የእንስሳት ኳራንቲን ምዝገባና ደህንነት ዳይሬክቶሬት

የእንስሳትኳራንቲንምዝገባናደህንነትዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት

የእንስሳት ኳራንቲን ምዝገባና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የኢምፖርት ኤክስፖርት ኳራንቲንና ሠርተፊኬሽን አገልግሎትን አስመልክቶ አዋጆች፣ደንቦችናመመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም ተፋጻሚነቱንም ይከታተላል፣
  • በሀገሪቱ የመግቢያና መውጫ በሮች ላይና አመቺ በሆኑ ሥፍራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የድንበር ቁጥጥር ኬላዎችንና የኳራንቲን ጣቢያዎች እንዲቋቋሙ ሃሳብ ያቀርባል፣ጠቀባይነት ሲያገኝ ያቋቁማል ያስተዳድራል፣
  • በሽታን ከመከላከል አኳያ ከውጪ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ወይም ከሀገር ውሰጥ ወደ ውጪ ለሚወጡና ለሚገቡ እንስሳት የእንስሳት ውጤቶችና ተዋፅዖዎች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የሥጋት ትንተና የሚካሄድበትን የአሠራር ስልት ይቀይሳል፣የትንተናውን ውጤት መሠረት በማድረግ ወደ ሀገር ለሚገቡ እንስሳት፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተወፅዖዎች ዓለም አቀፍ የማስገቢያ ፈቃድ (Import permit) ¾T>cØuƒ” ስታንደርድ ያወጣል፣ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፣
  • ለእንስሳት በሽታዎች ሥርጭት የመረጃ አሰባሰብ ሥራ አጋዥ የሆኑ የበሽታ ክስተት ሪፖርቶችን ከኳራንቲን፣መድለቢያና ማቆያ ጣቢያዎች ያሰባስባል፣ለሀገራዊ የመረጃ ቋት ሪፖርት የሚደረግበትን ሥርዓት ይዘረጋል.ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣
  • የተቀባይ ሀገሮች ተቆጣጣሪ አካላት በአካል መጥተው ግብታቸው ተጠናቆ ሥራ ለመጀመር የተዘጋጁ የኳራንቲን ጣቢያዎች ተፈትሸውና ተመዝነው ዕውቅና እንዲያገኙ በይፋ ይጋብዛል፣ ያስተናግዳል፣ የምዘናውንም ውጤት ለሚመለከተው ያሳውቃል፣
  • የሀገሪቱን የእንስሳት ልየታ፣ምዝገባ፣ደህንነትና ጥበቃ ሥርዓትና ለመዘርጋትየሚየስችል የፖሊሲ ሃሳብ ያመነጫል፣ ስትራቴጂ ይቀርፃል፤ የሕግ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፣ሲፈቀድም ይተገበራል፣
  • በቁም እንስሳት ተቀባይ አገሮች ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ጠንካራ የእንስሳት ልየታ፣ምዝገባና የኋልዩሽ ክትትል ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የአጭር፣የመካከለኛና፣የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ይነድፋል፣በየምዕርፉም እንዲተገባር ያደርጋል፣
  • የእንስሳት ልየታና ምዝገባ ሥርዓቱንና የእንስሳት ጤና ጥበቃ አገልግሎቱን ውጤታማ የሚያደርጉ አዳዲስና ዘመናዊ አሰራሮችን በመለየት የቴክኖሎጂ ሽግግር ያደርጋል፣ተግባራዊነቱንም ይከታተላል
  • ¾እንስሳት ደህንንት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመሥራት እንስሳት በመኖሪያ አካባቢያቸው፣አገልግሎት በሚሰጡበት፣በሚጓጓዙበትና የጤና አገልግሎት በሚያገኙበት ወቅት ደህንነታቸው /Welfare/ እንዲጠበቅና ከጭካኔ ተግባራት ነፃ እንዲሆኑ ማድርግ የሚቻልበትን የአሠራር ስልት ይቀይሳል፣ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣
  • ብሔራዊ የእንስሳት ደህንነት የሥራ ቡድንን(Animal Welfare Working Group)እንቅስቃሴን በበላይነት ይመራል፣ያጠናክራል፣የሙያ ዕገዛና ድጋፍ ይጣል፣
  • የተለያዩ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች በእንስሳት ደህንነትና ጥበቃ ሥራዎች ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ይከታተላል፣በቅንጅት የሚሰሩበትን አሰራር በመቅረፅ ተግባራዊ ያደርጋል፣
  • ከእንስሳት ደህንነትና ጥበቃ አኳያ በውጪ የገበያ ዕድሎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ክፍተቶችና ሥጋቶችን ይለያል፣ክፍተቱን ለመሙላት የሚያስችሉ የእንስሳት ደህንነት ሥራዎችን ለመሥራት የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ተግባራዊነቱንም ይከታታተላል፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.