የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የኦፕሬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ሆኖ የፌደራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን የወልና የተናጥል ሥልጣንና ተግባራት ከሌሎች የሀገሪቱ ሕጎችና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር ተጣጥሞ ሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ የሚከተሉትን አብይ እና ቁልፍ ተግባራት ያከናውናል፡፡
- የህግ አገልግሎቱን ሥራዎች ያቅዳል፣ያደራጃል፣ይመራል፣ያስተባብራል፣
- የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ቁሳቁስና በጀት እንዲሟላ ያደርጋል፣ያስተዳድራል፣በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፤
- በዳይሬክቶሬቱ ያለውን አደረጃጀት ተጠቅሞ ሥራዎችን ከፋፍሎ ይሰጣል፣ ይደግፋል፣ አፈጻጸማቸው ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
- ለዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታ ይፈጥራል፣ ያላቸውን የአቅም ክፍተት በመለየት የሚሞላበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
- የዳይሬክቶሬቱንሥራ አፈጻጸም ውጤታማነት ይገመግማል፣
- የመንግስት ሠራተኛ አዋጅ ደንቦችንና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውንና መከበራቸውን ያረጋግጣል፣
- የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ የፖሊሲ ግብን ወይም የሚፈለገውን ውጤት ለማሳካት ካሉት አማራጮች ሕግ መውጣቱ የተሸለ አማራጭ መሆኑን ውሳኔ ባሳለፈባቸው ጉዳዮች ላይ የሚመለከተው ዘርፍ በቅድሚያ የተፅዕኖ ግምገማ ማድረጉን ያረጋግጣል በሂደቱ ይሳተፋል፤
- መሥሪያ ቤቱን በሚመለከት የፖሊሲ ግብ ወይም የሚፈለገውን ውጤት ለማሳካት የሚያስችሉ ጉዳዮች መሆናቸውን በመለየት በጥናት ላይ የተደገፈ የማሻሻያ ሃሳቦችን ያመነጫል በኃላፊ ሲወሰንም ሕግ እንዲወጣ ያደርጋል፤
- በቀጥታም ይሁን በትብብር በሚዘጋጁ ረቂቅ የሕግ ረቂቅ ዝግጅት ላይ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል ተቋሙ በባለቤትነት የሚያስፈፅማቸውን የሕግ ረቂቅ ሰነዶች አስኪ ፀድቁ ድረስም ክትትል ያደርጋል የፀደቁትን ያሰራጫል ወይም መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል፤
- በመሥሪያ ቤቱ ተግባራዊ የሚደረጉ አዋጆች ደንቦች መመሪያዎችና በህግ ሥልጣን ባለው አካል የሚሰጡ መመሪያዎች ትዕዛዞች በሥራ ላይ መዋላቸውን ወይም እንዲፈፀሙ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- የፖሊሲ ግብን ወይም የሚፈለገውን ውጤት ለማሳካት ሲባል ሕግ እንዲወጣ ከተወሰነ በኋላ ወይም በህግ የማስፈፀሚያ ደንብና መመሪያ እንዲዘጋጅ ይፋ በተደረጉባቸው ጉዳዮች ላይ ደንብና መመሪያ እንዲወጣ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- በሀገር አቀፍ ደረጃ ከህግ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥናትና ውይይቶች ላይ በመሳተፍ ግብዓት ይሰጣል፣መሥሪያ ቤቱን በሚመለከቱ የህግ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል፤
- የመሥሪያ ቤቱን የህግ አገልግሎት ሥራዎች አፈጻጸም ለማሻሻል የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮዎች የሚገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- መሥሪያ ቤቱን የሚመለከቱ ሕጎች፣የውል ስምምነቶችና የመግባቢያ ሰነዶች ሌሎች ህግ ነክ ሠነዶችን መተርጎም ሲያስፈልግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትብብር ይሰራል፤
- መሥሪያ ቤቱ ከሌላ ወገን ጋር የሚያደርጋቸው ድርድሮችና ስምምነቶች የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቁና ውጤታማ እንዲሆኑ የህግ ድጋፍ ይሰጣል፤
- የሚዘጋጁ የድርድር ነጥቦችን የስምምነት ሠነዶች ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣የስምምነቱን አፈጻጸም ይከታተላል፣አለመግባባቶች ሲኖሩ በሕግ መሠረት እንዲፈቱ ያደርጋል፤
- ከተቋሙ ኃላፊ በሚሰጥ ውክልና መሠረትም መሥሪያ ቤቱን ወክሎ ከሌሎች መሥሪያ ቤቶች ወይም ድርጅቶች ጋር ይደራደራል፣ይወያያል፤መሥሪያ ቤቱን የሚመለከቱ የፍርድ ቤት ጉዳዮች የህግን አግባብ ተከትለው ተገቢውን ውሳኔ እንዲያገኙ ክስ ይመሰርታል ወይም የመከላከያ መልስና ተዛማጅ ተግባሮችን በማከናወን ይከታተላል፣ያስፈጽማል፤
- መሥሪያ ቤቱን በሚመለከት በሚነሱ የህግ ጉዳዮችና ጥያቄዎች ላይ ተገቢውን ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣል፤
- መሥሪያ ቤቱን በሚመለከቱ ህግ ጉዳዮች ላይ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ሥራውን በትብብር ያከናውናል፤
- ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮችና ለየሥራ ዘርፎች በህግ ነክ ጉዳዮች ላይ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