የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ
የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስትሩ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍን ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፤ለአርብቶ አደሩ፤ለግል ባለሀብቱና በእንስሳት ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማትን የሚያፋጥን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ደርጋል፣ ይመራል፤
- ሀገራዊ የእንስሳት ዘረመል ሀብት እንዲለይ፤እንዲመረጥ፤እንዲሻሻል፤ጥቅም ላይ እንዲውልና እንዲጠበቅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይመራል፣ ይከታተላል፤
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ምርምሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ሲፀድቅም እንዲተገበር ያደርጋል፣ ይመራል፤
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት እና የአየር ንብረት ለዉጥ መቋቋሚያ አሬንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ የስልጠና ማዕከላት/የልህቀት ተቋማትን እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ ይመራል፤
- ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ኢንቨስትመንት የሚውል የመሬት አቅርቦት እንዲኖር፤ አጋዥ የሆኑ የፋይናንስ፤የመድን ዋስትና እንዲሁም የብድር አቅርቦት ሥርዓት እንዲጎለብት አግባብ ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራል፤
- የተፈጥሮ ግጦሽና በመስኖ የሚካሄድ የመኖ ልማት፣ የደረቅና ዕርጥብ መኖ ባንኮችን ያስፋፋል፣ የሚገኘውን ጠቀሜታ ይገመግማል፣ግብረመልስ ይሰጣል፣
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ተገቢውን የጤና አገልግሎት ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፣ መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ኤክስቴንሽን ለአርቢው እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- በየግብርና ለሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠሩ ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፣ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይመራል፤
- ለእንስሳት ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱትን የእንስሳት ዝርያና የመኖ ዕፅዋት ዘር ብዜትና ሥርጭት ተቋማትን የማቋቋሚያ ሐሳብ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ይተገብራል፤