የስርዓተ ምግብ ማስተበናበሪያ ጽ/ቤት
የምግብና ስርዓተ-ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ተጠሪነት ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ያከናውናል፡-
- በዘላቂነት የህብረተሰቡን የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት ለማሟላት በምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለፀጉ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ህብረተሰቡ ሊገዛቸው የሚችለዉ፣ ለማኅበረሰቡ ወግና ባህል ተስማሚ የሆኑ፣ ደህንነታቸውና ጥራታቸው የተጠበቀ እና ለእለታዊ የምግብ ንጥረ ነገር ፍላጎት በቂ የሆነ ምግብ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ መመገብ የሚያስችሉ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፤
- የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ጉዳዮችን በግብርና ሴክተሩ ውስጥ በተለያዩ ፖሊሲዎች፣ አስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች ውስጥ ተካተው እንዲተገበሩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ያከናውናል፣ ይደግፋል፣ ያስተባብራል፣ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- የሥርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ረቂቆችን አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ስትራቴጂዎችን ፓኬጆችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃዉ አፈፃፀማቸውን በበላይነት ይከታተል፤ ያስተባበር፣ ይመራል፤
- በሀገር አቀፍ ደረጃ አዳዲስ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ቴክኖሎጂዎችና የተሻሻሉ አሰራሮች፣ ዘላቂ የሆነ የባህሪና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚረዱ የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ስትራቴጂዎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ ይቀርጻል፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችንና ፓኬጆችን ያዘጋጃል፣ የትምህርት ተቋማትና የግብርና ቴክኒክ ኮሌጆች ሥርዓተ ምግብ ተኮር ግብርናን በካሪኩለማቸው እንዲያካትቱ ያደርጋል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- የአካባቢን የማምረት አቅምና ሀብት መሰረት ያደረገ የግብርና ክላስተር አመራረት ላይ አርሶ/አርብቶ/ከፊል አርብቶ አደሩ የተሰባጠረ(diversified diet) የአመጋገብ ስርዓተ እንዲኖር የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
- በምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለጸጉ እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ በተፈጥሮ የሚገኙ እና በተወሰኑ ክፍሎች ብቻ ለምግብነት የሚውሉ ሆኖም መቀንጨርን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያላቸውን ምግቦች ላይ ጥናቶች እንዲካሄዱ ያደርጋል፣ የተጠኑ ጥናቶችን ይገመግማል፣ ግኝቶችን ወደተግባር እንዲገባ ያደርጋል፤
- በሀገር አቀፍ ደረጃ የማህበረሰቡን የአመጋገብ ስርዓት ላይ የዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፣ ጥናቱን በዋናነት ያስተባብራል፣ መረጃው እንዲደራጅ በማድረግ ለውሳኔ ሰጪ አካላት ያቀርባል፤
- የምግብ ብክነትን ለመቀነስ እና የምግብ ደህንነት ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ይለያል፣የምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ይደግፋል፣ ለአ/አደሩና ለግል ባለሀብቱ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማልና አቅጣጫም ይሰጣል፤
- የተሰባጠረ የአመጋገብ ሥርዓት በማስረጽ የስርዓተምግብ መጓደል ችግሮችን በመቅረፍ የተሻለ ለውጥ ያመጡ ተሞክሮዎች፣ አሰራሮችነና ቴክኖሎጂዎችን፣ ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የሚያሰራጭበትን ስልት ይነድፋል፤
- የምግብ ንጥረ ነገር ይዘት እንዳይባክን የሚያደርጉ፣ የሴቶችን ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ እና አዋጭ የሆኑ የሥርዓተ ምግብ ቴክኖሎጂ ፍላጎት በጥናት እንዲለይ ያደርጋል፣ ወደ ማህበረሰቡ የሚሰራጩበትንና የማላመድ ስራ ያስተባብራል፤
- በአርሶ አደሩ አካባቢ ጥቅም ላይ በመዋል ያሉ ባህላዊ የምግብ ማቆያ ዘዴዎችን ያጠናል፤ ከተሻሻሉ አሰራሮች ጋር ተዋህደው የተሻለ ጠቀሜታ የሚሰጡበትን መንገድ ያመቻቻል፤
- የምግብና የስርዓተ-ምግብ ሁኔታ ትንተና መረጃዎችን የሚሰበሰቡበት ስልቶች፣ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን ያፈላልጋል፣ ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፤
- የስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርና ጽንሰሀሳብ የሴክተሩ ይእቅድ ትግበራ ክትትል እና ግምገማ አካል ለማድረግ የአሰራር ስልቶችን ይነድፋል፣ ያስተባብራል፣ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- የአርሶ/ከፊል/አርብቶ አደሩን የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል የሚረዱ የባህሪ ለውጥ ተግባቦት ስራዎችን በማከናወን ከሚያገኙት ምርት የተሰባጠረ ምግብ እንዲመገቡ መደግፍ፣ በየደረጃው ያለውን የሥርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና ተግባራት አፈፃፀም መከታተል፣ መገምገምና ውሳኔ የሚፈልጉትን ለበላይ አካላት ማሳወቅ፤
