FDRE Ministry of Agriculture

የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ (ዶ/ር) የከተማ ግብርና ልማት ስራዎችን ጎበኙ።

(አዲስ አበባ፣ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በአዲስ አበባ የከተማ ግብርና ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም የተቀናጀ የተፈጥሮ የከተማ ግብርና እና የእንስሣት ርባታ ስራዎችን ተመልክተዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን የፋይናንስና ቴክኒካል ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በዛሬው ዕለት ከአለም የምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር በመሆን ተዘዋውረው የጎበኙዋቸው የከተማ ግብርና ልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ (ዶ/ር) በበኩላቸው በከተማ ግብርና ባዩት የልማት ስራዎች መደነቃቸውን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለመደገፍ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በቀጣይም የከተማ ግብርና ልማት ስራ መስፋፋት እንዳለበት ጠቁመው ይህንንም ለማሳካት ድጋፉም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ሰለሞን ደምሰው

ፎቶግራፍ፦ ማቲዮስ ተገኝ

#ከማምረትበላይ

#BeyondProduction

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *