FDRE Ministry of Agriculture

የህልም ጉልበት ለዕመርታዊ ዕድገት!

(አዲስ አበባ፣ ኅዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች “የህልም ጉልበት ለዕመርታዊ ዕድገት!” በሚል መሪ ሃሳብ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) መድረኩን ሲከፍቱ ከለውጡ በኋላ በግብርናው ዘርፍ በአምስት ዓመታት ውስጥ እመርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅሰው ለአብነትም በስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በሌማት ትሩፋት ብሔራዊ ፕሮግራሞች ተቀርፀው በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለውይይት መነሻ የሚሆን በአምስት ዓመታት ውስጥ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ትሩፋቶች እና ተግዳሮቶች እንዲሁም ቀጣይ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ከግብርና ፖሊሲ ማሻሻያ እና የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ አንፃር እንዲሁም ስራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ከአመራሩ እና ሰራተኛው ተነስቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዘርፉ የተመዘገቡ ለውጦችን ለማስቀጠል የአመራሩ እና የሰራተኛው ሚና ጉልህ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል ሁሉም ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

በእለቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ደም ለግሰዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዮሐንስ ደመቀ

ፎቶግራፍ፡- ያሬድ አሰፋ

—————-