FDRE Ministry of Agriculture

2ኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በሰመራ ከተማ መካሄድ ጀመረ

ሰመራ፣ መስከረም 10/2019 (ግብርና ሚኒስቴር) 2ኛው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ዛሬ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ከዛሬ መስከረም 10 እስከ 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደው ይህ ፌስቲቫል በግብርና ሚኒስቴር፣ በ Khalifa International Award for Date Palm and Agricultural Innovation እና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባለው የቴምር ዘርፍ ላይ ኢንቨስትመንትን፣ ፈጠራንና ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር የቴምር አምራቾችን፣ ባለሀብቶችን፣ ተመራማሪዎችን፣ የልማት አጋሮችንና ፖሊሲ አውጪዎችን በአንድ ላይ ያገናኛል።

የአፋር ክልል ርዕሰመስተዳደር አወል አርባ በክልሉ

በቴምር ምርታማነትን ለማሳደግብ የምርምር ስራዎችን በማስፋት እንዲሁም የአምራቹን ማህበረሰብ አቅም በመገንባት ምርታማነትን ለመጨመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወንዳለ ሀብታሙ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በተለይም በቆላማ አካባቢዎች ለቴምር ምርት ተስማሚ የሆነ ሥነ-ምህዳር እንዳላት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባለው የቴምር ዘርፍ ላይ ኢንቨስትመንትን፣ ፈጠራንና ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን ፌስቲቫሉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ዶ/ር ወንዳለ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ አማባሳደር አብደልሀሰን አልሻምዚ በበኩላቸው ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ መካከል እያደገ የመጣውን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቴምር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሙያዊና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ አጋርነቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

የ Khalifa International Award for Date Palm and Agricultural Innovation ዋና ጸሃፊ አብደልወሃብ አልቡካሪ ዛይድ (ዶ/ር) ይህ ፌስቲቫል ከአካባቢያዊ ሁነት ባለፈ በመላው አፍሪካ የእውቀት ሽግግር እና የትብብር ማዕከል ሆኖ ለማገልገል ያለመ ነው ብለዋል።

ለ3 ቀናት በሚቆየው 2ኛው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ጥናታዊ ፅሁፎች፣ የመስክ ጉብብት እንዲሁም የቴምር ምርት አውደ-ርዕይ ይካሄዳል።