የእንስሳት ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት

የእንስሳትሀብትልማትዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት

የእንስሳትሀብትልማትውጤታማነትናቀጣይነትየሚረዱፖሊሲዎችን፣ስትራቴጂዎችን፣አዋጆችን፣ደንቦችን፣መመሪያዎችንእንዲሁምአግባብነትያላቸዉየፈጻሚተቋማትማቋቋሚያሐሳብያመነጫል፣ይቀርጻል፣ሲፀድቅምአፈጻጸማቸውንይከታተላል፡፡የእንስሳትሀብትልማትኘሮጀክቶችን፣ኘሮግራሞችንናዕቅዶችንያዘጋጃል፡፡ዘመናዊየእንስሳትእርባታናልማትቴክኖሎጂዎችንበማፅረስለአርብቶአደሩናከፊልአርብቶአደሩህብረተሰብበአግባቡእንዲዳረስያደርጋል፡፡የወተት፣የሥጋቆዳናሌጦ፣የዶሮ፣የዓሳናየማርናሀርልማትናምርትእንዲሁምአጠቃላይየእንስሳትሀብታችንበብዛትምሆነበጥራትእንዲለማናለሀገራችንየኢኮኖሚዕድገትወሳኝሚናእንዲጫወትይሠራል፡፡በከተሞችለሚካሄደውየእንስሳትሀብትልማትሥራላይከፍተኛትኩረትበመስጠትየወተት፣የዶሮሥጋናየዕንቁላልምርትእንዲስፋፉናእንዲጠናከርብሎምየተጠቃሚውንፍላጎትበብዛትናበጥራትእንዲያሟላያደርጋል፣

