የእንስሳት ጤናና ቬትረነሪ ፐብሊክ ሄልዝ ዳይሬክቶሬት

የእንስሳትጤናናቬትረነሪፐብሊክሄልዝዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

የእንስሳት ጤናና ቬትረነሪ ፕብሊክ ሄልዝ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የሀገሪቱን የእንስሳት ጤናና ቬትረነሪ ፕብሊክ ሄልዝ ፖሊሲና ስትራቴጂ ይቀርጻል፤ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች ያዘጋጃል፤ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣የእንስሳት ጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል፣በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወቅታዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን እንዲዘረጋ ያደርጋል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • ሀገራችን በገባችው አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ውሎችና ስምምነቶች እንዲተገበሩ ያደረጋል፣ያስተባብራል፤አፈጻጸሙን ሪፖርት ያደርጋል፣ድንበር ዘለልና ዞኖቲክ የእንስሳት በሽታዎች በሀገሪቱ ላይ የሚያደርሱትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት በማጥናት የመፍትሔ አቅጣጫ ይነድፋል፤ሲፀድቅም አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • ከእንስሳት ጤና መረጃ ሥርዓት ጋር በተያያዘ የፖሊሲ ሃሳብ ያመነጫል፣ስትራቴጂ ይቀርፃል፤ የሕግ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፣ሲፈቀድም ይተገበራል፣የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና ዓለምአቀፋዊና አህጉራዊ ግዴታዎችን መሠረት በማድረግ ጠንካራ የእንስሳት ጤና መረጃ ሥርዓት ይገነባል፣ያስተዳድራል፣በየደረጃው ባሉ አካላት ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል ፣አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
  • በተገነባው የመረጃ ሥርዓት አማካኝነት በወቅቱ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ያደራጃል፣ይተነትናል፣ ለሚመለከተው የሥርዓቱ አካል ግብረመልስ ይሠጣል፣በተገኘው የመረጃ ትንተና አመላካች ውጤት ላይ በመመሥረት መወሰድ ያለበትን የቄጥጥርና መከላከል ርምጃ ያመለክታል፣ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፣የተገኘውንም ውጤት ይገመግማል፣
  • በወረርሽኝ መልክ በየወቅቱ ለሚከሰቱና በአጭር ጊዜ ውሰጥ ከፍተኛ ጉዳት ለሚያስከትሉ በሽታዎች የቅኝት ሥራዎችን ያስተባብራል፣ይመራል፣ውጤቱንም ያሳውቃል፣በመረጃ ሥርዓቱ የተገኙ ጭብጦች ላይ በመመርኮዝ በሽታዎች ሊያደርሱ የሚችሉትን ኤኮኖሚያዊ ጉዳት፣በህብረተሰብ ጤና ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተፅእኖ፣በውጪ ምንዛሪ ግኝትና በዝርያ ማሻሻል ሥራዎች ላይ ያለቸውን ተፅእኖ፣መሠረት በማድረግ የብሽታዎችን የመከላከል ቅደም ተከተል ያወጣል፣ያ
  • አንድ ጤና ለሁሉም (One Health) የሚለውን ዓለም አቀፍ የጤና ጥበቃ መርህ መሠርት በማድረግ ከዱር፤ከእርሻና ከቤት እንስሳት ወደ ሰው እንዲሁም ከሰውም ወደ ዱር፤እርሻና የቤት እንስሳት በመተላለፍ ከፍተኛ ማህበራዊና ኤኮኖሚያው ጉዳት የሚስከትሉ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚየስችል የፖሊሲ ሃሳብ ያመነጫል፣ ስትራቴጂ ይቀርፃል፤ የሕግ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፣ሲፈቀድም ይተገበራል፣
  • ከእንስሳት ወደ ሰው እንዲሁም ከሰው ወደ በመተላለፍ ከፍተኛ ማህበራዊና ኤኮኖሚያው ቀውስ የሚየስከትሎ በሽታዎችን ሀገር አቀፍ የመዘርዝር ሰነድ ያዘጋጃል፣ ዞኖቲክ በሽታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የጋራ የክትትል የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎችን ይሠራል፣ለህብረተሰቡ ተከታታይ ትምህርት ይሰጣል፣
  • ቅድሚያ በተሰጣቸው የእንስሳት በሽታዎች ላይ የመከላከልና የቁጥጥር ፕሮግራም ይቀርፃል፣ በሚመለከተው አካል ተፈፃሚ መሆኑን ይከታተላል፣የማስተካከያ ርምጃዎችንም ይወስዳል፣ለዋና ዋና በሽታዎች የስነምህዳራዊ የስርጭት ካርታ ያዘጋጃል፣(ሥጋት ተኮር) በክትባት መከላከል ለሚቻሉ በሽታዎች የክትባት ካሌንደር፣የባዩሴኩሪቲ ሥርዓት ያዘጋጃል፣ተግባራዊነቱንም ይከታታላል፣
  • በወቅታዊ የእንስሳት ጤናዎች ሁኔታ ላይ በመመስረት በህግ አግባበብ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ መገለፅ ያለባቸውን (Notifiable) በሽታዎች መዘርዘር ያወጣል በሚኒስትሩ ያፀድቃል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ከሀገራዊ አህጉራዊ አዓለምአቀፋዊ ሁኔታዎች በመነሳት በየጊዜው ለሀገሪቱ ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ የእንስስሳት ጤና ሁኔታዎች ላይ የሥጋት ትነተና ያካሂዳል፣የሥጋት መጠን ይለያል፣መወሰድ ያለበትን ርምጃ ያመለክታል፣ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣
  • በኢፒዲሚዮሎጂ ዙሪያ የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ይለያል፣ያዘምናል፣የባለድርሻ አካላትን አቅም የመገንባት ሥራዎች ያስተባብራል፣ይመራልለዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅትና(OIE) ለህጉራዊው የአፍሪካ ህብረት የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (AU-IBAR) በየጊዜው ሪፖርት ያቀርባል፣
  • የእንስሳት ጤና አገልግሎትን ለማሻሻልና ለማዘመን የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን ያስፋፋል፣ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ የምርምርና የልህቀት ተቋማት እንዲደራጁ ሐሳብ ያቀርባል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣ለእንስሳት ጤና አጋዥ የሆኑ የፋይናንስ፤የመድን ዋስትና እንዲሁም የብድር አቅርቦት ሥርዓት እንዲጎለብት አግባብ ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራል፤
  • በአርብቶ አደር አካባቢ ለልዩ የእንስሳት ጤና ጥበቃ አገልግሎት የሚያስፈልረጉ መሠረተ ልማቶች፣ጤና ኬላ፣ክሊኒኮች፣መስፋፋታቸውን ይከታተላል፣የማህበረሰብ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች እንዲሟሉ ይደግፋል፡፡

 

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.