የኤክስፖርት ቄራዎች ኢንስፔክሽንና ሠርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት
የኤክስፖርትቄራዎችኢንስፔክሽንናሰርተፊኬሽንዳይሬክቶሬትተግባርናኃላፊነት
የኤክስፖርት ቄራዎች ኢንስፔክሽንና ሠርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለእንስሳት ሃብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
- የሥጋ ምርመራ አገልግሎትን አስመልክቶ አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም ተፋጻሚነቱንም ይከታተላል፣
- ስለ ሥጋ ምርመራ አዳዲስ ዓለም አቀፍ አሠራሮችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ በኤክስፖርት ቆራዎችም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ባሉ ቆራዎች ለሚሠሩ ባለሙያዎች ያስተዋውቃል፣
- በኤክስፖርት ቄራ ግንባታና በሥጋ ምርት የወጪ ንግድ ሥራ ላይ ለመሰመራት ጥያቄ ለሚያቀርቡ ባለሀብቶች የማማከር ሙያው ድጋፍ ይሰጣል፣ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ለግንባታ የሚመረጠውን ሥፍራ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣
- በኤክስፖርት ቄራዎች ውስጥ የሚሠጠው የቅድመ ዕርድ እና የድህረ ዕርድ የምርመራ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፣
- ለውጪ ሀገር ገበያ በሚቀርብ የሥጋ ምርት ላይ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለው የሥጋ ምርመራና የሠርተፊኬሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፣
- በሥጋና በሥጋ ውጤቶች አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የወጡ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ደንቦችንና ስምምነቶችን ያስከብራል፣
- የእንሰሳት ማጓጓዣ ተሸከርካሪ ለእንሰሳት ማጓጓዣ ምቹና ፅዱ መሆናቸውን ይቆጣጠራል፣
- በኤክስፖርት ቄራዎችና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ውስጥ የንፅህና አሠራርን መመሪያ (Standard Sanitation Operation Procedures) ያዘጋጃል ትግባራዊ ያደርጋል፣
- በኤክስፖርት ቄራዎች ውስጥ ለሚሠሩ ሠራተኞችና ባለሀብቶች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ይሰጣል፣
- ለኤክስፖርት ተመርቶ የተዘጋጀ የሥጋ ምርትና ውጤት በተገቢው ንፅህናና ቅዝቃዜ ወደ ኤርፖርት መጓጓዙን ይቆጣጠራል፣ዓለም አቀፍ የጤና ሠርተፊኬት በመስጠት ይሸኛል፣
- ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን በሥጋ ምርት የወጪ ንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶችና የቄራ ሠራተኞች በየጊዜው የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣
- የሥጋ ምርመራ አገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናል፣መልካም ተሞክሮዎችን ይቀስማል ተግባራዊም ያደርጋል፣ከሥጋ ምርት ተቀባይ ሀገሮች የሚቀርቡ ግብረ መልሶችን መሠረት በማድረግ የማሻሻያ እርምጃዎችን ይወስዳል፣
- ለእንስሳት በሽታዎች የመረጃ አሰባሰብ ሥራ አጋዥ የሆኑ የሥጋ ምርመራ ሪፖርቶችን ከኤክስፖርት ቄራዎች ያሰባስባል፣ለሀገራዊ የመረጃ ቋት ሪፖርት ያደርጋል፣
- ከሥጋ ምርመራ አገልግሎት የሚሰበሰቡ ገቢዎች በአግባቡ ወደ መንግሥት ካዝና ገቢ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ያስፈፅማል፣