የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለእርሻ እና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ያከናውናል፡-

  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን ሥራ ያቅዳል፤ ይመራል፤ ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ለፖሊሲ ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ አዳዲስ ሃሳቦችን ያመነጫል፤ በተቋሙ የፖሊሲ ዝግጅትና የሥራ እቅድ ዝግጅትና ክለሳ ላይ ይሳተፋል፣
  • ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የብዙ ተዋንያን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ሥርዓትን ይቀርጻል፣ ያስተዋውቃል፣ በተመረጡ ወረዳዎችም የፓይለት ሥራ እንዲሰራ ያደርጋል፣
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የግብርና ኤክስቴንሽን ሥርዓት በማጥናትና በመገምገም ፖሊሲ ያዘጋጃል፣ የኤክስቴንሽን ሥርዓት ይቀርጻል፣ ፍኖተ ካርታዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና የአፈጻጸም መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣
  • የኤክስቴንሽን ሥርዓቱን ውጤታማ የሚያደርጉ የህግ ማዕቀፎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና የአፈጻጸም መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ ያስተዋውቃል፣ አፈጻጸሙን ያስተዋውቃል፣
  • የሰብል፣ የሆርቲካልቸር፣ የግብርና ሜካናይዜሽንና የመስኖ ልማት ፓኬጅ ዝግጅት እና ክለሳ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
  • በዲጂታል ኤክስቴንሽና የምክር አገልግሎት ዙሪያ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላትንና ቴክኖሎጂዎችን ይለያል፣ የሀብትና የጉልበት ድግግሞሽ እንዳይኖር በቴክኖሎጂዎችና አሰራሮች ዙሪያ የማጣጣም ሥራዎችን ይሰራል፣
  • በእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሥር ለሚገኙ ቡድኖች ሥራን ያከፋፍላል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ የማሰተካከያ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚመራበትን የሥራ መርሃ ግብ ያዘጋጃል፤የጥናት ውጤቶችን መሠረት በማድረግ የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፤ የነበረውን ያሻሽላል፤
  • የመስኖ ኤክስቴንሽን ኤክስቴንሽን አገልግሎት ውጤታማነት በተመለከተ ይገመግማል፣ የግምገማ ውጤቱን መሠረት በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ የኤክስቴንሽን አገልግሎቱን የሚያሳልጥ ሥርዓትና የአሰራር መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ የጋራ ግንዛቤ  ይፈጥራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • የኩታ ገጠምና ሰፋፊ እርሻዎች የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን  ውጤታማ  የሚያደርጉ የአሰራር ሥርዓቶችና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ያስተዋውቃል፣ ግንዛቤ ይፈጥራል፣ ለተግባራዊነቱም አብሮ ይሰራል፣
  • የግብርና ሜካናይዜሽን ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥናቶችን ያጠናል፣ ሥርዓትና የአሰራር መመሪያዎችን በማዘጋጀት ያስተዋውቃል፣
  • በእርሻና ሆርቲካልቸር፣ በመስኖ ልማት እና በግብርና ሜካናይዜችን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ዙሪያ የሚሰሩ የልማት አካላትን ይለያል፣ የሥራ ትስስር ይፈጥራል፤አብሮም ይሰራል፡፡
  • ለደንበኞች ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመረጽ የማሻሻያ ስር ነቀል ለውጥ በሚያስፈልግበት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፣
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት የለውጥ ሀይሎችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት አርአያ በመሆን ለውጤት የሚያነሳሳ የሥራ አካባቢን ያመቻቻል፣
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን የአቅም ክፍተት ይለያል፣ ክፍተቱ በአጭርና በረጅም ጊዜ ስልጠናዎች እንዲሞላ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
  • ልዩ ልዩ ሀብት አመንጭ የሆኑ ኘሮጀክቶች እንዲቀረጹ ያደርጋል፣ ይቀርጻል፣
  • የሥራ ሂደቶች በሚመድቧቸው ባለሙያዎች ተሳትፎ የኅብረተሰብ ችግርና ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፤ እንዲካሄድ ያደርጋል፣ ጥናቱን በዋናነት ያስተባብራል
  • ሴቶችና ወጣቶች የልማቱ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የአሰራር ስልት ይቀይሳል፣ በተግባር ተጠቃሚነታቸውንም በመስክ በመገኘት ያረጋግጣል፤
  • የእማወራና የባለትዳር ሴቶችን የሥራ ጫና ሊቀንሱ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮች እንዲቀርቡ ከምርምርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣
  • የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን አርሶ አደሮች፣ የግል ባለሀብቶችና ሌሎችም ለምርታማነት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የሚበረታቱበትን ስልት በመንደፍ እንዲተገበር ያደርጋል፣
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር  ኤክስቴንሽን  አገልግሎት  ባለሙያዎች  በተሰጡ  የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች  እና  ሌሎች  ተጓዳኝ  ጥናቶች  እንዲካሄዱ  ሁኔታዎችን  ያመቻቻል፣  የተጠኑ ጥናቶችን ይገመግማል፣ ግብዓቶችን በመጨመር  የመጨረሻ  መልክ  ያስይዛል፣  ለውሳኔ  ሰጭ አካል በማቅረብ ያስወስናል፤
  • የተሸለ ተሞክሮ ያላቸውን አገሮች በመምረጥ የልምድ ልውውጥ ያደርጋል፤ተሞክሮዎች እንዲቀመሩና እንዲስፋፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በተግባር ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፤
  • የተዘጋጁ ረቂቅ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የስራ ማንዋሎችን ይገመግማል፣ ግብዓት ይሰጣል የመጨረሻ መልክ ያስይዛል፤
  • የእርሻና ሆርቲካልቸር አክስቴንሽን አገልግሎትን ሊያፋጥኑ የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችን ለማስፋፋት የሚያግዙ የማስተማሪያ የአሰራር ቁሳቁሶች እንዲዘጋጁ በተጨማሪም የተሻሉ አፈጻጸሞችንና የአካባቢ በቀል ልምድና ተሞክሮዎችን በመለየት የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ዝግጅት ያስተባብራል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣

Publications

PFS Guideline

FFS Guideline

Best Practice Guideline

ADPLAC Guideline

Pastoral and Agro Pastoral Extension System

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.