FDRE Ministry of Agriculture

ጥምረት ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት!

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር «ጥምረት ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት» ጉባኤን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል፡፡

ጉባኤው በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከርና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

በግብርና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ገነት አብደላ፤ ጉባኤው የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን በማረጋገጥና ሁሉ የማህበረሰብ ክፍልን ያካተተ ልማት በማምጣት ለዘላቂ የግብርና ዕድገት ሚናው የላቀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አጋርነትና ጥምረትን በማጠናከር በዘርፉ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማስፈን የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ስራ አስፈፃሚዋ አሳስበዋል፡፡

በጉባኤው የ“Women’s Empowerment through Gender Transformative Market Opportunities (WEGO) ፕሮጀክት ከግብርና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ጋር በመተባበ በአማራና ሲዳማ ክልሎች የተሰሩ ስራዎችን ጨምሮ የአለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ባዘጋጀው የምግብ እና አመጋገብ የበጎ ፍቃድ መመሪያ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

ጥምረት ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የትምህርት እና የምርምር ተቋማትን ጨምሮ ከ 80 በላይ ፍቃደኛ አባላትን የያዘ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *