የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ
የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሰብልና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ሆኖ የሆርቲካልቸር ሰብሎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፡-
- የሆርቲካልቸር ልማት አቅም የመገንባትና የማሳደግ ስራዎችን መምራት እንዲሁም በሆርቲካልቸር ልማቱ ውስጥ የቁጥጥር እና የጥራት ማረጋገጥ ተግባራት በአግባቡ መከናወናቸውን በበላይነት የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፤
- ለሆርቲካልቸር ልማቱ የሚያስፈልጉና በየደረጃው ባሉ ስትራቴጂካዊ ውሳኔዎችን ለሚሰጡ አካላት የሚያገለግሉ የተደራጁ መሠረታዊ የሆርቲካልቸር ልማት መረጃዎች መኖራቸውን ያረጋግጣል፤
- ለፖሊሲ እና ስትራቴጂ ቀረፃ እና ትግበራ የሚጠቅሙ ያላቸውን መነሻ ሀሳቦችን ማመላከት እና ለቀረቡትም ማረጋገጫ ይሰጣል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት በቀጥታ የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ደረጃዎችና ተግባራት ተቀባይነት ማግኘታቸውንና ተሻሽለውም መተግበራቸውን ይከታተላል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን የሚደግፉ የቴክኖሎጂዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች ልየታ፣ መረጣ፣ ጥንቅር እና የማላመድ ተግባራትን በበላይነት ይመራል፤
- በሆርቲካልቸር ልማቱ ውስጥ አስፈላጊ የቁጥጥር ደረጃዎች እና ትግበራዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን በበላይነት ይመራል፤
- የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግና የፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል በጋራ በማፅደቅ ለተፈፃሚነታቸው አስፈላጊውን ሀብት እንዲመደብ ያደርጋል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት ውጤታማነት ከልህቀት ማዕከልነት አኳያ እንዲሁም የስልጠና ፕሮግራሞችና ጠቃሚ ሀሳቦችን በማፍለቅ ሂደት በበላይነት ይሠራል፤
- በሆርቲካልቸር ልማት የግብርና ውስጥ ባሉ ክፍሎች መካከል የዕውቀት ልውውጥ እንዲኖር እንዲሁም የማበረታቻ ሥራዎች መኖራቸውን ያረጋግጣል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት የሥራ ዕቅድ እና ትግበራው በበላይነት በመምራት ይቆጣጠራል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት ፍትሃዊ በጀት አጠቃቀም ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት አስፈላጊ የሰው ኃይል ልየታ እና መሟላት ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት ፖሊሲዎች እና የትግበራ የሙያ ደረጃዎች በትክክል መዋቀራቸውን እንዲሁም ባለተቋረጠ አግባብ መተግበራቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት ሪፖርቶች ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱና በጥራት መቅረባቸውን በበላይነት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት ሙያ ክፍል ሠራተኞች የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ ወቅቱን የጠበቀ የአፈፃፀም ግምገማ፣ የመምራት እና የማብቃት እንዲሁም አፈፃፀምን የተመለከቱ ውይይቶች እና ግብረ-መልስ እንዲኖር በማድረግ ድጋፍ ያደርጋል፤
- የሆርቲካልቸር ልማት የክሂሎት እና ብቃት ፍላጎቶች ለማሟላት ስልታዊ የልየታ ስራዎችን በበላይነት ይመራል፤
- የተለያዩ ውሳኔዎችን ለመስጠት የሚያስችሉ ኮሚቴዎች ወይም አደረጃጀቶች እንዲኖሩ በማድረግ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ድርሻ በመውሰድ ተሳትፎ ማድረግ፤