- የግብርናውን ሴክተር ስራዎች የሀገሪቱን የምግብ እና ሥረዓተ ምግብ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ መሰረት ባደረገ መልኩ ለመምራት ተጠያቂ አካል መፍጠር እንዲቻል በየደረጃው ባሉ አደረጃጀቶች የምግብና ሥርዓተ ምግብ መዋቅራዊ አደረጃጀት እንዲፈጠር ያያርጋል፣ሥራው የሚመራበትን የአሰራር ስርዓት ያዘጋጃል፤
- ሥነ-ምህዳርንና የማህረሰቡን የአኗኗር ዘይቤ መሰረት ያደረገ የሥርዓተ ምግብ መጓደል ችግር ለመፍታት የሚያስችል ጥናቶችን በማድረግ መመሪያዎች፣ ማንዋሎች እና ፓኬጆችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
- የግብርናውን ሴክተር የስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርና ስራዎችን በብቃት እንዲተገበር የስርዓተ- ምግብ ተኮር ግብርና ሰርቶ ማሳያ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችን ያከናውናል፤
- በግብርናው ሴክተር የስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርና ስራዎች ትግበራ ለማሳለጥ እንዲቻል የሥርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና የሥልጠና ማኗል እና የስልጠና መርጃ መሰረተ የአቅም ግንባታ ስልጥና ይሰጣል፤
- ከምርምር ማዕከላት የተለቀቁ አዳዲስና የተሻሻሉ ለሥርዓተ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ አስተዋፅኦ ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች ይለያል፣ ሰርቶ ማሳያ ያካሂዳል፣ የፓኬጅ አካል በማድረግ ስልጠና ይሰጣል፤
- ከምርምር ማዕከላት፣ ከየትምህርት ተቋማት፣ ከአጋር አካላት እና ከግል የግብርና ለስርዓተ ምግብ መሻሻል የሚወጡ ቴክኖሎጂዎች እና በምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለፀጉ የምግብ አይነቶችን ከሚመለከታቸውን አካላት ጋር በማቀናጀት እንዲተዋወቁ ያደርጋል፤
- በምርት እና ምግብ ደህንነት ጉድለት ምክንያት እየተከሰተ ያለውን የምግብ ብክነት፣ የኤክስፖርት ሪጄክሽን፣ እና የህብረተሰብ ጤና እክል እንዳይፈጠር የማስፈጸሚያ ስልቶችንና አሰራሮች ያዘጋጃል፤
- ስነ-ምህዳርን ማዕከል ያደረጉና በምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለጸጉ ምርቶችን የምግብ አዘገጃጃት መመሪያ (Agroecology based Food recipe guideline ) እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
- የምግብና ስርዓተ ምግብ ሰርቶ ማሳያ ማዕከላት /Nutrition Demonstration Center (NDC)/ እና ሥርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና ሞዴል መንደር /Nutrition Sensitive Agriculture Model Village (NSA-MV)/ ለመመስረት መስፈርትና ዲዛይን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
- በአገር አቀፍ ደረጃ የምግብና ስርዓተ ምግብ ሰርቶ ማሳያ ተቋማትን ለማቋቋም (NDC)፣ ሞዴል የስርዓተ ምግብ መንደር ለመፍጠር (NSA-MV) የሚረዱ ከፍተኛ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን እንዲዘጋጁና እንዲተገበሩ በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፡፡
- የምግብ ደህንነት ማረጋገጫ መስፈርቶች፣ የህግ ማዕቀፍ ሰነድ እንዲለዩና እንዲወጡ ያደርጋል፣ በመስፈርቶቹ መሰረት የምግብ ደህንነት ማረጋገጫ ፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ይዘረጋል፤
- የግብርና ምርት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በንጥረ-ነገር ይዘቱ የበለፀገ የተሰባጠረና ጤናማነቱ የተጠበቀ የአመራረት እና አጠቃቀም ሥርዓት መኖሩን ያረጋግጣል፡፡
- የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ሀገራዊ የአመጋገብ ሥርዓት ስትራቴጂ አፈጻጸምን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፡፡
- በብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በምግብ ንጥረ ይዘታቸው የበለጸጉ የግብርና ምርቶች መረጃ በልዩነት እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡
- በሀገር አቀፍ ደረጃ የምግብ ንጥረ ይዘት ክፍተት በጥናት እንዲለይ (Nutrient gap Analysis) ያስተባብራል፤ ምርምር ማዕከላት ክፍተቱን መሰረት ያደረገ በስነህይወታዊ የበለጸገ የግብርና ምርት እንዲያፈልቁ ያስተባብራል፤ የፈለቁት ወደ ማህረሰቡ የሚገቡትን የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፡፡
- የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የፖሊሲ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች ያዘጋጃል፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓተ ፍኖተ ካርታ (Ethiopia`s Food System, Road map and High level interventions) ያዘጋጃል፤ አፈጻጸሙን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይከታተላል፡፡
- የግብርናውን ሴክተር የሥርዓተ ምግብ ተኮር አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል፤