ስነ-ህይወታዊ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
ስነ-ህይወታዊግብዓትአቅርቦትዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት
ስነ-ህይወታዊ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤
- ተገቢ ስነ-ህይወታዊ ግብአቶችን ፍላጎትና የግዠ ምንጮችን የመለየት አሰራርና እቅድን ፣ፖሊሲንና አሰራርን መፈተሸና ተግባራዊነታቸውን ይመለከታል፤
- ስነ-ህይወታዊ የግብአት አቅርቦት አሰራርን ከጠቅላላው የግበዓት አቅርቦት ሰርዓት አንጻር እቅድ ማውጣት ስራን ይመራል፤
- በግዠ ምንጮች ፣ በመጋዘኖች፣ እና በስርጭት ፖሊሲ ፣ አሰራር እቅድና አተገባበርን ይመራል፤
- የስነ-ህይወታዊ ግብአት አቀራረብና ከአቅራቢዎች ጋር የሚኖርን ኮንትራቶችን ስራ ይመራል፤
- የስነ-ህይወታዊ ግብአት አቅርቦት መልካም ተሞክሮዎችን በማውጣት ፣የተሻለ የዋጋ አቅርቦትና የቆሻሻ አወጋገድን ይተገብራል፤
- የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለመተግበርና ለመደገፍ ፣ እና የንግድ ፍትሀዊነትን ይመርጣል፤
- የግብርና ግብይት ለማስፋፋት እና የግብዓት አቅርቦት አሰራርን ፖሊሲዎች፣ ስልት፣ አሰራር ፣ ፕሮግራምና ሂደቶችን ቀረጻና ትግበራ ይመራል፤
- የጎለበተና የማይናውጥ የግዢ ቦታዎችን ፣ ግዢዎችን፣ የቆጠራ ቁጥጥሮችን ፣ መጋዘኖችንና የአቅርቦትና የስርጭት ስራዎችን ይመራል፤
- ተፋሰስ ልማት በሚካሄድበት አከባቢ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃና ችግሮችን ለመፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መነሻ የሚሁኑ መረጃዎችን ይሰበስባል ይለያል፤
- የተሰበሰቡ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት መረጃዎችን የማደራጀት፣ ለዘመናዊ መረጃ ቋትና ፣ለዕቅድ ዝግጀት ያመቻቻል፣
- የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ሥራ በአከባቢው ያለበትን ደረጃና የህበረተሰቡን ልማዳዊ አሠራር በመለየት የተሰበሰቡ መረጃዎጨችን መሰረት በማድረግ ቀላል ትንታኔ ይሰጣል፣ በአግባቡ ያደራጃል፣
- በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ የውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰብሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ያደርጋል፤
- የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት በተመለከተ ለሚዘጋጁ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ ህጎች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች መረጃዎችን ያሰባስባል፤
- የስነ-ህይወታዊ ግብአት በሚመለከት በተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ መሰረት ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ይሰጣል የሚሰጥበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- በተፋሰስ ልማት የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት ሥራዎች ለማስፋፋት የተቀመሩ አዳዲሰና የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችና መመሪያዎችን ያሰራጫል ፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
- በተፋሰስ ልማት ተግባራዊ የሚደረጉ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ሥራዎች በተዘጋጀው ዕቅድና መመሪያ መሰረት እንዲከናውኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ይከታተላል፤
- የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የስነ-ህይወታዊ ግብአት ልማት በተዘጋጀው የአሰራር ማኑዋል መሠረት እንዲተገበሩ ድጋፍ ያደርጋል ፣ መከናወናቸውንም ውጤታማነታቸውን ይከታተላል ሪፖርት ያደርጋል፤
- በብዜት ስለሚቀርቡ የስነ ህይወታዊ ግብዓት አቅርቦት አሰራር እቅድና አተገባበርን ይመራል፤
- የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የገጠር ፋይናንስ አገልግሎቶችን ስርዓት ለማሻሻል፣የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት፣ጥናቶችን በማድረግ፣ስልጠናዎችን በመስጠት፣ በመከታተልና በመደገፍና በአቅራቢዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ትስስር እንዲኖር በማድረግ ማህበረሰቡን የፋይናንስ ተጠቃሚነቱን ያረጋግጣል ፡፡