የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት

የምግብዋስትናማስተባበሪያዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የምግብዋስትናማስተባበሪያዳይሬክቶሬትተጠሪነቱየተፈጥሮሀብትናምግብዋስትናዘርፍበሚኒስትርዴኤታሆኖየሚከተለውተግባርናኃላፊነትይኖረዋል፡-

  • የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በባለቤትነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፣ አፈጻጸሙንም ክትትል በማድረግ በአፈጻጸም ሂደት ላጋጠሙ ችግሮች የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
  • ለፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን ሀብት(ገንዘብ/ ምግብ) በማሰባሰብና በፕሮግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር መሰረት የበጀት ድልድል በመስራት ለክልሎች እንዲሰራጭ ያደርጋል፣ የተላከውም ሀብት ለታለመለት አላማ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
  • ለፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ክፍያ የሚውል ሀብት (ገንዘብ/ምግብ) ለክልሎችና ወረዳዎች ፈጥኖ እንዲደረስ በማድረግ የተጠቃሚዎች ክፍያ በፕሮግራሙ መርህ መሰረት (primacy of transfer) የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት መፈጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፡፡
  • በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አማካኝነት የሚካሄዱ የማህበረሰብ የልማት ስራዎችን በባለቤትነት ይመራል ፣ ያስተባብራል ፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ጋር በመሆንም አፈጻጸሙን ይከታተላል ፣ በአፈጻጸም ሂደት ላጋጠሙ ችግሮችም የማተካከያ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
  • የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ቀዳሚ የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ከሚመለከታው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የብድር አገልግሎት ያገኙት ተጠቃሚዎች በተሰጣቸው ብድር በመጠቀም በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሰስራዎች ላይ በመሳተፍ በቤተሰብ ደረጃ ተጨማሪ ገቢና ጥሪት ፈጥረው ኑሮአቸውን እያሻሻሉ የመጡ መሆናቸውን ይከታተላል፣ የፕሮግራሙ አፈጻጸም ውጤታማነትን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ መልስም ይሰጣል፡፡
  • የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የምግብ አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት የቅደሚያ ማስጠንቀቂያና ምለሽ ዳይሬክቶሬት እና የሰትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት ኤጀንሲ መጋዘኖችን መጠቀም የሚያስችል አሰራር ይፈጠራል፡፡
  • የማህበረሰብ የልማት ሰራዎችን ከቤተሰብ የኑሮ ማሻሻያ ስራዎችና ከስርአተ ምግብ ጋር በማስተሳሰር ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል፣በሚሰሩት የማህበረሰብ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅሙ እንዲጎለብት ይደረጋል፡፡
  • የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አጠቃላይ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ እንዲሁም ለሚፈልጉት አካላት ተደራሽ ያደርጋል፡፡
  • የክልል ምግብ ዋስትና የስራ ሂደቶች በየሩብ አመቱ የሚልኩትን የአፈጻጸም ሪፖርት በመገምገም የተጠቃለለ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
  • በየሩብ አመቱ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የፋይናንስ አጠቃቀምና አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለገንዘብ ሚኒሰቴር ያቀርባል፡፡
  • በየስድስት ወሩ ከለጋሽና በክልሎችና ፌደራል ደረጃ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈጻጸምን ይገመግማል፣ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡

 

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.