የእንስሳት ጤናና ቬተሪናሪ ፐብሊክ ሄልዝ መሪ ሥራ
የእንስሳትና ዓሳ ልማት ኤክስቴንሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለእንስሳትና ዓሳ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ያከናውናል፡-
- በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ መሠረት የጥምር ግብርና እንስሳትና ዓሳ ልማትና ጤና ኤክስቴንሽንን ለማስፋፋት የሚያስችሉት የፖሊሲ የስትራቴጂና የአሰራር ስርዓቶች እንዲመነጩ፣ እንዲቀረፁና ተግባራዊ እንዲሆኑ በስሩ የሚገኙትን ዳይሬክቶሬቶችን ያስተባብራል፣ ይመራል፤
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍን ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፤ለአርብቶ አደሩ፤ለግል ባለሀብቱና በከተማ እንስሳት ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
- ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በማስቀረፅ ወደ ስራ እንዲገቡ አመራር ይሰጣል፣ ያስተባብራል፤
- በስሩ ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች አስፈላጊው ግብዓቶችና ፋሲሊቲዎች እንዲሟሉ ያደርጋል፤
- የጥምር ግብርና እንስሳትና ዓሳ ልማትና ጤና ኤክስቴንሽንን በሚመለከቱ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ለሚኒስቴር ዴኤታው የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
- ለቴክኖሎጂ ሽግግር አጋዥ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፓኬጆች ለስነምህዳሩ እና ለተጠቃሚው የሚስማማ ሆኖ መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የማሻሻያ ሀሳቦችን በማካተት እንዲዳብር ያደርጋል፤
- ለኤክስቴንሽን ስርጭት የሚውሉ የመልክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች ደረጃቸውንና ጥራታቸውን ጠብቀው ለተጠቃሚው በሚመች መንገድ እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ ያደርጋል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ቴክኒካዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በየደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚና ፈፃሚ አካላት አቅምን ለማጎልበት እንዲቻል በፌዴራልና በክልል/ዞን ተገቢው ስልጠና እንዲዘጋጅ በማድረግ የአቅም ግንባታ ስራዎች እንዲካሄዱ ድጋፍ ይሰጣል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤
- የኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥንና የቴክኖሎጂ ስርጭትን ቀላልና ውጤታማ ለማድረግ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የኤክስቴንሽን የልማት ቡድኖች ሴቶች እና ወጣቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ የሚደረጁበትን ስልትና ስትራቴጂ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲደራጁ ያደርጋል፣ ተግባር ላይ እንዲዉሉ ይከታተላል፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- ልማቱ ውጤትን መሰረት በማድረግ ከጤናው፣ ከግብዓት፣ ከመኖ፣ ከዝርያ ማሻሻል፣ ከግብይቱና ሌሎች እሴት ሰንሰለቶችን ባስተሳሰረና በተናበበ መልኩ መቀናጀቱን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- የሴክተሩን ባለሙያና የልማቱ ተዋናይ አካለትን የክህሎት ክፍተት በመለየት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፣ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ተግባራዊነቱንም ይገመግማል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፤