የስነ-ምግባር መልካም አስተዳደርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት

የስነ-ምግባር መልካም አስተዳደርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የስነ-ምግባር፣ መልካም አስተዳደርና ጸረ-ሙስናዳይሬክቶሬትተጠሪነቱ ለጽ/ቤቱ ኃላፊ ሆኖየሚከተሉትንተግባርናኃላፊነትይኖሩታል፡-

  • በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሥነ ምግባር ደንቦች እና የፀረ ሙስና ሕጎች መከበራቸውን ይከታተላል፣ ስለ አፈፃፀማቸውም የመሥሪያ ቤቱን የበላይ ኃላፊ ያማክራል፤
  • በተቋሙ ሀብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ ሕግ የጣለባቸውን የመሥሪያ ቤቱን ሠራተኞች ሀብትና የገንዘብ ጥቅሞች መዝግቦ ለሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ለኮሚሽን ያስተላልፋል፤
  • ለሙስና ቀዳዳ የሚከፍቱ የአሠራር ዘዴዎችን ለማስተካከል /ለመድፈን/ የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችና ስልቶች እንዲጠኑ አማራጭ ሃሳቦችን ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፣ ሲወሰንም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
  • እንደ የመሥሪያ ቤቱ መርሃ ግብር /በሳምንት፣ በሁለት ሳምንት፣ በወር፣ በሩብ ዓመት፣ በመንፈቅ ዓመት/ በሚካሄዱ የእቅድ ግምገማዎች ወቅት በዳይሬክቶሬቶች ውስጥ በተከሰቱ የሥነ ምግባር ችግሮች ላይ ሠራተኛው ውይይት እንዲያደርግ ለመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ያሳስባል፣ ስለአተገባበሩም ክትትል ያደርጋል፤
  • በኢ-ሥነ ምግባራዊ ችግሮች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎችን ይከታተላል፣ሪኮርድ ይይዛል፣ ከርምጃው በኋላ ያለውን ሁኔታ ይገመግማል፣ ሪፖርትም ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፤
  • በተቋም የስነ ምግባር መርሆዎች ጉድለት የጥቆማ አሠራር ስርዓት ይዘረጋል የጥቆማ አቅራቢዎች ማንነት በሚስጥር ይይዛል፣ የጥቆማ መቀበያ ስርዓት እንዲዘረጋ ያገርጋል፤
  • አግባብ ያላቸው ሕጎችና የመንግሥት ሠራተኞች የሥነ ምግባር ደንብ በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ዘንድ ተገቢ ግንዛቤ አግኝተው በአግባቡ እንዲተገብሩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ተባብሮ ይሰራል፤
  • የመልካም የአስተዳደር መርሆዎች እንዲከበሩና የአገልግሎት አሠጣጥ ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢ ላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልክ እንዲስተካከል የመሥሪያ ቤቱን የበላይ ኃላፊ ያማክራል፤
  • የመንግሥት ባለሥልጣናት ወይም ሠራተኞች ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ በመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት ተጠቃሚ ሕብረተሰብ መካከል አድልዎ እንዳይፈፅሙ ይከታተላል፣ ተፈፅሞ ሲገኝ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሪፖርት ያደርጋል፤
  • በወርሃዊ ወይም ዓመታዊ መጽሔት ውስጥ መልካም ሥነምግባርን የሚያወድሱና የሙስና አስከፊነት የሚገልጹ መጣጥፎችና ጥናታዊ ጽሁፎች እንዲካተቱ ጥረት ያደርጋል፤
  • የሠራተኞች ቅጥሮች፣የደረጃ ዕድገቶች የኮንትራትና የግዥና ሽያጭ የጨረታ ውሎችና አፈፃፀማቸው ላይ የሥነምግባር ደንብ እንዳይጣስና የሙስና ወንጀል እንዳይፈፀም ይከታተላል፣ተፈጽሞ ሲያገኝም ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፈ ሪፖርት ያደረጋል፤
  • በየበጀት ዓመቱ ስለሚያከናውናቸው ተግባሮች ዕቅድ፣ መርሃግብርና በጀት አዘጋጅቶ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፣ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በወር፣በሩብ ዓመትና ዓመታዊ ያቀርባል፣
  • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዩች የሚሰጠዉ አገልገሎት አዋጆችን፤ ደንቦችንና መመሪያዎችን የተከተሉና የመልካም አስተዳደር መርሆችን የተከተሉ መሆናቸዉን ይከታተላል፣ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡

Main menu en-GB (2)

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.