የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ተጠሪነቱ ለኦፐሬሽን አገልግሎት ጄኔራል ዳይሬክተር ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
- የዘርፉ ዓላማዎች ለማስፈጸም የሚችል ዕቅድና በጀት ሲዘጋጅ ይሳተፋል፣ሲጸድቅም ይፈጽማል፣የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤
- የመ/ቤቱ ዓመታዊ ግቦች ለማስፈጸም የሚያስችል ግልጽና ከፊዚካል ዕቅድ ጋር የተጣጣመና የግዥ አፈጻጸም መመርያ መሠረት በማድረግ የተቋም ግዥ ዕቅድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ሲጸድቅም ይፈጽማል፤
- በየበጀት ዓመቱ የተፈቀደ የዕቃና አገልግሎት ግዥ በመንግስት በተፈቀደ የግዥ አፈጻጸም መመርያ መሠረት በግልጽነትና በተጠያቂነት ከሙስና በጸዳ መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
- የመ/ቤቱ የቋሚ ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ዘመናዊ የአሠራር ስርዓት የተከተለ መሆኑን ያረጋግጣል፤
- የተቋሙ ንብረቶች በአግባቡ ለተፈቀደለት ዓላማ ጥቅም ላይ መዋሉና የሚያስረዱ የንብረት አጠቃቀም ሪፖርቶችና መግለጫዎች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤
- በተቋሙ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር በሚመለከት የወጡ አዋጆች፣ደንቦችና የአሠራር መመርያዎች ስራ ላይ መዋላቸው ያረጋግጣል፤
- የዘርፉ ቋሚ ንብረቶች ተገቢው ጥበቃ የተደረገ መሆኑና ረዥም ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የአሠራር ስርዓት አጥንቶ ያቀርባል ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የንብረት አጠቃቀምና አያያዝ የፈጻሚ ሠራተኞችና ተጠቃሚዎች ግንዛቤ እንዲዳብር ክትትል ያደርጋል፣ይደግፋል፣
- በመ/ቤቱ አስፈላጊው የግዥ አፈጻጸምና የንብረት አያያዝ የሚያስረዱ ሰነዶች፣ካርዶችና መዛግብ መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፤
- የተቋም የግዥ አፈጻጸምና የንብረት አጠቃቀም በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋል የተገኘው ውጤት ለተቋሙ አመራር አካላት ያሣውቃል በኦዲት የተገኙ ግኝቶች ወዲያውኑ እንዲስተካከሉ ያደርጋል፤
- በስራ ሂደቱ በየደረጃ ያሉትን ፈጻሚዎች የመልካም አስተዳደርና የስነ ምግባር መርሆዎች አክብረው አገልግሎት እንዲሰጡ ይከታተላል፣ይደግፈል፤
- በዳይሬክቶሬቱ ያሉት ፈጻሚዎች የስራ አፈጻጸማቸው ለማሻሻል የሚረዱ ስልጠናዎች እንዲያገኙ በመንግስት የስልጠና አፈጻጸም መመርያ መሠረት ያቅዳል፣ ሲፈቀድም ይፈጽማል፤