የኦዲትና እንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት
የኦዲትና እንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
የኦዲትና እንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
- የተቋሙ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት የሚያረጋግጥ የረዥም፣የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የውስጥ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ሲፈቀድም ይተገብራል፣
- ከዘርፉ ዓላማ አንጻር ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት በመለየት የስጋት ተጋላጭነት ያላቸው የመ/ቤቱ የስራ ሂደቶች መሠረት ያደረገ የኦዲት የስራ ትዕዛዝና ሃሣብ መሠረት ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣
- መደበኛ የውስጥ ኦዲትና ኢንስፔክስን ምርመራ ተግባራት ኦዲት ተደራጊ የስራ ሂደቶችና ተጠሪ ተቋማት በቅድሚያ እንዲያውቁት ያደርጋል፣
- የተቋሙ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ለማጠናከር የሚያችል ዘዴ ያለውን አሠራር በመፈተሸ እንዲሻሻል ያቀርባል፣ሲፈቀደም አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
- ለመ/ቤቱ ዓላማ ማስፈጸሚያ የተፈቀደው ሀብት በከፍተኛ ቁጠባና ውጤታማነት መንገድ ከግብ ለማድረስ ስለመቻሉን በምርመራ ያረጋግጣል፣
- በተቋሙ የመንግስት የፋይናንስ፣የግዥና ንብረት፣የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር ህጎች፣ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸው በምርመራ ያረጋግጣል፣
- በተቋሙ የሰው ሀብት አያያዝና ስምሪት ህግና የአሠራር መመርያዎች የተከተለ ስለመሆኑ በኢንስፔክሽን ምርመራ ያረጋግጣል፣
- በመ/ቤቱ የሚዘጋጁ የስራ አፈጻጸም እና ፋይናንስ ሪፖርቶችና መግለጫዎች በምርመራ ትክክለኛነታቸው ያረጋግጣል፣የስራ አፈጻጸም የሚሻሽሉ አስተያየቶች ያቀርባል፣ሲጸድቅም አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
- በምርመራ ወቅት በኦዲት መጀመርያ እና በኦዲት ማጠናቀቅያ ከኦዲት ተደራጊ የስራ ሂደቶችና ተጠሪ ተቋማት ስብሰባ ያደርጋል፤
- የውስጥ ኦዲተሮች በምርመራ ወቅት የኦዲት የሙያ ስነ ምግባር መሠረት በማድረግ ምርመራ ማድረጋቸውንና ሪፖርት ማቅረባቸው ያረጋግጣል፤
- በውጭ ኦዲተሮች የሚቀርቡ የተቋሙ የምርመራ ግኝቶች በወቅቱ እንዲስተካከሉ ክትትል ድጋፍ ያደርጋል፣የኦዲተሮች አቅም በዕውቀት፣በክህሎትና በተፈላጊ ችሎታ ለማሣደግ የሚያስችል የስልጠና ዕቅድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ሲፈቀድ ይፈጽማል፤
ከላይ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት የተገለፀ ቢሆንም የሰው ኃይል ብዛት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሚወሰን በመሆኑ በዚህ ዶክመንት አላካተትንም፡፡