የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚኒኬሽን ፤ዳይሬቶሬት
የህዝብ ግንኙነትና ክሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት
በተቀናጁየድርጅታዊግንኙነቶችንንድፍእናየህዝብግንኙነትዕቅድ፣ስትራቴጂእናፕሮግራሞችንዲዛይንናትግበራበብቃትእየምራ ዘላቂየድርጅታዊማንነትእናምስልመገንባት።የህዝብግንኙነትእናየኮሚኒኬሽንዳይሬክተር፤ ተጠሪነቱየፖሊሲ፣ ፕሮግራሞች እና ግንኙነቶች ጄኔራል ዳይሬክተር ክፍልሆኖየሚከተሉትተግባራትናኃላፊነትአለው፡-
- የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ይህዝብ ግንኙነትና ስርዐተ ተግባቦት (communication) ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስትራቴጂና አላማ ጋር በተስማማ መንገድ ለመከወን የሚያስችል ስትራቴጂ ፡ ዕቅድና መርሃ ግብር ዝግጅትና ትግበራ ይመራል፤
- የህዝብ ግንኙነትና የተግባቦተ ስርዐት ክዋኔ ፖሊሲ ፡ ደንብና መርህ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በምልዕክቶቹ ሊደርስ የሚፈልጋቸውን ባለድርሻ አካላት መለየት ፡ የመልዕክት አይነቶችና ይዘቶችን መለየትና እንዳግባቡም አስፈላጊውን ምልዕክቶች ያዘጋጃል፤
- ሕዝባዊ ፕሮግራሞችን ፣ ዝግጅቶችን የሚያካትቱ የተቀናጁ የህዝብ ግንኙነት ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እና መተግበር እና ውጤታማነታቸውን ይከታተላል፤
- የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ከፕሬስ ፣ አጋሮች ፣ መንግሥት ፣ ኢንዱስትሪ ፣ ማህበረሰብ ወዘተ ጋር ያለውን የግኙነት ፍሰትና ዘዴን ያቀናጃል፤
- የግንኙነቶች እና የህዝብ ግንኙነት መርሃ ግብሮችንያስተባብራል፤
- በማህበራዊ ሚዲያ ሰርጦች አማካይነት ህዝብ ተኮር ሚዲያ ስትራቴጂዎችን እና ፖሊሲዎችን ያዘጋጃል፤
- በመስመር ላይ እና በመስመር ውጭ ያሉ የግንኙነት ጎዳናዎችን (ዲዛይን)መቅረጽ እና ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ጋዜጣዊ መግለጫዎች ፣ የሚዲያ ግንኙነቶች ፣ እና የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች እና የንግግር ፕሮፖዛል ይመራል፣ ያቀርባል፤
- የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የህዝብ ግንኙነት እና የግንኙነት ውጤታማነት እና ቅልጥፍናን ይከታተላል፣ያሻሸላል፤
- የሥራ አፈጻጸሙን በመደበኛነት በሕዝባዊ ግንኙነቶች ላይ ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፤
- አስፈላጊ የሆኑ የውስጥ ግንኙነቶችን (ከሰራተኛ ከአመራር ጋር ወዘተ) መለየት ፣ የውስጥ የግንኙነት መልዕክቶችን ያዘጋጃል፣ያስተላልፋል፣ያሰራጫል፤
- የሠራተኛ መሰጠትና ተሳታፊነትን የሚያሳድጉ የውስጣዊ መልዕክቶችን ዝግጅትና አፈፃፀም ይመራል፤
- ለሰራተኞች መረጃ መስጠት እና የሚኒስቴሩን ተልእኮ፣ እስትራቴጂ፣ ፖሊሲዎች እና አፈፃፀም መረጃዎቸን ያረጋግጣል፤
- የሚኒስቴሩን ቤተ-መጽሐፍትና እና የሰነድ አያያዝ አገልግሎቶችን አፈፃፀም ይቆጣጠራል፤
- የውስጥ እና የውጭ ግንኙነቶችን አፈፃፀም ይቆጣጠራል፣ ውጤታማነቱን ያረጋግጣል፤