የመኖ ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት

የመኖ ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት

በአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ችግር ላይ የተመሠረተ የሀገሪቱን የእንስሳት መኖ ለማልማት የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፡፡ ለእንስሳት ሀብት ልማት አስፈላጊ የሆኑ የውኃ፤የመኖ ባንኮች፣ የተፈጥሮና የመስኖ ግጦሽ ልማት እና አጠቃቀም የሚስፋፉበትን፣ ቀጣይነት ያለው ጥቅም የሚሰጡበትን የአሠራርና ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነድፋል፡፡ የእንስሳት መኖ ቴክኖሎጂዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ያጠናቅራል፣ለየሥነ-ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የሚያሰራጭበትን ስልት ይነድፋል፡፡

የመኖ ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለእንስሳት ሀብት ዘርፍ ሆኖ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነት አለው፡-

  • ለእንስሳት መኖ ልማትና አጠቃቀም፣ ውጤታማና ቀጣይነት የሚረዱ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ያመነጫል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያድረጋል፣
  • በአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ችግር ላይ የተመሠረተ የሀገሪቱን የእንስሳት መኖ ለማልማት የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃዉ የአፈጻጸሙን ሂደት ይከታተላል፣
  • በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ለእንስሳት ሀብት ልማት አስፈላጊ የሆኑ የውኃ፤የመኖ ባንኮች፣ የተፈጥሮና የመስኖ ግጦሽ ልማት እና አጠቃቀም የሚስፋፉበትን፣ ቀጣይነት ያለው ጥቅም የሚሰጡበትን የአሠራርና የአስተዳደር ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነድፋል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊቱን ይከታተላል፣ ሀገራዊ መረጃ ያደራጃል፣ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • አዳዲስ ሀገር አቀፍ የመኖ ልማት ኘሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን ይቀርጻል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃዉ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ቴክኒካዊ ዕገዛ ይሰጣል፣
  • ለሀገሪቱ የመኖ ልማትና የማምረቻ ኢንዱስትሪ ማነቆ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የፖሊሲ ችግሮችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በዳሰሳ ጥናት በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱንና ዉጤቱን ይገመግማል፣ግብረ መልስ ያስጣል፣
  • የእንስሳት መኖ ቴክኖሎጂዎችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ለየሥነ-ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በመቅረፅና የአሰራር ስልት በመንደፍ  ለባለሙያዎች/ለተጠቃሚዎችስልጠና በመስጠት ያስተዋውቃል፣ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የሴቶች እና የወጣቶች ልማት ቡድኖች በተለያዩ የእንስሳት መኖ ልማት አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት በማድረግ የሚደረጁበትን የአሰራር ስልትና ስትራቴጂ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ያጠናል፣ ሲፀድቅም ተግባር ላይ እንዲዉሉ ለክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የስልጠና፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣
  • የመኖ ልማት ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች ከአሬንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትና የአየር ለዉጥ መቋቋሚያ ስትራቴጂ ሥራዎች ጋር በማጣጣም እንዲካሄድና የተፈጥሮ ሀብቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ተስማሚነት ያለው አሠራር እንዲፈጠር አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመሆን የተሳለጠ ሀገራዊ ሥርዓት እንዲዘረጋ ሐሳብ ያመነጫል፣ ሲፀድቅ ይተገብራል፣ አፈጻጸምንም ይገመግማል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • ለችግር ጊዜ የሚዉል፣ ደራሽ ነፍስ አድን የመኖ እና የውኃ አቅርቦትን አስተማማኝ ለማድረግ የቅድሚያ ትንበያ፣ መከላከልና የዝግጁነት ሥራዎችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ይነድፋል፣ የክምችት አቅም እንዲገነባ ያደራጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ዉጤቱን ይገመግማል፣ግብረመልስ ይሰጣል፣
  • ሰፋፊ የተሸሻሉ የመኖ ዕፅዋት እርሻዎች በኢንቨስትመንት አሠራር እንዲቋቋሙ፣የሀገር ውስጥ ፍጆታ እንዲሻሻልና የመኖ ወጪ ንግድ እንዲጠናከር የአሰራር ስልት ይነድፋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣የቴክኒክ ዕገዛ ይሰጣል፣
  • የተለያዩ የእርሻና የእንዱስትሪ መኖ ጥሬ ዕቃ ወይም ግብዓቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲሰባሰቡ፣ እንዲከማቹና ፣ ለተጠቃሚዉ እንዲደርሱ ለማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችንና  የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተደራሽነትን የሚያሳልጡ የሥልጠናና የሙያ አገልግሎት በየደረጃው እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
  • የምርምር ሥራ የሚሹ የእንስሳት መኖ ልማት አጀንዳዎችን በመለየት ምርምር እንዲካሄድባቸው ሐሳብ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ዉጤቱንም ከሌሎች ጋር በመሆን እንዲተገበር ያደርጋል፣ይገመግማል፣ ግብረመልስ ይሰጣል፣
  • የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ተቋማት እንዲቋቋሙ፣እንዲስፋፉ፣ለተለያዩ የእንስሳት ዓይነቶችና የምርት ባህርያት ላይ የተመሠረተ የምጥን መኖ ቀመር ያዘጋጃል፣ የአመጋገብ (ኑትሪሽን) ሥርዓት ያደራጃል፣ የምጥን መኖ ምርት ሀገሪቱ በአፀደቀቻቸዉ ወይም በተቀበለቻቸዉ የጥራት ደረጃዎች መሠረት እንዲመረቱ ከሚመለከታቸው የቁጥጥር አካላት ጋር የድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል፣
  • ለሴክተሩ ባለሙያዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሀብቶችና ቡድኖች የአቅም ግንባታ ሥልጠና፣ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ውጤቱንም ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል::
  • ከበላይ አካል የሚሰጡትን ተጨማሪ ሥራዎች ያከናውናል፣ የዕቅድ አፈፃፀምና ወቅታዊ ስራዎችን ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.