረጋጋጥ፣ ውጤቱን ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትሪንግ ኮሚቴና የለበላይ ኃላፊ ማቅረብና ማሳወቅ፤
 • አገራዊና ዓለም-አቀፋዊ ከሆኑና የዓየር ንብረት ለውጥና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ግለሰቦችን በማስተባበርና በመቀናጀት ሥራዎች በተናበበ መልኩ እንዲተገበሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ስረዓት ይዘረጋል፣ የጋራ የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ልምድና መረጃ እንዲለዋወጡ ያደርጋል፤
 • የክልል ፈጻሚ አካላትን እንዲሁም ከዓየር ንብረት ለውጥ፣ ጥምር ዳን እርሻና የአከባቢና መህበራዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴ ለሚያደርጉ የባለድርሻና የተባባሪ አካላት (በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የልማት አጋሮች፣ አርሶና አርብቶ አደሮች) የግንዛቤ ማስጨበጫ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን መስራትና አስፈላጊ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፣ መረጃ ይይዛል፣ ያደራጃል፤
 • ተቋሙን የሚመለከቱ የልማት ሥራዎች የአካባቢና ማህበረሰብ አያያዝ ማዕቀፍ (Environmental and Social Management Framework) መሰረት በማድረግ ሥራዎች መተግበራቸውን መከታተልና ማረጋገጥ፤
 • በአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ ቁጥር 299/1995 መሰረት ወደ ልማት የሚገቡ የግብርና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ እንዲያዘጋጁና እንዲተገብሩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤ በግብርና ልማት እንቅስቃሴ ምክንያት የደንና ብዝሃ ሕይወት ሃብት መመናመን፣ የውሃ ሃብት ብክነትና ብክለት፣ እንዳይከሰት መከታተልና ማረጋገጥ፣ የአግሮ ኬሚካሎች አያያዝ አጠቃቀምና አወጋገድ ስርዓት መሰረት ተግባራዊ መሆኑን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከቱ ዓለም-አቀፍ የስምምነት መድረኮችና ድርድሮች ላይ ይሳተፋል፣ የስምምነቶቹን መንፈስም ለበላይ የአመራር አካላት ያቀርባል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ እንዲሆኑ የስተባብራል፣ ይከታተላል፤
 • የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣምያ እና ማስተሰርያ አመላካቾች/indicators/ በሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ስር የሚገኙ ዘርፎች (በመደበኛ፣ በፕሮግራሞችና በፕሮጀክቶች) እቅድ ውስጥ እንዲካተቱ/Mainstream/ እንዲደረጉና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለዚህ ስራ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ አፈጻጸማቸውንም መከታተልና የተገኛውን ውጤት ለተቋሙ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስትሪንግ ኮሚቴና ለበላይ ኃላፊ ማቅረብ፤
 • በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርናው ዘርፍ የሙቀት አማቂ ጋዞች መጠን መቀነሳቸውን፤ የአየር ንበረት ለውጥን ተጽእኖ መቋቋም አቅም መገንባቱን ለመከታተል የሚያስችል ወጥ የሆነ የመረጃ ቅብብሎሽ፣ የክትትል፣ ዘገባና ማረጋገጥ/MRV/ ሥርአትን ይዘረጋል፣ ያሻሽላል፣ ደረጃውን የተበቀ ዓመታዊ ሪፖርት እንዲዘጋጅ ክትትል ያደርጋል፣ መረጃ ያደራጃል ለበላይ ኃላፊ በማቅረብ ያጸድቃል፣ ያሠራጫል፤
 • የክልል ፈጻሚ አካላትን እንዲሁም ከዓየር ንብረት ለውጥና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ የጥምር ደንእርሻ፣ የአከባቢና መህበራዊ ድህንነት ዙርያ እንቅስቃሴ ለሚያደርጉ ባለድርሻና ተባባሪ አካላት (በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የልማት አጋሮች፣ አርሶና አርብቶ አደሮች) ክፍተት በመለየት የግንዛቤ ማስጨበጫ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን መስራትና በስራ አፈፃፀም ላይ ያመጡጥን ለውጥ መከታተልና መገምገም፤
 • ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ሂደት ውስጥ፣ ጥምር ደን እርሻና የአከባቢና መህበራዊ ደህንነት ስራዎች ዙርያ የተሻለ ውጤት ያስገኙ አሰራሮችንና ልምዶችን በመቀመር፣ በማደራጀት ወደ ሌላ ስፍራዎች እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
 • ተቋሙን የሚመለከቱ መንኛውንም የአየር ንብረት ለውጥ ነክ ጉዳዮችን፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ ጥምር ደን እርሻና የአከባቢና መህበራዊ ደህንነት ሥራዎችን በባለቤትነት ያስተባብራል፣ ያከናውናል፡፡

 

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.