የእንስሳትሀብትልማትዳይሬክቶሬትተጠሪነቱለእንስሳትሀብትዘርፍሚኒስትር ዴኤታ ሆኖየሚከተሉትተግባራትናኃላፊነቶችይኖሩታል፡-

  • የእንስሳት ሀብት ልማት ውጤታማነትና ቀጣይነት የሚረዱ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣መመሪያዎችን እንዲሁም አግባቢነት ያላቸዉ የፈጻሚ ተቋማት ማቋቋሚያ ሐሳብ ያመነጫል፣ ይቀርጻል፣ ሲፀድቅም አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣
  • አዳዲስ ሀገር አቀፍ የእንስሳት ሀብት ልማት ኘሮጀክቶችን፣ ኘሮግራሞችንና ዕቅዶችን ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ቴክኒካዊ እገዛ ይሰጣል፤
  • ለእንስሳት ሀብት ምርትና ምርታማነት ዕድገትና ቀጣይነት የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማሰባሰብና በማጠናቀር አዳዲስ የኤክስትንሽን ፓኬጆችን በመቅረፅ እንዲተገበሩ ያደርጋል፡፡
  • የእንስሳት ሀብት ልማት ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ስልጠናዎችንና ልምድ ልውውጦችን አዘጋጅቶ ለክልል/ዞን ባለሙያዎች ይሰጣል፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል
  • በአርሶ/አርብቶ አደሩ ልዩ አቅምና ባህርይ ላይ የሚያተኩር የእንስሳት ሀብት ልማት ስትራቴጂያዊ አካባቢዎች በአሳታፊ ሁኔታ ለማቋቋም የአጭር፣የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
  • ለጥሬ ወተት ምርት አሰባሰብ፣ ክምችት፣አጓጓዝና አያያዝ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋትና በማሰራጨት የማምረት፣የግብይትና የአጠቃቀም አቅም ለማጎልበት እንዲቻል ለባለሀብቱ፣ ለአርሶ እና አርብቶ አደሩና ባለሙያዎች የዕውቀትና ክህሎት ማበልፀጊያ ሥልጠና እንዲጠናከር ያደርጋል፣ የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ የሰጣል፣
  • ለወተት ምርት ጥራት አጠባበቅና ቁጥጥር የሚያግዝ የጥራት ደረጃዎች እንዲዘጋጁና ሥራ ላይ እንዲዉሉ አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት ጋር በመሆን ይሠራል፣
  • ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለወጪ ንግድ የሚውል የቁም እንስሳት እንዲሁም የሥጋ ምርት አቅርቦትን በቀጣይነት ለማሳደግ እንዲቻል ሰፋፊ የሥጋ እንስሳት ዕርባታ ጣቢያዎች ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ከሚመለከታቸዉ ጋር ተስማሚ ስትራቴጂና አሠራር ይቀይሳል፣ሲፀድቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ውጤቱንም ይገመግማል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የእንሰሳት አርቢው ህብረተሰብ በሥጋ እንስሳት ክብካቤና አያያዝ ላይ የተሻለ ግንዛቤና ክህሎት በመገንባት የሥጋ ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ፣በቂና አስተማማኝ የቁም እንስሳት፣ሥጋ፣ቆዳና ሌጦ ለኢንዱስተሪ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት እንዲሻሻል፣የሀገራችን የወጪ ሥጋ ንግድና የውጪ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ መሠረታዊ የአመራረትና የአሠራር ለውጥ (ትራስፎርሜሽን) የሚካሄድበትን ስልት ይነድፋል፣
  • ለቁም የሥጋ እንስሳትና የሥጋ ጥሬ ምርት ጥራት ብሔራዊ ደረጃዎችንና የብራንዲንግ ሥርዓት እንዲዘጋጅ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ይሠራል፣ሲጸድቅም ሥራ ላይ እንዲዉሉ ከቁጥጥር ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሠራል፣
  • የእንስሳት ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት፣ አያያዝና አስተዳደር ለማሻሻል ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋትና በማሰራጨት የማምረት አቅም ለማጎልበት እንዲቻል በዘርፉ ለተሠማሩ ባለሀብቶች፣አርሶ እና አርብቶ አደሮችች አና ባለሙያዎች የዕቀትና ክህሎት ማበልፀጊያ ሥልጠና እንዲጠናከር ያደርጋል፣ የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፣
  • የዶሮ ሀብት ልማት ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ ለተጠቃሚዎች ያስተዋውቃል፣ያሰራጫል፣ውጤታማነታቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የማሻሻያ ሀሳብ ያቀርባል፣
  • የእንስሳት ሀብት ልማት ላይ ለባለሀብቱ፣ ለአርሶና አርብቶና ከፊለል አርብቶ አደር፣ለተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች፣ለባለሙያዎች የዕውቀትና ክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠና እንዲዘጋጅና እንዲሰጥ ያደርጋል፣የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፣
  • ምርምር የሚሹ የእንስሳት ሀብት ልማት ሥራዎችን በመለየት ሳይንሳዊ ምርምርና የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያገኙ አግባብነት ካላቸው የምርምር ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር ይሠራል፣
  • የሀገሪቱ የውኃ አካላት ሐይቆች፣ ግድቦች አና ወንዞች የዓሳ ሀብት ክምችት ዓይነት፣ መጠንና ስርጭት እንዲሁም ተሳትፏዊ የዓሳ ሀብት ማኔጅመንት ሥርዓት ከክልሎች ጋር በጥናት ይለያል፣ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣
  • የዓሳ ዘር ብዜትና ሥርጭት ማዕከላት በተስማሚ ሥነ-ምህዳሮች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ የዓሣ ዘር አቅርቦት አስተማማኝ ሥርጭቱንም ይከታተላል፣ ዉጤቱንም ይገመግማል፣
  • በዓሳ እምቅ ሀብት አስተዳደር፣በዕርባታ፣ማስገሪያ መሣሪያዎችና በድህረ ምርት ቴክኖሎጂ ላይ ምርምር የሚያስፈልጋቸው መስኮችን በመለየት ሳይንሳዊ ምርምር እንዲካሄድባቸው ከሚመለከታቸው አካላት ያቅዳል፣ ተግባሩንና ዉጤቱንም ይገመግማል፣
  • የዓሳ ምርት በዝግጅት፣ክምችት፣አያያዝ፣አጓጓዝና በሽያጭ ሂደት ላይ ጥራትና ደህንነቱ ተጠብቆ ለተጠቃሚ እንዲደርስ የሚያስችል ደንብና መመሪያ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
  • የዓሳ ምርት አያያዝና አመጋገብ በህብረተሰቡ ዘንድ የተሸለ ልምድና ባህል እንዲዳብር ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሥነ-ምግብ ሥልጠናና ኤክስቴንሽ አገልግሎት እንዲስፋፋ ያድርጋል፣ ዉጤቱንም ይገመግማል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • ለማርና ሐር ሀብት ልማት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ ለተጠቃሚዎች ያስተዋውቃል፣ ያሰራጫል፣ ውጤታማነታቸውን በመገምገም እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ለተለያዩ የማርና ሐር ልማት ግብዓቶችና ምርት ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲመረቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ደረጃዎችን ያዘጋጃል፣
  • ለየሥነ-ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው ተስማሚ የሆኑ የማርና ሐር ቴክኖሎጂ ፓኬጆችን በማጠናቀር ለክልል ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ይሰጣል፣አፈፃፀማቸውን በመከታተል እንዲሻሻሉ ያደርጋል፣ ቴክኒካዊ እገዛ ይሰጣል፣
  • የማርና ሐር ልማት ቴክኖሎጂ ስርጭትን ውጤታማና ተደራሽ ማድረግ እንዲቻል በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የኤክስቴንሽን የልማት ቡድኖችን ያደራጃል፣ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፣ ክትትል ያደርጋል፣
  • ለውጪም ሆነ ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚቀርብ የማርና ሐር ምርቶችን በብዛትና በጥራት እንዲመረቱ የአውት ግሮወርስ የአሠራር ሥርዓት ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
  • በእንስሳት ሀብት ልማት ለተሠማሩ ባለሀብቶች፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦች ዕውቀትና ክህሎት ለማጎልበት የሚረዱ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች፣የአጭርና ረጅም ጊዜ ትምህርት እንዲስፋፉ የተሻለ አሠራር ይቀይሳል፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
  • የእንስሳት ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት በተዘረጋው የአሰራር ሥርዓት መሰረት ሥራዎች መከናወናቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜው እየገመገመ እንዲሻሻል ያደርጋል፣አፈጻፀሙንም ይከታተላል፣የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ለበላይ አካል ያቀርባል፡፡
  • የእንስሳት ሀብት ልማት አጠቃላይ ሥራዎችን አፈጻፀም ይከታተላል፣ይገመግማል፣የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ለበላይ አካል ያቀርባል፡፡

Main menu en-GB (2)

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.